በኢትዮጵያ የሊቢያ ኤምባሲ የጋዳፊን ዕርምጃ አወገዘ

(በኃያል አለማየሁ)

በኢትዮጵያ የሚገኘው የሊቢያ ኤምባሲ በፕሬዚዳንት ሙአመር ጋዳፊ የሚመራው የሊቢያ መንግሥት፣ በሰላማዊ ተቃዋሚ ሠልፈኞች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን የኃይል ዕርምጃና ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን ማሰማራቱን አጥብቆ እንደሚያወግዝ አስታወቀ፡፡