የወያኔ የገንዘብ ድርጎ ማዕበሉን አያግደውም። በሎሚ ተራ ተራ

ኢትዮጵያ አንድነሽ እማማ ክቡር ነሽ
ወያኔ የት አውቆሽ በሙል አፉ ይጥራሽ።

ስሞኑን ሁላችንም እንደምንመለከተው፤ ጋዳፊ በአለም የመገናኝ ስርጭቶች መደረክ ምን ያኽል ቅሌታምና አርቆ ማየት እንኳን የማይችል እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቅል በሚል ሕዝቡን ሲጨረስና ሲያሳድድ ታይቷል። ጭፍን አምባገነን መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጨካኝና ይሉኝታ የሌለው አሁንም ሆኖ የተገኝ ወራዳ መሆኑን ሚዲያዎች እየዘከሩት ነው።

እኔን በጅጉ ያስደነቀኝና ያስገርመኝ ግን ያንባገነኖች ተመሳሳይ ባህሪ ነው። አይታችሁ እንደሆን ለአርባ አምት ዞር ብሎ ያላየውን ህዝብ ዛሬ በቃኝ ብሎ ሲነሳ ምን ጎደላችሁ? ……. ‘ የጠየቃችሁት ይሟላል፤ …. ብቻ አታምጹ…. ወላጆች ልጆቻችሁን ምከሩ፤ ወደቤታችሁ ግቡ በሉ ሲል ተደምጦል። የኛው ደፋር ቀንደኝው መለስ ዜናዊም እንዲሁ እያደርገ እንደሆነ ስመለከት ከመገረምም አልፌ ተገርመምኩ እላችኋላሁ።

ሌላው አስደናቂው ትዕይንት አምባገነኑ ጋዳፊ በትሪፖሌ ተመሽገው ፤ ቢጤዎቻቸውን ስብስበው ተመልከቱ ….. ምን እየተደርገ እንዳለ… እኔ ያላደርግኩት ምን አለ ? ይህን የሚያስተባብሩብኝ “አልካይዳ” ((ቢላድን) ነው። እያሉ ጠርቤዛ እየደበድቡ ሲፎክሩ ከኛው ጉድ መለስ ዜናዊ ጋር የሚለያችው ምንድነው ትላላችሁ ? እሳችው ተመሽገው መለስ ግን በፓርላማ መሆኑ እንጄ ሁለቱም አንድ ናችው።

አንባ ገነኑ መለስ ዜናዊም እንደ ጋዳፊ ወጣቱን እንዲያምጽ የሚቀስቅሱት ቅንጅቶች ናቸው። ግንቦት 7 ነው። እከሌ ነው። እከሊት ነች፤ እያሉ ሲያጎሩ በፓርላማ ሲደመጡ……. አዪ ጉድ ሲያልቅ አያምር አሉ…… ከማለት ሌላ ምን ይባላል ወገኖች ?።

ወያኔ አገርን በወረራ ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሕዝብን ነፃነት በመግፈፍ፤ በተወለደበትና እትብቱ በተቀበረበት ምደር በአፈናና በምዝበራ ስርቶ እንዳይኖር፤ በልቶ እንዳያድር የግፍ ግፍ እያደረስበት ነው። በደሉንና ግፉን እጥፍ ድርብ በማድረግ ሕዝብን ፍዳውን ማስቆጠር ከጀመረ እንሆ ዛሬ 20 አመቱን ሊደፍን ጥቂት ቀናቷች ጎደሉት።

ሆኖም ይህ ግፍ ያስመረረው ታጋሹና አስተዋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥልቀትና በማስተዋል ምዝበራውንና ብዝበዛውን ተገንዝቦ በጎረቤት አገሮች እየተቀጣጠለ ያለውን የነፃነት ችቦ ለማንቦግቦግ በመጨረሻውና በ 11ኛው ደቂቃ ላይ ይገኛል። ታዲያ ይህ የነፃነት ችቦ እንዲቀጣጠል በነቂስ ከያለበት እየተጠራራና እየተስባስበ ባዲስ ትኩስ ሃይልና ኢትዮጵያዊ መንፈስ ችቦውን ሊለኩስ በተዘጋጀው ወጣት ሃይል ላይ የተደገስው ድግስ ምን ይሆን ?

ይሉኝታና ሃፍረት የሌለው ወያኔ ለሃያ አመት ያለምንም እርህራሄ በውርደትና በስቃይ ሲመዝብረው የቆየውን የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን በተለይ ወጣቱን ክፍል ነው። በወጣትነት ዘመናችው፤ ጊዜ ሳያልፍ ብዙ ሊያደረግ ሲገባው ዛሬ ችቦውን ሊለኩሱ በተነሱበት በመጨርሻው ስዓት በተልካሻ የገንዘብ ድርጎ ለመደለል የድግስ ድንኳኑን እየደኮነ ነው።

በመሃበር፤ በክልል ተደራጁ። ይሄን ያኽል ሚሊዮን ብር እንስጣችኋላን። የስራ እድል እንፈጥርላችኋላን። በማለት የድለላ ዘመቻውን በስፋት እያስፋፉ መሆኑን የስሙት አስተዋይ የ ኢትዮጵያ ወጣቶች በመገረምም በመደነቅም ይሁን እስቲ .. ገንዝቡም ይገባናል። ችቦውንም መለኮሳችን አይቀሬ ነው። እያሉ ግንዝቡን በግራ እጅ ችቦውን በቀኝ እጅ በማለት ወያኔን እየተሳለቁበት እንደሆን ሥስማ ሳቅም ደስታም ፈነቀለኝ።

የሚደንቀው የወያኔ ቅሌት ግን ያው ከስሞኑ የጋዳፊ አይነት ትእይንት ምንም የማይለይ መሆኑ ነው። ያላወቅውና ያልተርዳው ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በምንም በማንም ነፃነቱን አሳልፎ አለመስጠቱን ነው። ወያኔ የህዝቡን የልብ ትረታም የማይረዳ ደካማ፤ ከመሆኑም በላይ ያነጣጠረውን የገንዘብ ድርጎ፤ አስተዋዩና የዘመኑ ጠበብት ወጣት ሃይል አይረዳውም ተብሎ ይሆን ላይና ታች መራወጡ?።

አይ ሃፈረተቢሱ ወያኔ ሃያ አመት ሊሞላው ጥቂት ቀን እስኪቀረው ድረስ ዞር ብሎ ያላየውን ሕዝብ ዛሬ አሳቢ ሆኖ ይቅረብ ? ማፈሪያ። በጭካኔና በምን ቸገረኝነት ሲያስረውና ሲገለው ሲከፋፍለውና ሲያዋርደው የት ነበረ ? አልፎ ተርፎም በምሬት አገሩን እየለቀቀ እንዲሰደድ ሲፈርደበት ምንም ሳይታየው ዛሬ ችቦው ሊለኮስ ሲል ለገንዝብ ድርጎ መነሳሳት፤…… መጥኔ…. ወያኔዎች….. የቅሌት ቅሌት…. አያሰኝም ትላላችሁ።

የነፃነት ችቦውን ለማቀጣጠል ኢትዮጵያዊያን ምን ማድረግ አለባችው ትላላችሁ ? የኔን እምነት 7 ነጥቦች እንሆ ።

ከሁሉም በፊት ሃይልም ጉልበትም ጥበብም ማስተዋልም ሁሉ በጁ ላለው አምላክ አገራችንን በጽናት በጸሎት እንደየ እምነታችን ለአምላካችን አደራ መስጠት።

የግል ወየም የድርጅት አጀንዳችንን በግላችንና በልባችን ይዘን አገራችንን ኢትዮጵያን በማስቀደም ለነፃነት ትግላችን የመጨረሻውን ችቦ ለማቀጣጠል በጸና ኢትዮጵያዊ አንድነት እጅ ለእጅ መያያዝ።

በውስጥም በውጪም የተጀመረው የመትባበርና የአንድነት መንፈስ ከጠነከረው በላይ እንዲጎለብት ሌት ከቀን ጠንክሮ መስራት።

በየጎራው የሚደረገው ያመለካከት ልዩነትና የአስተሳስብ ወይም በውይይት መድረክ የሚደርጉ መወቃቀሶች እትዮጵያን ከማስቀደም የመነጨ እንጂ በምንም እና በማንም አስተሳስብና አመለካከት ወደ ጥላቻ እንዳይለወጥ ልበስፊ በመሆን መስራትና ወያኔንና አጋሮቹን ግን በመለየት ጠንክሮ መታገል።

ልዩነታችንን በማቻቻል የነፃነቱ ችቦ እንዲቀጣጠል ወያኔ የሚያሴረውን ሴራ በንቃት በመጠበቅ በህብረት ማክሽፍ። በተለይም ወጣቱ ትውልድ ላይ የተነጣጠረው የገንዘብ ድርጎ ፋይዳቢስ መሆኑን በጽናት ማስረዳትና ማስተማር።

የጀመርነው የነፃነት ትግል እልህ አስጨራሽ ሊሆን እንደሚችል በማመን ያለምንም ቸልተኝነት አንዱ አንዱን በማበረታታት ነጻነታችንን እስክንቀዳጅ ድረስ በጽናት መታገል።

ለማይቀረው ተግባራዊ የነጻነት ትግል ጉልበትንም፤ እውቀትንም፤ ገንዘብንም መስዋት በማድረግ ነፃነትን እስክንቀዳጅ በጽናት መታገልና ድልን እንደምንቀዳጅም ማመን ዋናዎቹ ናችው እላለሁ።

ይኽንን በማድረግ የ ኢትዮጵያ የነጻነት ጮራ ባጭር ጊዜ እንዲፈነጥቅ ማድረግ እንችላለን።

በተባበረ ኢትዮጵያው አንድነትና መንፈስ የተቀጣጠለው የነፃነት ችቦ ነፃነትን ሳይቀዳጅ አይጠፋም !

በቸር ይግጠመን
ሎሚ ተራተራ March-2-11