ጄኔራል ፃድቃን፣ ኢህአዴግና የሰሜን አፍሪካ አብዮት

እስክንድር ነጋ (ከአዲስ አበባ)

ጥድፊያ፣ ጥድፊያ፣ ጥድፊያ ሰዓቱ እየደረሰ ነው። ገና መጣጥፉ አላለቀም፤ ይቀረዋል። መጻፍ…ማረም፣…መሰረዝ… እንደገና መጻፍ፤ ማስተካከል…. ምን ማለቂያ አለው… ሁለት ሰአታት ይቀራሉ…ለመጨረሻዋ ቡና ጊዜ አለ። እፎይ!… የአርብ የግማሽ ቀን ውሎ ይህንን ይመስላል… ለእኔ ለጸሀፊው። በዋሽንግተን ካለው ግዙፉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር የአርብ ቀጠሮ ከያዝኩኝ ይሄው ሰነባብቻለሁ። ይህች ቀጠሮ እንዳትፋለስ ነው ጥድፊያው። ሌላው ዲያስፖራ እንኳን በሚመቸው ሰአት ነው የሚያገኘኝ።