የብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ የቀብር ሥነ ሥርዐተ ተፈጸመ
- ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ለመሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ነበር፤
- ‹‹ብፁዕነታቸው በመንፈሳዊው ትምህርት የተሟላ ሊቅነት ያላቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔርን በዝማሬ መላእክት፣ ሕዝበ ምእመናንን በትምህርት፣ በስብከተ ወንጌል እና በጸሎተ ቡራኬያቸው ያገለገሉ ያሬዳዊ ቅርስ ነበሩ፡፡›› (ዜና ሕይወታቸው)
- ‹‹ድጓው፣ ጾመ ድጓው፣ ዝማሬ መዋስዕቱ አልሞተም፤ እዚያው ከዋናው ከቅዱስ ያሬድ ጋራ በሰማይ ያመሰግኑበታል፤ የካቲት 24 ቀን የተክለ ሃይማኖት በዓል ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም እንዲቀድሱ ተራ ደርሷቸው ነበር፤ ነገር ግን በወዲያኛው ዓለም ከእነ ቅዱስ ያሬድ እና ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋራ እንዲቀድሱ ተጠሩ፡፡›› (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ)
(ደጀ ሰላም፤ ማርች 5/2011)፦ ከትናንት በስቲያ በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በ76 ዓመታቸው ያረፉት የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ሥርዐተ ቀብር ዛሬ፣ የካቲት 26 ቀን 2003 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡ የብፁዕነታቸው አስከሬን ትናንት ዓርብ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት ወደ ካቴድራሉ ተወስዶ ጸሎተ ፍትሐት ሲደረስለት ያደረ ሲሆን በመላው አህጉረ ስብከትም ጸሎተ ፍትሐቱ ተደርጓል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
