የማጅራት ገትር ወረርሺኝ( ኣንቅፂ) ድርቅ በመታቸው ኣከባቢዎች ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
እሁድ 21 / 02 / 2008 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ማይክሮፎን በመያዝ ከ1 ዓመት እስከ 29 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኝ ማንኛውም ሰው የማጅራት ገትር( ኣንቅፂ) ክትባት መውሰድ እንዳለባቸው በጥብቅ እየታዘዘ ነው።
Amdom Gebreslasie

በኣሁኑ ሰዓት የትግራይ ክልል ጨምሮ በድርቅ የተጠቁ ኣከባቢዎች በማጅራት ገትር ወረርሽኝ በሽታ ምልክቶች እንዳጋጠመና የመከላከል ስራ ካልተሰራ ወደ ህዝቡ መዛመት ሊያጋጥም እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንዳሉ ይገለፃል።
ድርቅ ያጠቃቸው ኣከባቢዎች በምግብና ውሃ እጥረት የሰው ሂወት እየጠፋ ያለ ከመሆኑ በላይ ሊነሳ የሚችለው የወረርሽኝ በሽታዎች በድርቅ ከተጠቁ ኣከባቢዎች ኣልፎ ወደ ተቀረው የሃገሪቱ ክፍሎች ሊዛመትና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
በትግራይ ሰሜን ምዕራብና ማእከላዊ ዞኖች እየተስፋፋ ያለው ሆድ እየነፋ የሚገድል በሽታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ሂወት እየቀዘፈ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን እስካሁን ምንም ዓይነት የመድሓኒት ይሁን ክትባት ኣልተገኘለትም።
መንግስት በሽታው ከ11 ዓመታት በላይ ደብቆ በመያዙ እስካሁን መድሃኒት ሳይገኝለት በርካታ ሂወት እያጠፋ ይገኛል።
መንግስት ዛሬ እያወጀው ያለው የማጅራት ገትር( ኣንቅፂ ) ወረርሽኝ ክትባት ዕድሚያቹ ከ1_29 ዓመት የሆናቹ እንድትከተቡ እንመክራለን።
ኣዎ ድርቅ ባስከተለው የምግብና የውሃ እጥረት ሊነሱ የሚችሉ ወረርሽኞች ነቅተን ልንጠብቅ ይገባናል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO………!

