በብራዚል ፣ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከተደመደመ 2 ወር ሊሞላው ጥቂት ቀናት ናቸው የቀሩት። ሪዮ ዴ ጃኔሮ ውስጥ በዝነኛው ማራካና ስታዲየም ፤ በፍጻሜ ግጥሚያ ጀርመን ፣ አርጀንቲናን 1-0 አሸንፋ ለ 4ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት መሆኗ

ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ጄምስ ፎሌይ የተባለ ሌላ አሜሪካዊ ጋዜጠኛን በተመሳሳይ መንግድ ገድሎ ነበር። ግድያዉ ያስቆጣቸዉ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ መንግሥት በቡድኑ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስድ እየጎተጎቱ ነዉ።

ኢትዮጵያ በ2005 ዓ.ም. የጀመረችውን የቡና ስያሜዎችና የንግድ ምልክቶች የማስመዝገብ ሂደት እንደገና አነቃቃች። የኢትዮጵያን አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት በበላይነት በሚመራውና ህገወጥ የቡና ንግድንና አላግባብ የሚጣል የቡና ዋጋ ተመንን ለመከላከል፣

የዩኤስ አሜሪካ ወታደራዊ አየር ኃይል በሰው አልባ አይሮፕላን በሶማልያ የሚገኙ የአሸባብ ሚሊሽያዎች ላይ የአየር ድብደባ አካሄደ። የአየር ጥቃቱ የተካሄደዉ ትናንት ሌሊት እንደሆን ተመልክቶአል።

ብሪታንያ ሀገሬ ላይ የአሸባሪዎች ጥቃት ሊደርስብኝ ይችላል በሚል ስጋት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ቁጥጥሯን ማጥበቋ ተገለፀ። ከኢራቅ እና ከሶርያ የፅንፈኝነት አስተሳሰብ ይዘው የሚመለሱ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ ተጠርጣሪ ሙሥሊም አክራሪዎች

በያዝነዉ ዓመት የካቲት ወር በምዕራብ አፍሪቃ ጊኒ ከተከሰተ አንስቶ ወደተለያዩ የአካባቢዉ ሃገራት በመዛመት ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ የሚነገርለትን የኤቦላ ተኀዋሲ ለመከላከል የተለያዩ ሃገራት የየራሳቸዉን ጥረት እያደረጉ ነዉ።

ባለፉት አስምስት ወራት ብቻ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዉ ሞቷል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተሰዷል።በስንዴ ምርቱ ከዓለም የታወቀዉ ግዛት፤በነፋሻ አየሩ የሚወደደዉ ያ ግዛት እየጠፋ ነዉ።

ከጎርጎሪዮሳዊዉ 1933ዓ,ም እስከ 1945 ጀርመንን የገዛዉ አምባገነን መሪ አዶልፍ ሂትለር በመሠረተዉ ብሔራዊ ሶሻሊስት የሠራተኛ ፓርቲ በምሕፃሩ NSDAP አማካኝነት ከአካባቢዉ አልፎ ሌሎች ክፍለ ዓለማትንም የመቆጣጠር ህልም ይዞ ተንቀሳቅሷል።

በደቡብ አፍሪቃ ንዑስ ግዛት በሌሴቶ ንጉሳዊ አስተዳደር ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሳይካሄድ አልቀረም የሚል ዜና ከተሰማ በኋላ፣ ሶስት የደቡብ አፍሪቃ ልማት ማኅበረሰብ፣ በምሕፃሩ የ«ሳዴክ» አባል ሀገራት የፖለቲካ የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የተጠቃለሉበት ኮሚቴ ትናንት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ስለሌሶቶ ጊዚያዊ ሁኔታ መከረ።

ባለፉት አስምስት ወራት ብቻ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዉ ሞቷል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተሰዷል።በስንዴ ምርቱ ከዓለም የታወቀዉ ግዛት፤በነፋሻ አየሩ የሚወደደዉ ያ ግዛት እየጠፋ ነዉ።

ኢራቅ ዉስጥ ለሚገኙ የኩርድ ተወላጆች የጦር መሣሪያ እናቅርብ የሚለዉ ሃሳብ ባለፉት ሳምንታት እዚህ ጀርመን ሲነሳ ሁለት የተለያዩና የሚፃረሩ አስተያየቶች ባለፉት ቀናት ተሰምተዋል። በእነዚህ ነጥቦች ላይም ሰሞኑን ፖለቲከኞቹ ሲከራከሩበት ሰንብተዋል።

የ28ንቱ የአዉሮጳ ሃገራት መንግሥታትና ጠቅላይ ሚኒስትሮች፤ ትናንት ብራስል ላይ ልዩ ጉባኤ ካካሄዱ በኋላ ለኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሄርማን ቫን ሮምፑይ እና ለኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃለፊ ካትሪን አሽተን ፤ ተተኪ መረጡ።

የደቡብ አፍሪቃ ግዛት በሆነችዉ ንዑሷ የሌሴቶ ግዛት ንጉሳዊ አስተዳደር ላይ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መፈፀሙ ተዘገበ። መፈንቅለ-መንግሥቱን ተከትሎ የሌሶቶ ጠቅላይ ሚንስትር ለሕይወታቸው በመስጋት ሀገር ለቀዉ መዉጣታቸዉም ተጠቅሷል።

የደቡብ አፍሪቃ ግዛት በሆነችዉ ንዑሷ የሌሴቶ ግዛት ንጉሳዊ አስተዳደር ላይ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መፈፀሙ ተዘገበ። መፈንቅለ-መንግሥቱን ተከትሎ የሌሶቶ ጠቅላይ ሚንስትር ለሕይወታቸው በመስጋት ሀገር ለቀዉ መዉጣታቸዉም ተጠቅሷል። ።

የደቡብ አፍሪቃ ግዛት በሆነችዉ ንዑሷ የሌሴቶ ግዛት ንጉሳዊ አስተዳደር ላይ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መፈፀሙ ተዘገበ። መፈንቅለ-መንግሥቱን ተከትሎ የሌሶቶ ጠቅላይ ሚንስትር ለሕይወታቸው በመስጋት ሀገር ለቀዉ መዉጣታቸዉም ተዘግቦአል።

በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ብቻ ሳይሆን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በየሚካሄደዉ ንግግር ሰሞኑን አንድ ሰነድ ተፈራርመዋል።

አህምት ዳቩቶግሉ ቱርክን የሚያሥተዳድረዉ የፍትሕ እና የልማት ፓርቲ በቱርክኛ አፅሮቱ የ «AKP» ዋና ሊቀመንበር ሆነዉ ተሾሙ። እስከ ዛሬ የቱርክ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዉ ያገለገሉት አህሜት ዳቩቱግሉ በተጨማሪ፤ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት በመሆን በአዲስ የተመረጡትን የሬሴፕ ተይፕ ኤርዶኻንን የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ስልጣንንም ተረክበዋል።

አህምት ዳቩቶግሉ ቱርክን የሚያሥተዳድረዉ የፍትሕ እና የልማት ፓርቲ በቱርክኛ አፅሮቱ የ «AKP» ዋና ሊቀመንበር ሆነዉ ተሾሙ። እስከ ዛሬ የቱርክ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዉ ያገለገሉት አህሜት ዳቩቱግሉ በተጨማሪ፤ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት በመሆን በአዲስ የተመረጡትን የሬሴፕ ተይፕ ኤርዶኻንን የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ስልጣንንም ተረክበዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በመስተዳድር 3 ሰሜናዊ ጫፍ ዋግ ሃምራ አካባቢ በሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች የዝናም እጥረት ባስከተለው ድርቅ ሳቢያ፣ አንዳንድ የአካባቢው አርሶ አደሮች ለረሃብ መጋለጣቸውን ለአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ለዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ገልጸውለታል።

የዓለም አቀፉ የ «ጋዝፕሮም » ኩባንያ ባንክ (GPB Global)በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በአፋር መስተዳድር፤ ነዳጅ ዘይ ት ለመፈለግ ከአንድ ወር ገደማ በፊት ውል መፈራረሙ ተመልክቷል።በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ዘይት አሳሽ ኩባንያዎች፣ እስካሁን

ሚንስትሩ ግብፅ ኮሚቴዉ እንዲስየም ተስማማች ማለት «የግድቡን ግንባታ በይፋ ተቀበለች ማለት አይደለም» በማለት አጠቃላይ ዉዝግቡን ለማስወገድ ሰወስቱ ሀገራት አሁንም ብዙ መራቃቸዉን አልሸሸጉም።

ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ማኅበር አዘጋጅነት በተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዳይመንድስ ሊግ ዛሬ ምሽት በስዊትዘርላንድ የዙሪኽ ከተማ በሚደረጉ ውድድሮች ይፈፀማል።

የሩዋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ለእስር ተዳርገዋል፤ በርካታ ሰዎችም ያሉበት ቦታ አይታወቅም። የደረሱበት እስካሁን ያልታወቁት ዜጎች ከመንግሥት ተቃዋሚ ወገን ብቻ ሳይሆን፤ ከደጋፊዎችም በኩል መሆኑ ተመልክቶአል። በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የአገዛዛዊ መንግሥት ሃገሪቱን ሥጋት ላይ መጣሉ እየተነገረ ነዉ።

መንግሥት በአንዳንድ የግል ጋዜጦች ላይ ክስ ከመሠረተ እና ባለፈው ግንቦትም ዘጠኝ ጋዜጠኞች እና የድረ ገፅ አምደኞች ከታሰሩ ወዲህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

ቡሄን አስታከን ሆያ ሆዬን ይዘን ብቅ ያልነዉ ዘግየት ብለን ቢሆንም፤ እንደ ባህላችን አዲስ ዓመት ጠብቶ መስቀል በዓል እስኪከበር ሆያሆዬን መጨፈራችን የታወቀ ነዉና፤ ዛሬም ጀርመናዉያኑ ሆያ ሆዬ ባስጨፈሩበት የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡሄ ዜማ የዕለቱን ዝግጅት ለመጀመር ወሰን። ሆያሆዬ ያስጨፈሩት ጀርመናዉያኑ የሙዚቃ ባንድ ካሪቡኒ አዲስ ይባላል።

የጀርመን መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ ርዳታ አቅርቦት የሚውል 750,000 ዩሮ ርዳታ ሰጠ። በአፍሪቃ ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ በወቅቱ የአንደኛውን ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ገንዘቡ ለሚቀጥሉት አራት ወራት የሚያስፈልገውን ምግብ ለማቅረቢያ እንደምታውለው የጀርመን ኤምባሲ አስታውቋል።

ግብርና-ቀመስ የሥነ-ሕይወት ዕውቀት፣ በሳይንሳዊ ዘዴዎች የዕጽዋትንና አዝርእትን እንዲሁም የእንስሳትን ተፈጥሯዊ ይዞታም ሆነ መለያ ማሻሻልም ሆነ መለወጥ የሚቻልበት አሠራር ነው። በርከት ያለ የእህል ምርት ለማፈስ፤ ከጥንት ጀማሮ አርሶ አደሮች፣ የዘር እኽል እየመረጡ በመዝራት አያሌ ዘመናት ጠብቀው ለማቆየት መቻላቸው የሚታበል አይደለም።

ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።

የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ግን ያሁኑ ስብሰባ እንደተባለዉ ከወሳኝ መፍትሔ ባይደርስ እንኳ ሰወሥቱ ሐገራት በተለይ ኢትዮጵያና ግብፅ ጦር የያሰብቅ መሠሎ የበረዉ ዉዝግባቸዉን በድርድር ለመፍታት መስማማታቸዉ ራሱ ጥሩ ጅምር ነዉ።

እስራኤል እና ሀማስ ትናንት የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ከትናንት አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንደፀና ይገኛል። ተቀናቃኞቹ ወገኖች በግብፅ ሸምጋይነት ነበር ሰባት ሳምንታት ለሆነው የ2,002 ሰዎች ሕይወት ላጠፋው ውጊያ ገደብ ያልተደረገበት ስምምነት የደረሱት። በስምምነቱ መሠረት፣ በጋዛ ላይ የተጣለው ዕገዳም በከፊል እንደሚነሳ ተገልጾዋል።

የጀርመን መንግሥት የኢራቅ ኩርዶችን ለማስታጠቅ መወሰኑ የሰሞኑ የጀርመናውያን አብይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው ። የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ዛሬ ሳምንት ሐሙስ ድረስ የሚሰጧቸው መግለጫዎች ጀርመን ጦርነት ወደ ተባባሰባት ኢራቅ የጦር መሣሪያዎችን አትልክም የሚል ነበር ።

ምዕራብ አፍሪቃ ዉስጥ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈዉ የኤቦላ ተኀዋሲ ምሥራቅ አፍሪቃ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ዉስጥም መከሰቱን በሳምንቱ መጨረሻ የሀገሩቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል።

የምሥራቃዊ ዩክሬን አማፂያን ከሐገሪቱ መንግሥት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩበት ካለፈዉ ሚያዚያ ወዲሕ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።ጦርነቱ አማፂያኑን ትረዳለች በምትባለዉ ሩሲያና የኪየቭን መንግሥት በሚደግፉት ምዕራባዉያን መካካል ከማዕቀብ-ቅጣትና አፀፋ ቅጣት ያደረሰ ጠብ ቀስቅሷል።

በእስራኤልና ሃማስ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተኩስ አቁም ዉል ድርድር ከተቋረጠ ወዲህ ሁለቱ ወገኖች ተመልሰዉ አንዱ ሌላዉ ላይ ጥቃት መሠንዘር ቀጥለዋል። ዘገባዎች እንደሚሉት እስራኤል ዛሬ ባጠናከረችዉ የጦር አዉሮፕላን ድብደባ ጋዛ ዉስጥ ሁለት ትላልቅ ሕንፃዎችን መትታለች።

በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AMISOM ከሁለት ዓመታት በኋላ ወታደሮቹን ከሶማሊያ ለማዉጣት እቅድ እንዳለዉ ተነገረ። በተመድ የጸጥታዉ ምክር ቤት መርሃግብር መሠረት AMISOM በሶማሊያ የሚኖረዉ የሰላም ማስከበር ኃላፊነት በተጠቀሰዉ ዓመት ያበቃል።

የኤቦላ ወረርሽኝ የመነጋገሪያ ርዕስ በሆነባት ናይጄሪያ ፤ ከበሽታው ሌላ ህዝቧን ያሳሰበው ሌላም ነገር አለ። ይህም በሀገሪቱ ስር የሰደደው አማፂው እስላማዊ ቡድን ቦኮ ሀራም ነው። አማፂያኑ በተቆጣጠሩት ሰሜን ናይጄሪያ እስላማዊ ካሊፋት መመሥረታቸውን በገለፁበት በአሁኑ ወቅት በሌላ በኩል ታግተው የተወሰዱትን ሴት ተማሪዎች ለማስመለስ ትግል ተይዟል።