የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ለቀየሰዉ የትምሕርት መርሕ ማስፈፀሚያ የተዘጋጁ የማስመተማሪያ መፅሐፍት በወቅቱ ለየትምሕርት ቤቶቹ አለመድረስ የመማር ማስተማሩን ሒደት እንዳጎለዉ አንዳድ የደቡብ ኢትዮጵያ ተማሪዎችና አስተማሪዎች አስታወቁ።

ሊቢያ ያሉ ኢትዮጲያውያን ስደተኞች በብጥብጥ እየታመሰች ካለችው ከዚያች ሀገር በምን ቀዳዳ እንደምንወጣ ጨንቆናል እያሉ ናቸው። መዲናዋ ትሪፖሊ ውስጥ ያሉበት አካባቢ ህብረ ብሔራቱ የአየር ጥቃት ዒላማ ከሆኑት ስፍራዎች ቅርብ ቦታ መሆኑን የተናገረው የሃያ ዘጠኝ ዓመቱ ወጣት ሁሴን ኡስማን የመንፈቅ ልጁንና ባለቤቱን …

ትሪፖሊ ያሉ ኢትዮጵያውያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ናቸው Read more »

በየማነ ናግሽ | ሪፖርተር በመጪው ዓመት መጀመሪያ ወራት የኤርትራ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድና ከአገር ውጭ ብሔራዊ ሸንጐ ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ብሔራዊ ኮሚሽን፣ የኤርትራ ነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በመጪው ግንቦት ዓለም አቀፍ ሠልፍ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ ከተመሠረተ ስድስት ወር የሆነውና በመጪው ጥቅምት ወር …

የኤርትራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የተቃውሞ ሠልፍ ጠሩ Read more »

በታምሩ ጽጌ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ከ13 ዓመታት በላይ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ፣ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ዲፓርትመንት ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አሥር ከፍተኛ ኃላፊዎች መጋቢት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ከትናንት በስቲያ በዋስ ተለቀቁ፡፡

በታምሩ ጽጌ የሸራተን አዲስ ሆቴል ባንኩዌት በተባለው የሥራ ዘርፍ በምግብና መጠጥ አቅራቢነት ላይ ይሠሩ ለነበሩ 19 ሠራተኞች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሆቴሉ እንዲያገኙ ፍርድ የሰጠባቸውን 11 ውሳኔዎች በመቃወም፣ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ ሊከፈላቸው የነበረውን የጥቅማ ጥቅም …

ሸራተን አዲስ ሆቴል የ19 ሠራተኞቹን የጥቅማ ጥቅም ክፍያ አቋረጠ Read more »

በኃያል ዓለማየሁ አዳማ በሚገኘው በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ቅርንጫፍ መሥርያ ቤት ያገለግሉ የነበሩት አቶ ጄሉ ሁሌ የተባሉ የጥበቃ ሠራተኛ፣ ከትናንት በስቲያ ከንጋቱ 12፡30 ጀምሮ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የአዳማ ከተማን በመሣርያ ተኩስ ካሸበሩ በኋላ ሁለት ሰዎችን ገድለው እሳቸውም መገደላቸው ተገለጸ፡፡

‹‹ሒደቱ በዚሁ ከቀጠለ ሽምግልናውን ለማቆም ወስኛለሁ››  የአስታራቂ ኮሚቴው ሊቀመንበር በኃይሌ ሙሉ በእነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲና በእነፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ቡድን መካከል በአስታራቂ ሽማግሌዎች አማካኝነት ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋጫ ከማግኘት ይልቅ፣ ወደኋላ እየተጎተተ መሆኑን የአስታራቂ ኮሚቴው …

የአንድነት ፓርቲ የድርድር ሒደት ወደኋላ እየተጎተተ ነው Read more »

በብርቱካን ፈንታ ለሦስተኛ ጊዜ በአፍሪካ አስተዳደር ላይ ለሚደረገው ጥናት “ምርጫና የብዙህነት አስተዳደር በኢትዮጵያ” በሚል የኢትዮጵያን ክፍል የሚያጠኑ ታዋቂ ግለሰቦችና ምሁራኖች ታወቁ፡፡

በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ሚስተር ዲርክ ኒበል የተመራ አንድ የጀርመን መንግሥት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርጎ መመለሱ ይታወሳል፡፡ ያንን ጉብኝት ተከትሎ የሃገሪቱ ፓርላማ የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በርሊን ላይ ገለፃዎችን አዳምጦ ነበር፡፡ ከገለፃዎቹ በኋላም ተከታይ …

የኢትዮ-ጀርመን ግንኙነትና የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ Read more »

የመለስ አገዛዝ ኤርትራን አስመልክቶ አዲስ የውጭ ፖሊሲ ማውጣቷን ገለፀ። የአሥመራን መንግሥት ከሥልጣን ለማስወገድ “አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት የኤርትራን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ መንግሥታቸው ዲፕሎማሲያዊም ሆነ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይወስዳል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ …

መለስ የአሥመራን መንግሥት ለማስወገድ “አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለ Read more »

በወንዶቹ ማርቆስ ገነቴ በማራቶን ሲሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም፥ የገባበት ሁለት ሰዓት ስድስት ደቂቃ ሰላሳ አምስት ሴኰንድ፥ በካሊፎርኒያ ታሪክ የመጀመሪያው፥ በዓለም ሁለተኛው ፈጣን ጊዜ ሆኖ ተመዝግቦለታል።   ከሁሉም በላይ ብዙዎችን ያስደነቀው፥ ትላንት በውድድሩ ወቅት ዝናብ ባይጥል ኖሮ፥ የማርቆስ ጊዜ ከዚህም የበለጠ ፈጣን …

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል በአሜሪካ Read more »

“ዋጋ የተጨመረው የቀዝቃዛ ውኃ ታሪፍ ስለጨመረ ነው”   ድርጅቱ“ይህን ያህል ጭማሪ መደረጉ ተገቢ አይደለም”  ተገልጋዮች በብርቱካን ፈንታ የአዲስ አበባ የፍል ውኃዎች ድርጅት በደንበኞቹ ላይ ከየካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የ35 በመቶ ጭማሪ አደረገ፡፡

በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር ለመለስ ዜናዊ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዘመናዊ ቤት በአራት ኪሎ የምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ እየተገነባላቸው ነው፡፡ አዲስ የሚገነባው ቤት እርሳቸውን የሚጐበኙ እንግዶች የሚያርፉባቸውን የእንግዳ መቀበያ ቤቶችን ያካትታል፡፡ ኢሕአዴግ የደርግን አገዛዝ በ1983 ዓ.ም ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ …

መለስ ዜናዊ የ80 ሚልዮን ብር ቤት እየተገነባለት ነው Read more »

– በ668 ሺሕ ብር የተሰጠ ኮንትራትም በ115 ሺሕ ብር እንዲሠራ ተደረገ በታምሩ ጽጌ ከተቆረቆረች 400ኛ ዓመቷን ባለፈው ዓመት በጥር ወር 2002 ዓ.ም. ያከበረችውና በሰሜን ጐንደር ዞን ውስጥ የምትገኘው የዳባት ወረዳ ከተማ የውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የቴክኒክ ቁጥጥር ባለሙያና አንድ …

ሰሜን ጐንደር ውስጥ በ774 ሺሕ ብር ሙስና የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ታሠሩ Read more »

በውድነህ ዘነበ የጥጥ እርሻ ባለቤቶች በዚህ ሳምንት ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኒያላ ኢንሹራንስ ጋር በሚያካሂዱት ስብሳባ ምናልባት በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በኮንትራት ስምምነት የሚቀርብ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር ሊያገኙ እንደሚችሉ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

– ‹‹አንድ ተራ አስከባሪ በቀን ከ3,000 እስከ 5,000 ብር ያገኛል›› የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በታምሩ ጽጌ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የሚገኙትን 8,500 ታክሲዎችን በአምስት ቀጣናዎች ለማሠማራት ያጠናው ጥናት የተሟላና ችግርን የሚቀርፍ ሳይሆን፣ ችግሩን ይበልጥ ሊያባብስ እንደሚችል …

የታክሲዎች የቀጣና ስምሪት ጥናት ተተቸ Read more »

የአረብ ሊግ የሊቢያ የዓየር ክልል ከበረራ ነፃ እንዲሆን በጠየቀ በሳምንቱ አሁን የዓየር ጥቃቱን እየነቀፈ ነው። ዛሬ የአረብ ሊግ ዋና  ጸሐፊ አምር ሙሳ  ሲናገሩ የተባበሩት መንግሥታቱ ለበረራ ክልክል ቀጣና ገቢራዊነት አረብ ሊግ ከፈለገው አልፎ የሄደ ነው ብለዋል። አምር ሙሳ በካይሮ ለጋዜጠኞች …

የአረብ ሊግ በሊቢያ ከበረራ ክልክል ቀጣናን ለማስከበር የተወሰደውን ርምጃ አፈጻጸም ነቀፈ Read more »

ከሳምንት በፊት በጂማ ዞን አሰንዳቦ ከተማ ተጀምሮ ወደ ጭሮ አፈታ ኦሞ ናዳ እንዲሁም ወደ ሌሎች ወረዳዎች የተዛመተዉ የቤተ ክርስቲያኖችና የግል ቤቶች መቃጠልና የሰዎች መፈናቀል ነዉ፤ ለዛሬዉ ጥያቄዎ መልስ ርእስ መነሻ የሆነን። ሆኖም ስለዚህ ክስተት ስንዘግብ ካሁን በፊት በጉራጌ ዞን ዘጠኝ …

በቅርቡ ለደረሱት አብያተ ክርስትያናት ቃጠሎ ከጊዜያዊው መነሻዎች ባሻገር ለዓመታት የቆዩ የተሳሳቱ ምክኒያቶች አሉ ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች አመለከቱ Read more »

«የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ይዞታና አንድምታው፤» በእሰጥ አገባ የተጀመረው የሁለት ወገን ክርክር ቀጥሏል። የክርክሩ ተሳታፊዎች፥ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ደግሞ ከዚህ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው። አቶ ተስፋዬ ”የንግር ነፃነት“ ዛሬ በኢትዮጵያ «ተረጋግጧል፤» ሲሉ፤ አቶ ግዛው በበኩላቸው፤ ከዓመታት …

የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ የዛሬ ይዞታውና አካሄዱ፤ ከየት ወደ የት? Read more »

«ሃኪምዎን ይጠይቁ፤» በምሽቱ ቅንብሩ፥ ጆሮ ላይ «ጭው፤» የሚልና ሌሎች መሰል አዋኪ ጩኸቶችን ምንነትና መነሻ አስመልክቶ አድማጮች ላደረሱን ጥያቄዎች የባለ ሞያ ምላሽ ይዞ ቀርቧል። ለሞያዊ ማብራሪያው በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በConnecticut ክፍለ ግዛት በሚገኘው የConnecticut ዩኒቨርሲቲ ረዳት የህክምና ፕሮፌሰርና የአንገት በላይ ህክምና …

ምንም ዓይነት ውጫዊ ድምፅ በሌለበት የሚሰማ ጆሮ ላይ ጭው የሚል ድምፅ ከምን ይመጣል? Read more »

ዩናይትድ ስቴትስ እና ሸሪኮችዋ በሊቢያ በመዲና ትሪፖሊ አጠገብ ባሉ  የሀገሪቱ መንግሥት ዒላሚዎች ላይ የጀመሩትን  ያየር ጥቃት ቀጥለዋል። ርምጃው እየተወሰደ ያለው የሊቢያ የአየር ክልል ከበረራ ክልክል እንዲሆን እና ህዝቡን ከመንግሥቱ ጥቃት ለመከላከል በተባበሩት መንግሥታት በተውሳኔ በተፈቀደው መሰረት ሲሆን የምዕራባውያን የጦር አውሮፕላኖች …

ዩናይትድ ስቴትስ እና ሸሪኮችዋ በሊቢያ ያየር ጥቃቱን ቀጥለዋል፥ ጋዳፊ በምላሹ በረጅም ጦርነት እጠምዳችኋለሁ ሲሉ ዝተዋል። Read more »

የተባበሩት መንግስታት በሊቢያ ላይ የበረራ ዕገዳ እንዲከበር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የተከፋፈል አቓም መያዛቸው ታውቓል። በሊቢያው መሪ ሙዓማር ጋዳፊ ላይ ጥቃት አንዲጀመር ፈረንሳይ በዋና አቀንቃኝነት ተንቀሳቅሳለች። ጀርመን ግን በሊቢያ ላይ የተጀመረውን ርምጃ ተቃውማለች።

የምዕራባዉያን መንግስታት እና የአረብ ሊጋዉ ትናንት ፓሪስ ላይ የሞአመር ጋዳፊን ሃይል ለማምከን ከተስማ በኳላ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተለይ የፈረንሳይ የእንግሊዝ እና የዪናይትስ ስቴትስ የጦር ሃይሎች የኮነሪል ጋዳፊን ቁልፍ የጦር ሰፈሮች እየደበደቡ ነዉ።

በእረፍት ላይ የሰነበቱት ተማሪዎች ወደግቢ እየተመለሱ ነው   ጠንካራ ፖለቲካዊ ጽሁፎችን በመጻፍና ድፍረት የተሞላባቸውን ሀሳቦች በማስተጋባት የሚታወቀው፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፡ ከእረፍት እየተመለሱ ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደ ግብጽና ቱኒዚያ አጋሮቻቸው የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታ ሊቀይር የሚችል አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ። …

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ Read more »

የ1967ቱን አብዮትና የተከተሉትን ሁኔታዎች ጨምሮ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ግዙፍ ታሪክ የሚመለከት ታሪክ ቀመስ ልብወለድ ነው፤ ምርኮኛ። በዚህ ከመፅሃፉ ጋር በምንተዋወቅበት የመጀመሪያ ክፍል ዝግጅት፥ በመፅሃፉ አብይት ጭብጦች፥ አፃፃፍና አተራረክ ዙሪያ እንነጋገራለን። ለመፅሃፉ መነሻ ወደ ሆነው ጊዜና ቦታ ለአፍታም ቢሆን በምናብ እንጓዛለን። …

ቆይታ ከ«ምርኮኛ» ልቦለድ መፅሃፍ ደራሲ ቆንጅት ብርሃን ጋር Read more »

በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ኮት ዲቯር ባለፈው ህዳር ወር ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊው ምርጫ በኋላ በአሸናፊው እና በተሸናፊው ፕሬዚደንቶች አላሳ ዋታራ እና ሎውሮ ባግቦ ደጋፊዎች መካከል የቀጠለው ግጭት አሁን ሀገሪቱን ወደርስበርሱ ጦርነት እያመራት ይገኛል።

መንግሥት በግጭቱ “የአልሸባብ እጅ አለበት” ይላል:: ነዋሪዎች አልተቀበሉትም (ሰንደቅ፣ በጋዜጣው ሪፖርተር፣ መጋቢት 7 ቀን 2003 ዓ.ም)፤ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በሊሙ ኮሳ ወረዳ ከሳምንት በፊት በተከሠተው የሃይማኖት ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ባለመዋላቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ነዋሪዎቹ …

በጅማ በሃይማኖት ሽፋን ጉዳት ያደረሱ ወገኖች በቁጥጥር ሥር ባለመዋላቸው ቅሬታ እየቀረበ ነው Read more »

ኦህኮ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ይገልጻል። ሰላማዊ ትግሉን አላቋርጥም ይላል ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ መስተዳድር በተለያዩ ጊዜያት እስካሁን ከ102 በላይ የሚሆኑ ቢሮዎቹ በኢህአዴግ መንግሥት እንደተዘጉበት የገለጠው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ፣ ከዚህ ቀደም ያጋጥሙት ከነበሩት መሰናክሎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቀድሞ የፓርላማ አባላት የነበሩና …

የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ገለጸ Read more »

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋዜጠኛ አንተነህ ዘውዴ የአርብ ማርች 11 ቀን ውሎውን ሲያያዘው፤ እለቱን እንደማንኛውም ባተሌ አርብ “አስቀያሚ እና ሥራ የበዛበት” ከመኾን አልፎ የጃፓንን እጣ ፈንታ የሚፈታተን ይኾናል ብሎ አልገመተም ነበር። በእለቱ ወደ ነበረውን የሆስፒታል ቀጠሮ ከሔደ በኋላ ወደ ቤቱ አቀና። …

ኢትዮጵያውያን በጃፓን እንደምን ይኖሩ ይኾን? Read more »

በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “አምባገነኖችን እየናጠ ያለው ህዝባዊ ማዕበል ወደ አገራችን መቼ ይደርሳል?” በሚል ጉጉት ውስጥ ናቸው። ይህ ጉጉት ተገቢም፤ የሚጠበቅም ነገር ነው። በዚህ ጉጉት መነሻነትም ከየአቅጣጫው የተለያዩ  መልእክቶችንና ጥሪዎችን እንሰማለን። ህዝባዊው አመጽ አገራችን ውስጥ የሚጀመርበት ሁኔታ በአብዛኛው አገር ውስጥ …

በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የማጥቃት ዘመቻ አሁኑኑ ይጀምሩ!!! Read more »

ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን በወያኔ ቁጥጥር ሥር ላሉት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የወያኔ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በህዝብ ምርጫ ሥልጣን ላይ ከወጣን ገና 10 ወራችን ስለሆነ ህዝቡ በአመጽ ከሥልጣን ሊያስነሳን ምንም ምክንያት የለውም ሲል የቱንዚያው አይነት ህዝባዊ አመጽ በአገራችን …

ዘረኛው መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ከወጣን ገና 10 ወራችን ነው ስለዚህ የቱኒዚያው አይነት አብዮት በአገራችን ሊከሰት አይችልም አለ Read more »

ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰትን በመቆጣጠር የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም እየባዘነ ያለው ዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የሰሜን አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት በአገራችን ውስጥ የፈጠረውን ህዝባዊ መነሳሳት በመፍራት ኢሳትን ከአየር ለማውረድ  ይቻለው ዘንድ የገንዘብ ፤ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሃይል ሊያስገኝ በሚችለው አቅም ሁሉ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ …

ወያኔ ኢሳትን ከአየር ለማውረድ ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ ላይ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ምንጮች ገለጹ Read more »

የወያኔ አገዛዝ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሰሜን አፍሪካው አይነት ህዝባዊ አመጽ ሊነሳብኝ ይችላል  ከሚል ፍርሃት በርካታ ወጣቶችን በሰበብ አስባብ እያሰረ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ  በላከልን ሪፖርት ገለጸ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት አዲስ አበባን ጨምሮ ባሉት ትላልቅ ከተሞች ብዛት ያላቸው የደህነንትና የፈደራል …

የኦሮሞ ፈዴራሊስት ዋና ጸሃፊ ከ40 በላይ አባላቶቻቸው መታሰራቸውን ገለጹ Read more »

ከቱኒዚያ ተነስቶ በተለይም የሰሜን አፍሪቃ ሃገራትን የለበለበው ህዝባዊ ማእበል የበርካታ ሃገራትን በር ማንኳኳት ከጀመረ ወዲህ ዓለማቺን ለአምባገነኖች የነበራት ትእግስት አልቆ እንጥፍጣፊ ብቻ እንደቀራት የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፣ ፣ ዶ ር ብርሃኑ ነጋ …

ዶ|ር ብርሃኑ ነጋ ዓለም ለአምባገነኖች የነበረው ትእግስት መሙዋጠጡን ገለጹ Read more »

አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማና ራይትስ ዎች በግርድፍ ትርጉሙ ”ነጻነት አልባው ልማት” :የርዳታ ገንዘብ አፈናን ለማጠናከር ሲውል  Development without Freedom; How aid underwrites repression in Ethiopia በሚል ርዕስ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ሁለት የአውሮፓ ህብረት ኮሚቴዎች ማለትም “የሰብአዊ መብት …

የአውሮጳ ፓርላማ የኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ ስብሰባ አደረገ Read more »

ሰሜን አፍሪካንና መካከለኛውን ምስራቅ እያዳረሰ ያለው ህዝባዊ አብዮት ሊፈነዳ ይችላል የሚል ፍርሃትና ስጋት ሰንጎ የያዘው የዘረኛው መለስ ዜናዊ አገዛዝ በአዲስ አበባ ትላልቅ መንገዶችና አደባባዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥበቃ ቡድን እንዳሰማራ የግንቦት 7 ዘጋቢ ከላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል። ባለፈው ረቡዕና ሃሙስ …

የአዲስ አበባ አውራ መንገዶችና አደባባዮች በከፍተኛ የፖሊስ እና ፀጥታ ጥበቃ ሥር መሆኑ ታወቀ Read more »