የብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ የቀብር ሥነ ሥርዐተ ተፈጸመ
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ለመሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ነበር፤ ‹‹ብፁዕነታቸው በመንፈሳዊው ትምህርት የተሟላ ሊቅነት ያላቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔርን በዝማሬ መላእክት፣ ሕዝበ ምእመናንን በትምህርት፣ በስብከተ ወንጌል እና በጸሎተ ቡራኬያቸው ያገለገሉ ያሬዳዊ ቅርስ ነበሩ፡፡›› (ዜና ሕይወታቸው) ‹‹ድጓው፣ ጾመ ድጓው፣ ዝማሬ መዋስዕቱ አልሞተም፤ …