ማትያስ ከተማ (ከስዊድን) Ethiopia Zare (ሐሙስ የካቲት 17 ቀን 2003 ዓ.ም. February 24, 2011)፦ ”ጥሎ ማለፍ” የተሰኘው የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ አዲስ ልብ-ወለድ መጽሐፍ እና በቅርቡ የወጣው ”እውነትም እኛ …” የተሰኘው የግጥም ዲቪዲ የካቲት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ …

የደራሲ አበራ ለማ ታሪካዊ ልብ-ወለድ መጽሐፍ በአዲስ አበባ ተመረቀ Read more »

በጸረ መንግሥት ተቃውሞ እየተናጠች ከምትገኘው ከሊቢያ ብዙ ሺህ የውጭ ሀገር ዜጎች በአውሮፕላን ፥ በመርከብም ይሁን በዕግር ብቻ ባገኙት መንገድ ዕግሬ አውጪኙን ተያይዘውታል። በሊቢያ ያሉ ኢትዮጲያውን ስደተኞች እየተፋፋመ ባለው ህዝባዊ ዓመጽና በየጸጥታ ኃይሉ በያዘው ርምጃ መካከል ተጠምደዋል። የሀገሪቱ መሪ ሞአማር ጋዳፊ …

በሊቢያ ኢትዮጲያውያን ስደተኞች በጸረ ጋዳፊው ዓመጽ ውስጥ ተጠምደው የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን አስታወቁ Read more »

ብርቱ ተቃውሞ የገጠማቸው የሊቢያው ዓብዮታዊ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ ጋዳፊ በስልጣን ለመቆየት የመጨረሻ ተስፋቸውን በአፍሪቃውያን ቅጥረኛ ወታደሮች ላይ ማሳረፋቸውን የመገናኛ ብዙኃን እና የተቃዋሚ ወገኖች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ትሪፖሊ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እንደገለፁት ግን ቤንጋዚ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መገደል፥ መደብደብ መታሠራቸዉንም ሰምተዋል።እዚያዉ ትሪፖሊ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ኢትዮጵያዉያን መገደላቸዉንም ገልፀዋል

ኢቴቪ እና ተዛማጅ ትዝታዎቼ (በእውነተኛ ታሪክ ላይ ያልተመሠረተ) /ክፍል አንድ/ ሴት አያቴ ቲቪ ክፈትልኝ ለማለት “ቲቢውን አብራው” ትለኛለች፡፡ የኢቲቪን አማርኛ ልዋስና “አንዳንድ ጥርሶች” ስለጎደሏት ብቻ አይመስለኝም “ቲቪ”ን “ቲቢ” የምትለው፡፡ ኢቲቪ ሲከፈት ሳሏ ስለሚነሳባትም ጭምር ነው፡፡ ኢቲቪ ሳምባዋን ሳይነካው አልቀረም፡፡ ሴት …

ኢቴቪ እና ተዛማጅ ትዝታዎቼ Read more »

ኳ! ኳ! ኳ! ኳ! ሊል ፤ሊደወል፤ የመጨረሻው ደወል፤ ከወዲያ ከሩቅ ከሚካአኤል ደጅ፤ ከማሪያም ደብር፤ ከጊዮርጊስ ደጃፍ፤ ከተክልዬ ገዳም፣ ከእየሱስ ደጅ፤ ሊያስተጋባ የደውሉ ጥሪ፣ በዱር በገደሉ፤ በየመንደሩ፤ በየገጠሩ፣ በየከተማው፤ በክፍላተ ሀገሩ፤ በተራሮች አናት ተሻግሮ እንደገና፤ ኳ! ኳ! ኳ! ኳ! ብሎ ሊጣራ፤ …

የመጨረሻው ደወል! (አስራደው – ከፈረንሳይ) Read more »

‹‹ነጋዴውና ግብር ሰብሳቢው አይጥና ድመት ሆነዋል››  ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ‹‹የመንግሥትን ለመንግሥት፣ የቄሳርን ደግሞ ለቄሳር ከተከፈለ ችግር አይፈጠርም››አቶ መላኩ ፈንታ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በአሥራት ስዩም

በዳዊት ታዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሥር ይሠሩ የነበሩት ነገር ግን በአዲሱ ኢትዮ ቴሌኮም ያልተካተቱ ሠራተኞች ይቋቋማሉ የተባሉት የሦስት ኩባንያዎች ጥናት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

‹‹እኛን የማገድ ሥልጣን የላቸውም›› ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ በብርቱካን ፈንታ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለድርጅቱ ውስጣዊ ብጥብጥ መንስዔዎች ናቸው ያላቸውን 14 አባላቱን በፍርድ ቤት እንዲታገዱ ማድረጉን ትናንት በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡

– ጅንአድ ከውጭ አገር ዕቃዎችን በገፍ ሊያስገባ ነው በውድነህ ዘነበ የንግድ ሚኒስቴር በገበያ ውስጥ የተፈጠረውን የሸቀጦች አቅርቦት ችግርን መፍታት ያስችላል ያለውን አዲስ ጥናት በሚቀጥለው ሳምንት ያጠናቅቃል፡፡

  በታምሩ ጽጌ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ፓርቲያቸው ተመልሰው የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ለማከናወን አሁን ብቃት እንደሌላቸው ለፓርቲው መግለጻቸውን፣ በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው የተኩትና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በታምሩ ጽጌ ለም ሆቴል አካባቢና ከቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል አለፍ ብሎ ባሉ የኖክ ነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የፈነዱ ፈንጂዎችን ማጥመዳቸው የተረጋገጠባቸውና ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በሞት፣ በዕድሜ ልክና በዓመታት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው አምስት ግለሰቦች ላይ ቅጣቱ እንዲፀና የፌዴራል …

በነዳጅ ማደያ ላይ ፈንጂ በመጣላቸው በሞት የተቀጡ ግለሰቦች ውሳኔ ፀና Read more »

በውድነህ ዘነበ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት በራሳቸው አነሳሽነት መርካቶ ላይ የተሰበሰቡ 800 የሚጠጉ መካከለኛ ነጋዴዎች መንግሥት ‹‹የአገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ሥርዓት ለማስያዝ›› በሚል እየወሰደ ያለው አዲሱ ዕርምጃ ክፉኛ ችግር ውስጥ እየተከተታቸው መሆኑን ገለጹ፡፡

በሊቢያ የህዝብ አመፅ ይቃጣል ተብሎ ሳይታሰብ ፤ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ፣ተጀምሮ እንደቀጠለ ነው። ይሁንና በግብፅ የታየውን ቁጥብነት ያላንጸባረቁት የአገሪቱ የጦር አኤሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች፣ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝባቸው ላይ መተኮሳቸው ከተዘገበ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ፤

በሊቢያ ሰልፈኞች ላይ መንግስት የወሰደው እርምጃ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሏል። የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል እያለ ነው። ቱርክ ለሊቢያ ባለስልጣናት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰዳለች።

ሰሜን አፍሪቃንና የአረብ አገሮችን በየተራ በማዳረስ ላይ ያለው ኅዝባዊ ቁጣ፤ ከአራት አስርታት በላይ ያችን አገር በጠንካራ መዳፍ ተጭነው የገዙትን ፕሬዝዳንት ጋዳፊን ወንበር መነቅነቅ ይዟል። የጦር ኃይላቸውና ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ለተቃውሞ በወጣው ሰልፈኛ ላይ እየተኮሱ መሆናቸው የተዘገበባት ሊቢያ መፍረክረክ የያዘች ትመስላለች። …

የሊቢያው ኅዝባዊ አመፅ ፈጣንና ያልተጠበቁ ውጤቶቹ። Read more »

ቤን አሊን፥ ከቱኒዝ፥ ሙባረክን ከካይሮ አሽቀንጥሮ የጣለዉ አዲሱ ሕዝባዊ አመፅ የአረቡን አለም እየናጠ በአዲስ ጎዳና እየዘወረዉም ነዉ። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽና የጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌሯ ዲሞክራሲያዊት ኢራቅም ከአዲሱ ሕዝባዊ ነዉጥ አላመለጠችም

“የአሁኑ የኢትዮጵያ መሪዎችና መልቲነት” በሚለው ጽሁፍ በአጠቃላይ መልቲዎች ምን ዐይነት ፀባይ እንደሚያራምዱ ለማሳያት ተመክሯል። በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በፖለቲካ አመራር ላይ ያሉ መልቲዎች ምን አይነት ጸባይ አንደሚያሳዩና እነሱን እንዴት መዋጋት እንደሚቻል ለማሳየት እንሞክራለን። ከዚህ በፊት ለማሳየት እንደተሞከረው መልቲዎች እጅግ ቀዝቃዛ ስሜት …

መልቲዎችን እንዴት ማቸነፍ ይቻላል? በደጉ ማረው Read more »

በቱኒዚያ የተጀመረው የዓረብ አገሮች አብዮት ፕሬዚዳንት አል አቢዲን ቤን አሊን ለ23 ዓመት ከተቆናጠጡበት የሥልጣን ወንበራቸው አስነስቷቸዋል፡፡ አብዮቱ በግብፅ ቀጥሎ በታህሪር አደባባይ ለ18 ቀናት በተካሄደው ተቃውሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ለ30 ዓመታት ከተደላደሉበት የሥልጣን ወንበር አሰናብቷቸዋል፡፡ ይህ የዓረብ አገሮች አብዮት እንደ ወረርሽኝ …

መሪዎች ከዓረብ አገሮች አብዮት ምን ይማራሉ? Read more »

በዓረብ አገሮች የሠራተኞችን ጉዳይ የሚከታተል ተቋም ባለመኖሩ ችግሩ ተባብሷል በታምሩ ጽጌ ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ ዱባይና የመን በሕገወጥ መንገድ የሚላኩ ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ፣ እንግልት፣ አካል መጉደልና ሞት ለመታደግ መንግሥት ከጎናቸው እንዲቆምና

– የኖርዌይ ልዕልትና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመጣሉ በዳዊት ታዬ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ፍሰት እያደገና አሁን ባለው ደረጃ ከአቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ፣ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ብቻ የሚመለከት መሥሪያ ቤት እንደሚቋቋም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

በኃያል ዓለማየሁ በኢትዮጵያ ከተመሠረተ 50 ዓመታት ገደማ ያስቆጠረውን ሬስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከወራት ድርድር በኋላ ሙሉ በሙሉ እንደገዛውና ከዚህ ወር ጀምሮም እንደተረከበው ታወቀ፡፡

በአስራት ሥዩም ባለፈው ሐምሌ ወር በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤትና በቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መካከል ስምምነት የተደረሰበት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡

በምስራቅ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዩጋንዳ ትናንት ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ሰባት የተቃዋሚ ወገን ዕጩዎች ዩጋንዳን ላለፉት ሀያ አምስት ዓመት በመሩት የስድሳ ስድስት ዓመቱ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አንጻር ተወዳድረዋል።