ስጋ ቆራጭ እንደ ጆሮ ቆራጭ የሚያስፈራበት ጊዜ መጣ!?

አቤ ቶክቻው (ከአዲስ አበባ)

 

ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ?

 

በዛሬው ወሬያችን ርእስ ያደረግነውን ጉዳይ ከማውጋታችን በፊት እስቲ ሌሎቹን ጉዳዮች ትንሽ ትንሽ እናውጋቸው! እንዴት ነው ወዳጄ ኮንዶሚኒየም ቤት እጣ ደረሰዎት እንዴ? እስቲ አዎ! ይበሉና ያስደስቱኝ። እውነቱን ለመናገር የዘንድሮው ኮንዶሚኒየም እጣ ደረሰኝ ብሎ ሲያወራ የሰማሁት አንድም ሰው እኮ የለም። ወይስ የኔ ወዳጆች በሙሉ ምዝገባው በነበረበት 97 አመተ ምህረት በስራ ተጠምደው የነበሩ ናቸው? የሆነ ሆኖ እጣው ከደረሰዎ እንኳን ደስ አለዎ!