የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰው ነበር ። ላለፉት 28 ቀናት በተካሄደው ድብደባ ቤታቸው ታስረው የቆዩት ፍልስጤማውያንም ዛሬ መንገዶችንና ገበያዎችን ሞልተው ታይተዋል ።

የኢትዮጵያ መንግስት ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ይፋ አድርጓል። የደሞዝ ጭማሪዉ ከ 2003ዓ,ም በኋላ ሲደረግ የመጀመሪያ መሆኑ ነዉ። የመንግስት ሠራተኛውን ከሃገሪቱ እድገት ተጠቃሚ ለማድረግ የታሰበ ነው የተባለው ይህ ጭማሪ ከኤኮኖሚ አኳያ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?

ከመፅሄቶቹ ዋና አዘጋጆች አንዳንዶቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በህጉ መሠረት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ። ክሱን በተመለከተም ከህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጭ እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአንጎላ አቻው ጋር ትናንት ሉዋንዳ ውስጥ ተጋጥሞ 1 ለባዶ ተሸንፏል። ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ለዓለም የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ሚያሚ ውስጥ ለዋንጫ ይገናኛሉ። በሜዳ ቴኒስ ጥቁር አሜሪካዊቷ ሴሬና ዊሊያምስን በድል ጎዳና የሚያቆማት አልተገኘም። ጀርመናዊቷ ተፎካካሪዋን ከኋላ ተነስታ ድል ነስታለች።

ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደዉ የአፍሪቃ አሜሪካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች የምትገኘዉ የአፍሪቃ አህጉር ላይ ያላትን ፍላጎት እንደሚያሳይ ነዉ የተነገረዉ። የጉባኤዉ አዘጋጆች ዓላማዉ የተጠናከረዉ የቻይና አፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ያስከተለዉ ነዉ የሚለዉን ጥርጣሬ ወደጎን ነዉ ያደረጉት።

ከበርካታ አፍሪቃ ሃገራት ተጓዦችን በአየር መንገዷ የምታስተናግደው ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንዲሁም ወረርሽኙ ጉዳት ካደረሰባቸዉ ካሃገራት ብዙም ሳትርቅ የምትገኘው ጊኒ ቢሳው የኤቦላ ወረርሽኝ ወደየሀገራቸው እንዳይገባ ምን እያደረጉ ይሆን?

ያለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ ጠቃሚ ድርሻ ሊያበረክቱ ይችላሉ ካሏቸው 500 ወጣት አፍሪቃውያን ጋር ተነጋግረዋል። ዛሬ ደግሞ 50 ከሚሆኑ አፍሪቃውያን መሪዎች ጋር ለሶስት ቀናት ሊወያዩ ሌላ ጉባኤ ከፍተዋል።

ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር በሚመሩት የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና በአንፃሩ በሚዋጋው የሪየክ ማቸር ያማፅያን ቡድን መካከል የሰላሙ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ እንደገና ጀመሩ ተሰምቷል። በዚሁ እአአ እስከ 12.08.2014 ዓም ድረስ በሚዘልቀው

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ እድገት እና ብልፅግና ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ያሏቸውን ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት የተውጣጡ 500 ወጣት አፍሪቃውያንን ዘንድሮ ወደ ሀገራቸው ጋብዘው ነበር።

ምዕራብ አፍሪቃ ዉስጥ የኤቦላ ተሕዋሲ የገደላቸዉ ሰዎች ቁጥር ከሰባት መቶ ልቋል። በተጠቀሰዉ አካባቢ በተሕዋሲዉ ክፉኛ የተጎዱት ሃገራት የኤቦላ ወረርሽኝን ለመቋቋም ጠንካራና አዲስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስትና አማፂያን አቋርጠዉት የነበረዉን የሰላም ንግግር የፊታችን ሳምንት እንደሚጀምሩ አደራዳሪዎች አስታዉቀዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ማለትም IGAD አደራዳሪዎች ዛሬ እንደገለጹት በያዝነዉ ሳምንት ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ የሁለቱ ወገኖች የሰላም ንግግር የፊታችን ሰኞ ይጀመራል።

በቀላሉ ሊሰሩ ከሚችሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በገጠሩ አካባቢ ሰዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ነበር ከቀርቀሀ የተሰራች ዋሽንታቸውን ይዘው ሙዚቃ ሲጫወቱ የሚስተዋሉት።

የሐገሪቱን የሥልክና የኢንተርኔት አግልግሎት በብቸኝነት የሚቆጣጠረዉ ኢትዮ-ቴሌኮም በየጊዜዉ ለሚነሱት ወቀሳዎችና ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያት የሚላቸዉን ቴክኒካዊ ሠበቦች መደርደሩ አልቀረም።ችግሩ ግን የመቃለል እዝማሚያ አልታየበትም።

የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለሰባተኛ የስልጣን ዘመን ዳግም ከተመረጡ ዛሬ አንድ ዓመት ደፈኑ ።አምና በአብላጫ ድምጽ ተመርጠው በፕሬዝዳንትነት የቀጠሉት ሙጋቤ አሁንም በዚምባብዌ ነጮች የመሬት ባለቤት እንዳይሆኑ በያዙት አቋም እንደፀኑ ነው።

የእስራኤል የጋዛ ድብደባ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ። እስራኤል ተጨማሪ ተጠባባቂ ጦር ወደ ጋዛ አዝምታለች ። የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎችም ወደ ደቡባዊ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን ቀጥለዋል ። ስደተኞች በተጠለሉበት በጋዛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትምሕርት ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና አሜሪካን አውግዘዋል ።

የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት ረዘም ያለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ የተጠናከረው እና የዛሬ መልኩን የያዘው ግን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነው።

ባለፈዉ ዓመት ከሩሲያ ጋር የ326 ቢሊዮን ዩሮ የንግድ ልዉዉጥ ያደረጉት የአዉሮጳ ሐገራት በማዕቀቡ የወለፊንድ ዉጤት ባንድ ወይም በሌላ መንገድ መነካታቸዉ አይቀርም።ከዩናይትድ ስቴትስና ከቻይና ቀጥሎ ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልዉዉጥ ያላት ጀርመን ደግሞ ከሕብረቱ አባል ሐገራት ሁሉ ቀዳሚዋ ናት።

ለአፍሪቃ ሕብረት፤ ለአፍሪቃ ምጣኔ ሐብት ኮሚሽን ወዘተ እየተባለ በርካታ አፍሪቃዉን የሚመላለሱ፤ የሚስተናገዱባት ኢትዮጵያ እስካሁን የወሰደችዉ የጥንቃቄ እርማጃ ሥለመኖር-አለመኖሩ በይፋ የሰመነዉ የለም። ኬንያ ግን ወደ ሐገሯ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች።

ዩናይትድ ስቴትስ በኧዤን ከተማ በኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ቀናት በተካሄደው እና ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ፌዴሬሽን የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሦስተኛነትን ደረጃ አግኝታ ተጠናቋል።

በአሁኑ ጊዜ ምዕራባውያንን፣ በተለይም ፣ አውሮጳን እያሳሰበ ያለው ፈተናም ውስጥ የጣለው የዩክሬይን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ከሩስያ ጋ የገቡበት እሰጣ ገባ እና የፖለቲካ ፍጥጫ ነው።

በጎርጎሪዮሳዊዉ 1990 እና 1992ዓ,ም በቢሊዮን ይገመት የነበረዉ ለምግብ እጥረት የተጋለጠዉ ሕዝብ አሁን ወደ 842 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ አንድ ነገር ነዉ ቢባልም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉን ወገኖች አሁን የሚያሳስበዉ የተደበቀ ወይም ስዉር ረሃብ መኖሩ መሆኑን ያመለክታሉ።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበጋ ወራት ፍልሚያ ሊጀመር የቀሩት 19 ቀናት ግድም ነው። የዓለም ታላላቅ የእግር ኳስ ቡድኖች የተጨዋቾች ዝውውር ላይ ተጠምደዋል። በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የወጣቶች ፉክክር ኢትዮጵያ ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች።

አብዱረዛቅ ሙደሲር በቦንና ኮለን መካከል በምትገኘው ብሩህል ይኖራል። በጀርመን አስራ ሁለት ዓመታትን ለኖረው አብዱረዛቅ የዘንድሮው ረመዳን እንደወትሮው አይደለም። በአውሮጳ የሚታየው የበጋ ረጅም ቀን እንደ አብዱረዛቅ ረመዳንን ለሚጾሙ ፈታኝ ጊዜ ነው።

ሐማስ የግብፁ የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበር ቅርንጫፍ ወይም ጥብቅ ወዳጅ ነዉ።በግብፅ ሕዝብ የተመረጡትን የሙስሊም ወንድማማቾቹን ፖለቲከኛ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲን ከሥልጣን ያስወገዱት ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ የሙስሊም ወድማማች ጠላት ናቸዉ።ሐማስ ድሮም-ዘንድሮም የእሥራኤል ጠላት ነዉ። አልሲሲና እስራኤል ምን እና ምን ናቸዉ?

ግብጽ አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ ግድቡ ወደ ሃገርዋ በሚገባው የውሃ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳያደርስ ያቀረበችው ጥያቄ እንዴት እንደሚፈታ እያጠያየቀ ነው

ቦኮሐራም የተሰኘው የናይጀሪያ እስልምና አክራሪ ታጣቂ ቡድን ካሜሩን ውስጥ ሰርጎ በመግባት የካሜሩን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ባለቤትን አግቶ መሰወሩን የካሜሩን መንግስት አስታወቀ።

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ተቀናቃኝ ወገኖች ባለፈው ረቡዕ የተፈራረሙት የተኩስ አቁም ስምምነት ዘላቂነት እያጠያየቀ ነው። የፈረንሳይ ራድዮ፣ «ኤር ኤፍ ኢ» ባለፈው ሀሙስ እንደዘገበው፣ ስምምነቱን ተፋላሚዎቹ ወገኖች

በእስራኤል እና በሃማስ ቡድን መካከል ለዛሬ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተከብሮ የዋለ ይመስላል። የነፍስ አድን ሠራተኞችም ይህንን የ12 ሠዓታት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠቅመው ሌሎች 35 አስክሬኖችን ከጋዛ ሰርጥ ፍርስራሾች እንዳወጡ ተገልጿል።

ሁለት በመፅሀፍ ንግድ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ናቸው። አንዱ በአደባባይ ሌላኛዋ ደግሞ በኢንተርኔት መፅሀፎችን ለአንባቢዎቻቸው ያቀርባሉ። ስለሁለቱ ወጣቶች የመፅሀፍ ንግድ እና ከዚህ ጋር ሳይነሳ የማያልፈው የማንበብ ፍላጎት እና ባህል፤ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ምን እንደሚመስል አንድ የከፍተኛ ተቋም መምህርን ጠይቀናል።

የፓርቲዉ መሪዎች ዛሬ ለጋዘጠኞች በሠጡት መግለጫ እንዳሉት ማሻሻዉ በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የክፍለ ሐገር አከላላል እንዲቀር፤ መሬት በግል እንዲያዝና ብሕራዊ ቋንቋ እንዲኖር የሚጠይቁ ሐሳቦች ተካተዉበታል።