ከፖለቲካ ተቃዋሞች ጎራ የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኢአዴድ፤ ከመጪዉ የ2007ዓ,ም ብሄራዊ ምርጫ በፊት በተቃዋሚዎችና በኢአዴህ መካከል የተዉጣጣ ጊዜያዊ የአደራ መንግሥት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ።

በተለያዩ የሊቢያ ከተሞች የሚካሄደው ውጊያ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችና የውጭ ዜጎች የሰቀቀን ህይወት በመግፋት ላይ ይገኛሉ ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙት መካከል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይገኙበታል ።

በኢትዮጵያ ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የቴአትር ጥበብ ዛሬም በአዲስ አበባ መድረኮች የተወሰነ ነው። ሙያውን የሚያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መበራከት ቢታይም ወጣት ተመራቂዎች ግን በሥራ ለመሠማራት እድሉን ማግኘት ከባድ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋክልቲ 38 የጽዳት ሠራተኞችን አሰናበተ። ካላንዳች ማስጠንቀቂያ እና ምክንያት ከሥራ መባረራቸውን ለዶይቸ ቬለ ያስታወቁት ሴቶች በዚህ ምክንያት ትልቅ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገልጸዋል።

በተለያዩ ሀገራት የሚካሄዱ ውዝግቦችን እየተከታተለ የመፍትሔ ሀሳብ የሚጠቁመው «ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ» ሰሞኑን ስለኤርትራ አንድ ዘገባ አውጥቷል። የ«ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ» ዘገባ በተለይ ትኩረቱን

ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በስፋት ከተዋወቁት የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች መካከል « ኤሜርጄንሲ ኮንትራሴፕቲቭ» ወይም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ

ባለፈው ቅዳሜ በአንባብያን ይጠበቁ የነበሩ ሦስት መፅሄቶችና አንድ ጋዜጣ ሳይታተሙ ቀርተዋል ። ያልታተሙት መፅሄቶችና ጋዜጣ የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ክስ እንደመሠረተባቸው ካስታወቀው አምሥት መፅሄቶችና ጋዜጣ መካከል ናቸው ።

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሪ አልማሊኪ የኢራን መንግሥት ድጋፍ እንዳላቸዉ ይነገራል። የቴህራን መንግሥት አል ማሊኪ ገና በጎርጎሪዮሳዊዉ 2006ዓ,ም ባግዳድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ለመጀመሪያ ከያዙበት ጊዜ አንስቶ አዎንታዊ አመለካከቱን ሲቸራቸዉ ታይቷል።

በሃይማኖት ተጨቁነው እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ወደሚገኝ ተራራ ተሰደው የሚገኙ 20 000 የሚደርሱ የያዚዲ እምነት ተከታዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ነው የሚሰማው። ይህም አንዳንድ ጠበብት እንደሚሉት አሜሪካ ጣልቃ ከገባች በኋላ የተገኘ ለውጥ ነው።

በምሥራቃዊው ሱዳን ገዳርፍ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሰበብ-አስባቡ የአንዳንድ አክራሪ ቡድኖች የጥላቻ ሰለባዎች ሆንን» ሲሉ ብሶታቸውን ገለጡ። በ« ኤስ ኤም ኤስ » የሚደርሱን አጫጭር መልእክቶች እንደሚሉት ከሆነ ብዙዎች

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ያለቀበት አንደኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት መቶኛ ዓመት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታስቧል ።በቅርቡ የጦርነቱ መቶኛ ዓመት ከታሰበባቸው ሃገራት አንዷ የጦርነቱ የመጀመሪያዋ ሰለባ ቤልጂግ ናት ።

ዩክሬይን በሀገርዋ ምሥራቃዊ ከፊል በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያን መካከል በቀጠለው ውጊያ ሰበብ የመሠረታዊ አቅርቦት ችግር ላጋጠመው ያካባቢው ነዋሪ ሩስያ በ280 የጭነት ተሽከርካሪዎች አጀብ ሰብዓዊ ርዳታ ልካለች፣

እ ጎ አ፣ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፣ ላለፉት 11 ዓመታት ገደማ ፣ ቱርክን በ ጠ/ሚንስትርነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት ሪቸፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ በዚያች ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዚዳንት በህዝብ እንዲመረጥ በተደረገበት ደንብ፤

የጀርመን ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድንና የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኖየር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ። ኖየርን የመረጠዉ ታዋቂዉ የጀርመን የስፖርት መጽሔት ኪከር የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮአኺም ለቭንም የዓመቱ ምርጭ አሰልጣኝ በማለት መርጧል።

ባለፈው ሳምንት 24 ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ 16 ሰዎችን በምትጭን አንዲት ታክሲ ውስጥ ተሳፍረው ሲጓዙ የትራፊክ ፖሊስ እንዳስቆማቸው እና በብሪክስተን የፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተሰምቷል።

በሃይማኖት ተጨቁነው እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ወደሚገኝ ተራራ ተሰደው የሚገኙ 20 000 የሚደርሱ የያዚዲ እምነት ተከታዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ነው የሚሰማው። ይህም አንዳንድ ጠበብት እንደሚሉት አሜሪካ ጣልቃ ከገባች በኋላ የተገኘ ለውጥ ነው።

በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት የሚያበቃበትን መንገድ የሚያፈላልገው ተቋርጦ የነበረው የሰላም ድርድር ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ቢጀምርም፣ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አንፃር የሚፋለሙት

የአንድ ሀገር መገበያያ ገንዘብ በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋዉ ወይም የመግዛት አቅሙ የሚቀንስበት አጋጣሚ በርካታ ነዉ። በተለይ ደግሞ ጠንካራ ከሚባሉት ዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች ጋ ሲወዳደር እያደር አቅሙ ዝቅ የሚልበት አጋጣሚ ነው ያለው ።

በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት የሚያበቃበትን መንገድ የሚያፈላልገው ተቋርጦ የነበረው የሰላም ድርድር ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ቢጀምርም፣ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አንፃር የሚፋለሙት

የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ‘ በሚል ርዕስበተካሄደ ውይይት ላይ የተካፈሉ ተሳታፊዎች ሴቶች መብታቸውን ለማስከበርም ሆነ በአገራቸው ተጠቃሚ ለመሆን በየመስኩ ተሳትፎአቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

በዚህ ሳምንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የሰላም ንግግር የተቋረጠው ተቃዋሚው SPLM A አንዳንድ ተወካዮች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸውን በመቃወሙ መሆኑን የድርድሩ ተካፋይ የሆኑት የሴቶች ተወካይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች በተየያዩ አጋጣሚዎች ከሀገሪቱ ሲወጡ ኖረዋል። በተለይ በዉጭ ወረሪዎች አስገዳጅነትም ይሁን፤ ቅርሶቹን ጠብቆ ለማቆየት በሚል በታሪክ አጋጣሚ ቅርሶች ከኢትዮጵያ የወጡባቸዉ ዘመናት በመረጃም ጭምር ተመዝግበዉ የሚገኙበት ሁኔታ አለ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው በንግድ በመልካም አስተዳደርና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።

በንክኪና ከሰውነት በሚወጣ ፈሳሽ በሚተላለፈው በገዳዩ ኤቦላ ምክንያት ተውሃሲው በተሰራጨባቸው ሃገራት የንግድ ልውውጥ ቀንሷል ።የአገልግሎት ሰጭ የንግድ ተቋማት ገበያም ቀዝቅዟል ።

መኢአድ ባለፈው ዓመት ሐምሌ 2005 ዓም ከ600 ጠቅላላ አባላቱ 390ው በተገኙበት ስስበባ ቢያካሂድም ምርጫ ቦርድ ግን ምልዐተ ጉባኤው አልተሟላም ሲል መዋሃድ እንደማይችሉ ማሳወቁን የአመራር አባላቱተናግረዋል ።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉባኤ ሲያካሂድ የተገኙት 285 አባላት በመሆናቸው ይህ ሕጋዊ እንዳልሆነ በፅሁፍ ማሳወቁን ገልጿል ።

አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ ሰራተኞች የመን ካለፉት ስድስት ሳምንታት በፊት ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ የሰጠቻቸው እና በእስር የሚገኙትን የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ከአበባ፣ አታክልትና ፍራፍሬ የውጭ ገበያ በዚህ ዓመት ብቻ ከ245 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳገኘች የኢትዮጵያ ዘርፉ ልማት ተቋም ዋና ዳሬክተር አቶ ዓለም ወልደገሪማ ለዶይቸ ቬለ ዛሬ ገለጹ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት -አምነስቲ ኢንተርናሽናል የናይጀሪያ ጦር የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈፅሞዋል ሲል ወቀሳ ሰንዝሯል። ይህንን ወቀሳ የናይጄሪያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዝም ብሎ አላለፈውም።

በሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባለፈው የረመዳን ጾም ወቅት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው ረብሻ ላይ ተሳትፋችኋል በሚል የተጠረጠሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን እና የአዲስ ጉዳይ የፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ ን ጉዳይ

ትምሕርት ቤቱን የምታሠራው ለሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ያቆመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ በፋሺሽት ኢጣልያ የተረሸኑት ሐምሌ 22: 1928 ዓም ነበር።

በተለያዩ አራት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የታየዉ የኤቦላ ተሕዋሲ እስካሁን ለ826 ሰዎች ህልፈተ ሕይወት ምክንያት ሆኗል። ባለፈዉ ሳምንት ሴራሊዮን ዉስጥ ተሕዋሲዉ በሽተኞችን ይረዱ የነበሩ አንድ ዶክተርን ህይወት መቅጠፉ አጀብ ተብሎለት ሳያበቃ፤ አሁንም ሌላ ዶክተር በኤቦላ መያዛቸዉን ናይጀሪያ አረጋግጣለች።