አቶ ስዬ አብረሃ በሲያትል ያደረጉት ንግግር
ክቡራትና ክቡራን ጤና ይስጥልኝ በዛሬው ስብሰባ ከአቶ መለስ ሕልፈት በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር አንዳንዳ ሃሳቦችን ለማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ የአቶ መለስ ህልፈተ ህይወት ይፋ ሆኖ አስከሬኑ ቦሌ ደረሰ ሲባል የአዲስ አበባ ሕዝብ በድንጋጤና በሓዘን፤ የክረምቱ ዶፍ እየወረደበት አሰከሬኑን ቤተ መንግስቱ ድረስ አድርሶታል፡፡ አስከሬኑ ከገባ ከአስራ ሁለት ቀን በኋላ ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብም እርሙን አውጥቷል፡፡ በአቶ […]