ሊቢያ የስድስት ሚሊን የሚገመተዉ ሕዝቧ የነብስ ወከፍ ገቢ ከአስራ-አራት ሺሕ ዶላር በላይ ነበር።ከዘጠና በመቶ የሚበልጥ ሕዝቧ የተማረ ነበር። በነዳጅ ላይ የተመሠረተዉ ምጣኔ ሐብቷ በአመት በአማካይ 10,5 ከመቶ ያድግ ነበር።ዛሬ ሐብት ንብረት-የሕዝቧ ቅምጥል ኑሮ አይደለም አንድ ሐገርነቷም ያዉ ነበር ነዉ።

በመጪው ዓመት በታህሳስ ወር ሥራውን እንደሚጀምር የተነገረው «የምስራቅ አፍሪቃ ፈጣን ጣልቃ ገብ ጦር » ሰላም እና መረጋጋት በራቃቸው የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ወታደሮችን እያሰማራ አፋጣኝ ርዳታ ለመስጠት አቅዷል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን አደጋ የሚያስከትሉ መድሐኒቶች ሳይቀሩ በየመድሐኒት መደብሩ እንደልብ መሸጣቸዉ በሠፊዉ እየተነገረ ነዉ።በተለይ አስቸኳይ የፅንስ መከላከያ እንክብል (Emergency Ccontraceptive pill)ን ካንድ ጊዜ በላይ ከሐኪም ትዕዛዝ ዉጪ መዉሰድ በተጠቃሚዎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ባለሙያዎች እየመከሩ ነዉ።

የኢጣሊያ የባህር ኃይል ዛሬ እንዳስታወቀው በላምፔዱዛ የባህር መዳረሻ 18 አስክሬኖችን ሰብስቧል። የጀልባው ሞተር ላይ ጉዳት በመድረሱ ስደተኞቹ አደጋ እንደገጠማቸው ያስታወቀው የባህር ኃይል አክሎም «ሲሮ» የተባለው የባህር ኃይል መርከብ 73 ሰዎችን ከባህር ማትረፉን ገልጿል።

በምዕራብ አፍሪቃ ኤቦላ ተኀዋሲ አብዝቶ ጉዳት እያደረሰ ካለባቸው ሀገራት ውስጥ ላይቤርያ ናት። ከ15 የላይቤርያ ግዛቶች መካከል በስምንቱ የአስቸኳዩ ጊዜ ታውጆዋል። ስለበሽታው በቂ መረጃ የሌለው እና በሰበቡም ስጋት ያደረበባቸው የሀገሪቱ ነዋሪዎቹ በመንግሥታቸው ላይ እምነት አጥተዋል።

ዛሬ ወደ ኪይቭ የተጓዙት የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፕሮሼንኮ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የርዳታ ቁሳቁስ የጫኑት የሩስያ ከባድ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከምስራቅ ዩክሬይን መዉጣታቸዉ ተነገረ።

የኢትዮጵያ መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች ሃገሪቱን ጥለው መሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል።

ወደ ደቡብ ሱዳን በብዛት የሚገባው የጦር መሳሪያ ጦርነቱ እንዳይቆም እያደረገ ነው ሲሉ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር ተቆጣጣሪዎች ያሳስባሉ ።አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ደግሞ በደቡብ ሱዳን ላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ማዕቀብ እንዲጣል እየጠየቁ ነው ።

የኢትዮጵያ መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች ሃገሪቱን ጥለው መሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል።

በ ዩ ኤስ አሜሪካ የእርዳታ ድርጅት (USAID)አስተባባሪነት፣ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ላይ ያተኮረ ተመራማሪዎችንና ባለሙያዎችን ያሰባሰበ ዐውደ ጥናት አዲስ አበባ ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው። ከአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም አንስቶ የጥራጥሬ እኽልንና

በምሥራቅ ዩክሬን ለተባባሰዉ ዉጊያ መፍትሄ ለመፈለግ ሁለት እንቅስቃሴዎች በተከታታይ ተይዘዋል። በመጪዉ ሳምንት የዩክሬን ፕሬዝደንት ፔትሮ ፕሮሼንኮና በሀገራቸዉ በተፈጠረዉ ብጥብጥ እጇን ከታለች በማለት የሚከሷት የሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ቤላሩስ ላይ ተገናኝተዉ እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።

የኤቦላ በሽታ ዩጋንዳ ውስጥ አራት ጊዜ ተከስቶ ነበር። በኤቦላ ተኀዋሲ የተያዘው ሰው ቁጥር ግን በእጅ ጣት የሚቆጠር ነበር። ይህችው የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገር ምን ብታደርግ ነበር ያኔ የበሽታውን ስርጭት ባለበት ማስቆም የቻለችው? በምዕራብ አፍሪቃ ለምን ይህን ማድረግ አልተቻለም?

ኢራቅ ውስጥ አክራሪ እስላማዊ ኃይል የተሰኘውን ፣ (IS) በሚል ምህጻረ ቃል የታወቀውን የሱኒዎች ታጣቂ ኃይል ለመመከት ፤ የሰሜን ኢራቅ ራስ ገዝ መስተዳድር፣ ኩርዲስታን ፣ ምን ዓይነት የጦር መሣሪያ ያስፈልገዋል? ከጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክ

«ሁሌም ሰባት ቀን ሰርቼ ሶስት ቀን እረፍት፤ ሰባት ቀን ሰርቼ አራት ቀን ረፍት ቋሚ ፕላን ባለበት የኤርፖርት ስራዬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት እገባና ስድስት ሰዓት ሰርቼ ማታ ዘጠኝ ሰዓት እወጣለሁ፤ ማታ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ እጀምርና፤ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል የሚያልቅ የሁለት ሰዓት ሥራ እገባና እንደጨረስኩ፤

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ባለፈው ወር ማለቂያ ገደማ የስደተኞችን መስተንግዶ በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በዚህ ረገድ ከኬንያ ልቃ መገኘቷን ከሰሞኑ በሰጠው መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

የኤቦላ በሽታ ዩጋንዳ ውስጥ አራት ጊዜ ተከስቶ ነበር። በኤቦላ ተኀዋሲ የተያዘው ሰው ቁጥር ግን በእጅ ጣት የሚቆጠር ነበር። ይህችው የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገር ምን ብታደርግ ነበር ያኔ የበሽታውን ስርጭት ባለበት ማስቆም የቻለችው? በምዕራብ አፍሪቃ ለምን ይህን ማድረግ አልተቻለም?

ክረምቱን በማጠናከሪያ ትምህርት በንባብ ወይም በእረፍት ያሳለፉ ተማሪዎች ለመጪው የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጓቸውን እንደ ደብተር ብዕር መፃህፍትና የመሳሰሉትን በብዛት ሲገዙ የሚታዩት በዚህ ወቅት ላይ ነው ።

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላትን ለመሸምገል የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ)የሚያደርገዉ ጥረት ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም እስካሁን ያስገኘዉ ተጨባጭ ዉጤት የለም። በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር በሚመራው በመንግሥት ጦር እና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት በሪያክ ማቻር በሚመራው አማፂ ሐይል

ሳይንስ በአመዛኙ ለሰዎች የተሻሻለ ኑሮ በጅቷል ወይም በረከት ሆኗል ቢባልም በአንዳንድ ረገድ የርግማን ያህል የሚታይበት እንዳልታጣ የታወቀ ነው። ይህ የሆነው ግን በመሠረቱ፣ ምርምሩ፣ የፈጠራው ውጤት ፤ ግኝቱ ፣ መጥፎ

በዩናይትድ ስቴትስዋ የሚዙሪ ግዛትበምትገኘው በፈርግሰን ከተማ አንድ ጥቁር ወጣት በነጭ ፖሊስ ከተገደለ በኋላ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም አልቆመም ። ትናንት ማታም ተቃዋሚዎች በፖሊስ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰምቷል ። ትንናት ማታ ተቃዋሚዎች ውሃና ሽንት የያዙ ፕላስቲኮች ወደ ፖሊስ መወርወራቸውን ፓሊስ አስታውቋል ።

እስከከዛሬ ከ1,100 ሰዎች በላይ ሕይወት ያጠፋው እና ምልክቱም ከ2,100 በሚበልጡ ሰዎች ላይ የታየው የኤቦላ በሽታ የብዙዎቹን የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት መንግሥታትን አሳስቦዋል። ኤቦላ ወደየሀገሮቻቸው እንዳይዛመት የሰጉት ሀገራት ያየር ማረፊያዎቻቸውን እና ወደቦቻቸውን በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገራት ለሚመጡ መንገደኞች ዘግተዋል።

በዓለማችን ከአራት ሰዎች አንዱ በህይወት ዘመኑ አንዴ የአእምሮ ወይም የስርዓተ ነርቭ መዛባት ሊያጋጥመዉ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ለችግሩ የሚሆነዉ ህክምና ቢኖርም ፍፁም ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት የሚጠቀምበት እንደሌለ ነዉ ድርጅቱ የሚያመለክተዉ።

ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም. በአንዋር መስጊድ በተፈጠረው ግጭት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሪት ወይንሸት ሞላና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድን በዋስ ተፈተዋል።

የጀርመን ፊደራል የስለላ መሥሪያ ቤት ቱርክን ሲሰልል ቆይቷል የቀድሞዋንና የአሁኑን የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስልኮች ጠልፏል መባሉ ማነጋገሩን ቀጥሏል ። የጀርመን ፖለቲከኞች እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም ያልተናገረው የሐገሪቱ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ ግፊት እያደረጉ ነው ።

በዓለማችን ከአራት ሰዎች አንዱ በህይወት ዘመኑ አንዴ የአእምሮ ወይም የስርዓተ ነርቭ መዛባት ሊያጋጥመዉ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ለችግሩ የሚሆነዉ ህክምና ቢኖርም ፍፁም ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት የሚጠቀምበት እንደሌለ ነዉ ድርጅቱ የሚያመለክተዉ።

በግጭት ጦርነት እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የተሠማሩ ወገኖች ተግባር ማለትም ሰብዓዊነት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነዉ ዛሬ። ለሰብዓዊ ተግባራት ተሠማርተዉ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋልጠዉ ህይወታቸዉን የሚያጡ ወገኖች ዛሬ ዛሬ ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ።

15 ቱ የደቡባዊ አፍሪቃ መንግሥታት የልማት ትብብር ድርጅት፣ በምኅፃሩ የ«ሳዴክ» መሪዎች ያካባቢያቸውን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋት ተስማሙ። የኢንዱስትሪው ዘርፍ በ«ሳዴክ» የትብብር አጀንዳ ውስጥ ዓቢይ ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ርዕሳነ ብሔራቱ ትናንት በዚምባብዌ የሁለት ቀናት ጉባያቸውን ባጠናቀቁበት ጊዜ አስታውቀዋል።

እስከከዛሬ ከ1,100 ሰዎች በላይ ሕይወት ያጠፋው እና ምልክቱም ከ2,100 በሚበልጡ ሰዎች ላይ የታየው የኤቦላ በሽታ የብዙዎቹን የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት መንግሥታትን አሳስቦዋል። ኤቦላ ወደየሀገሮቻቸው እንዳይዛመት የሰጉት ሀገራት ያየር ማረፊያዎቻቸውን እና ወደቦቻቸውን በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገራት ለሚመጡ መንገደኞች ዘግተዋል።

ዲክስር ፊልክንስ በቅርቡ እንደፃፉት «ጅአፈሪን ልታስወግደዉ ትችላለሕ» ጠየቁ አሉ ቡሽ።«ምንገዶኝ» የአምባሳደሩ መልስ ነበር።ኢራቅ ሉአላዊት ሐገርናት ተብሎ የለም።ሉአላዊነቷን የሰጧት የሾሙላትን መሪ ሲያስወግዱባት ወይም የሚሹትን ሲሾሙባት ግን ሉዓላዊነቷን መዳፈር አይደለም።ጅአፈሪ ተወገዱ።ኑሪ አል-መሊኪይ ተተኩ።ባለፈዉ ሳምንት ማሊኪይ ተወገዱ።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ኃይል ለመመሥረት መስማማታቸዉን በይፋ ተናግረዋል። የመገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት፤ ሁለቱ ሃገራት ለማቋቋም የወሰኑት የመከላከያ ኃይል አንድ እዝ ስር የሚታዘዝ ነዉ። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ፤ መሰጡት መግለጫ ጥምሩ ጦር እስከ መጭዉ መስከረም ወር ማብቂያ ድረስ እንደሚቋቋም ገልፀዋል።

አምስት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሃላፊነታቸው የለቀቁበት ምክንያት አልገባኝም ሲሉ የፓርቲው ፕሬዝደንቱ አስታወቁ።የፓርቲዉ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው እንደሚሉት ከሥልጣን የለቀቁት አምስቱ ሰዎች በደብዳቤ ከገለፁት በስተቀር የሚያዉቁት የለም።

የኤቦላ ተኀዋሲ ወይም ቫይረስ» መዛመት እስካሁን ከታሰበዉ በላይ አስከፊ ነዉ ሲል የዓለም የጤና ድርጅት «WHO» ባለፈዉ ሳምንት ማስጠንቀቅያ ማዉጣቱ ይታወቃል። በምዕራብ አፍሪቃ በአሁኑ ወቅት በኤቦላ ቫይረስ የተያዙ አልያም በበሽታዉ የሞቱት ቁጥር በርግጥ ስንት እንደሆን መናገር አዳጋች ሆነዋል።

በአፍሪቃው ክፍለ-ዓለም ፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት በማሳየት ላይ መሆናቸው ከሚነገርላቸው ጥቂት ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። እ ጎ አ እስከ 2020 ባለ ማዕከላዊ ገቢ ሀገር ለመሆን እቅድ እንዳላት የምትገልጸውና «ይህን ትልም የማሳካት

የኤቦላ ወረርሽን የአፍሪቃ መንግሥታትን ክፉኛ አሳስቧል። የህዝቡ ጤንነት ስጋት ላይ በመዉደቁ ስትል ኬንያ ቆራጥ ርምጃ ስትወስድ የናይጄሪያ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ ከሙያዊ ግዴታቸው በመሸሽ ላይ ይገኛሉ።

በሊቢያ ከጥቂት ቀናት በፊት ስራውን የጀመረው አዲሱ ምክር ቤት የተመድ በተለያዩት ተቀናቃኝ ሚሊሺያ ቡድኖች መካከል ከብዙ ሳምንታት ወዲህ በቀጠለው ውጊያ ሰበብ ትልቅ ችግር ውስጥ የምትገኘዋን ሀገራቸውን እንዲረዳ

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ባግዳድ ተገኝተው ለኢራቅ መንግሥት ድጋፋቸውን ገለፁ። ሀገሪቱ በአማፂ ቡድኑ ላይ የምታደርገው ትግል ትክክል መሆኑን ለኢራቁ የፖለቲካ አቻቸው ሁሴን አል ሻሪስታኒ በመግለፅ ለሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ከምንም በላይ ሰብዓዊ ርዳታ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

እስራኤል እና ሃማስ መካከል የተደረሰዉ የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬም መዝለቁ እየተገለጸ ነዉ። የጋዛ ኗሪዎች ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ ለመጀመሪያ ዛሬ በሰላም የዕለተ ዓርብ ጸሎትን መካፈል መቻላቸዉ ተዘግቧል።

ኢራቅ ውስጥ ለአክራሪዎቹ የሱኒ ታጣቂ ቡድን ኃይሎች ጥቃት የተጋለጡትን ሰሜን ኢራቅ ውስጥ በጭንቅ ላይ የሚገኙትን ስደተኞች ለመታደግ እርዳታ ማቅረቡ ተገቢ መሆኑን የጀርመን መንግሥት ተስማምቶበታል ።

የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሪ አል ማሊኪ ስልጣናቸውን ለሽአቱ ለሃይደር አል አባዲ በማስረከብ ትናንት በይፋ ተሰናበቱ። ላለፉት 8 ዓመታት ኢራቅን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት አልማሊኪ ከሚያዚያው ምርጫ በኋላ ስልጣን እንዲለቁ ከሱኒዎች፣ ከኩርዶች እንዲሁም ከሺአዎች ከኢራንና ከዩናይትድ ስቴትስ በኩል ከፍተኛ ግፊት ሲደረግባቸው ቆይቷል።