የ IMF ዘገባና ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች የሚገኙ ሀገራት ምጣኔ-ሀብት በቀጣዮቹ 2 ዓመታት እድገት እንደሚያሳይ ተገለፀ። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቓም፤ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ፣ IMF ባወጣው ዘገባ ነው ይህን የገለፀው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች የሚገኙ ሀገራት ምጣኔ-ሀብት በቀጣዮቹ 2 ዓመታት እድገት እንደሚያሳይ ተገለፀ። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቓም፤ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ፣ IMF ባወጣው ዘገባ ነው ይህን የገለፀው።
(ሪፖርተር) — ዱባይ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ የአሠሪዋን ብልት በመቁረጧ ምክንያት በቁጥጥር ሥር መዋሏን ኤማራት አል ዮም ዘግቧል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የሰባ ዓመቱ አዛውንት ሁኔታውን ለፖሊስ ያስታወቁት ሰኞ ጧት ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊቷም ድርጊቱን ለመፈጸሟ የእምነት ቃሏን ሰጥታለች፡፡ ‹‹በሰውዬው በሚፈጽምብኝ ማስፈራራት ተሰላችቻለሁ፤›› ነበር …
የሐዋሳው ችግር አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ዝግጅት በአባላቱ የሐሳብ ልዩነት ሳቢያ አልተጠናቀረም፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያዘው አቋም ዋናው የልዩነቱ ነጥብ ነው። የአቡነ ጳውሎስ – አባ ሰረቀ ኮርፖሬሽን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጀው የ‹ብጥብጥ አፋልጉኝ› እና የውንጀላ ዘመቻ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ …
የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ በሐዋሳው ውዝግብ እና ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ ሥራ ስለሚደረገው አስተዋፅኦ ይወያያል Read more »
“የንፍሮ ቀቃይ ልጅ?” ሰው ባለማወቁ መሰደብ አለበት? ያውም በዐውደ ምሕረት ላይ? በዚህ መቼ በቃው። “ሥላሴ፣ እግዚአብሔር ወደዛ ወደዛ አትበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ” ሲል ማንም ተርታ ምእመን ሊፈጽመው የማይችለውን የድፍረት ንግግር አቅርቧል። የሚገርሙት ከኋላ ተደርድረው የተቀመጡት ጉዶች ናቸው። ልብሳቸውን አሳምረው ነገረ …
ዶቸ ቨለ (የጀርመን ድምፅ) ራዲዮ ከአንድ ሳምንት ገደማ ወዲህ አንስቶ የማሠራጫ ሞገዶቹ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውክም ሆነ የሚያፍን ድምፅ እንዳገጠማቸው በመጥቀስ የራዲዮ ጣቢያው ባለሥልጣናት፣ ሥርጭቱ፤ ከእውካ ነጻ ስለሚሆንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥት ይተባበር ዘንድ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ …
በሰሜን አፍሪቃና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ወደ አውሮጳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። በጣሊያኗ የላምፔዱዛ ደሴት ብቻ እስካሁን ከ22,000 በላይ ስደተኞች መድረሳቸው ተዘግቧል።
አማርኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ የሚል ማዕረግ ባይኖረውም፣ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ ነው፡፡ ልክ ከ፹ በላይ እንደሆኑት ቋንቋዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵዊነት በአማርኛ፣ አማርኛም በኢትዮጵያዊነት ይገለፃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በሃይማኖት መቻቻል አንቱ የተሰኘች ሃገር ናት – ‘ተብሏል፣ ብለናል፣ አስብለናል፡፡’ ታዲያ አማርኛስ ምን ያህል የሃይማኖታዊ …
እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ) ቻይና ሰራሽ እስክሪብቶዬን ከገዛኹት ሁለት ቀናት እንኳን አላስቆጠርኹም፡፡ ገና ከወዲሁ እየተቆራረጠ ግን ትዕግስቴን እየተፈታተነው ነው፡፡ በዘመኑ የአራዳዎች ዘይቤ «ሙዴ» ሊበላሽ አፋፍ ላይ እየተንገዳገደ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ የአምባሳደር ቡዝ ቃለ–ምልልስ አለብኝ፡፡ ለሁለተኛ ሳምንት መዝለቁ ምቾት አልሰጠኝም፡፡ አቦ! …
በበፍቃዱ ኃይሉ – “እዚህ ግቢ የሚሸጥ ዕንጀራ አለ” የሚል ፅሁፍ አንድ ግቢ በር ላይ ተፅፎ ባላይ ኖሮ ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ አልነሳሳም ነበር፡፡ ማስታወቂያውን አንብቤ ስጨርስ የሆነ ነገር እንደጎደለው ተሰምቶኝ ደግሜ አስተዋልኩት፡፡ እርግጥ ነው ዕንጀራ የሚለው ቃል ውስጥ ያለችው “ዕ” ለቃሉ …
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 11/2011)፦ ዓመታዊው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ከሚካሄድበት ከግንቦት ርክበ ካህናት አስቀድሞ አስቸኳይ የተባለ ጉባኤ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተጠራ መሆኑ ታውቋል። አጠራሩ ተገቢነት የለውም በሚል አባቶች ተቃውመዋል ተብሏል። የሐዋሳውን ውዝግብ ለመፍታት በሚል እየተጠራ ባለው በዚህ ጉባኤ የተያዘው የሐዋሳ ችግር ጉዳይ ቋሚ …
ሰበር ዜና፦ ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶስን ለአስቸኳይ ጉባኤ እየጠሩ ነው፤ ብዙዎች አባቶች አይገኙም Read more »
ከታቀደለት ጊዜ ወደ ሰዓት ገደማ ዘግይቶ ነበር የተጀመረው ስብሰባ «በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ላይ ከኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት የተዘጋጀ መድረከ ነበር። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ መንግሥት አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ አጠር ያለ የማስተዋወቅ ገለጻ በኋላ፣ ስለ ፭ ዓመቱ የዕድገትና …
ኤርትራ በባህር ዳርቻዋ ላይ ተይዘዋል ስለተባሉት እንግሊዛውያን የመጀመሪያ መግለጫዋን አውጥታለች ። ጉዳዩን ከፕሮፓጋንዳ እና ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጭ በትዕግሥት ስትከታተለው ቆይታለች። በቀጣይነትም የምታደርገው ይህንኑ ነው ሲል ባለፈው ዓርብ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ አስታውቋል። በሌላ በኩል የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር …
የመድረክ አመራር አባላት በስብሰባው ላይ ሲናገሩ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያለውን አንዳንድ እርምጃዎች የሚስማሙባቸውና የማይቀበሏቸውም እንዳሉ ለያይተው አስቀምጠዋል። የወቅቱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት መድረክ ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ መፈታት አለበት ብሎ ያምናል ብለዋል። አቶ ገብሩ በዓባይ ወንዝ …
ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን በዩኤስ አሜሪካ እና በካናዳ በርካታ ስብሰባዎች አካሄደ። የትምህርት፡ የመከላከያ እና የፍትህን ጨምሮ አርባ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ሚንስትሮች፡ ከፍተኛ ባለስልጣናትን እና የክልል መስተዳድር ፕሬዚደንቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋ ስብሰባዎች ባካሄዱባቸው ከተሞች፡ ወኪላችን አበበ …
በምርጫ አልተሸንፍኩም በማለት ዓለም ዓቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው ከአላሳን ዋታራ ኃይሎች ጋር ሲዋጉ የከረሙት የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝዳንት ሎሮን ባግቦ ተያዙ። የተቀናቃኛቸውን የአላሳን ዋታራን ቃል አቀባይ ጠቅሶ የጀርመን ዜና አገልግሎት DPA እንደዘገበው ባግቦ አቢዣን ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከቤተሰባቸው ጋር መያዛቸውን ቃል …
ቋሚ ሲኖዶስ ረቡዕ በዚህ ጉዳይ እንደሚነጋገር ይጠበቃል፤ (ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 11/2011)፦ በጥቂቶች ማስፈራሪያ ተልእኮውን ሳያጠናቅቅ የተመለሰው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ መፍትሔ እንዲፈለግ አለመደረጉ የሐዋሳን ምእመን እና ውጤቱን በገለልተኛነት የሚጠባበቀውን የክልሉን መንግሥት በእጅጉ እንዳሳዘነ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች ገለጹ፡፡ …
ቋሚ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚያስጠብቅ እና ሕዝቡን የሚያረጋጋ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች ጠየቁ Read more »
አብዛኛውን ጊዜ በብስክሌት የማቋርጠውን ትልቁን የኤዶጋዋ ድልድይ ዛሬ በእግሬ ልሻገረው እና ከበስተማዶ ካሉት በርካታ የሃገሬ ልጆች ጋር ወጌን ልጠርቀው ነው። ቢያንስ ግማሽ ሰአት ያህል ሃሳቤን እያወጣሁ እና እያወረድኩ ወደፊት ማቅናት አለብኝ። እርግጠኛ ነኝ እንደበፊቱ በተስፋ የተሞሉ እና የተረጋጉ ውይይቶች እንደማይኖሩ፤ …
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚገባቸው የጦርነት ቋንቋ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ከ10 ዓመት በፊት በጠራራ ፀሐይ አሻፈረኝ ያሉትን የሰላም ሐሳብ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለነበሩት ኮፊ አናን እኩለ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው ተንበርክከው እቀበላለሁ ባላሉ ነበር፡፡
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
አምባሳደር ዶክተር ተውፊቅ አብዱላሂ ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሱዳን ጠረፍ 40 ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘውና ቡምባዲ በምትባለው አካባቢ የሚገነባውን ታላቁ የሚሌኒም ግድብ የመሠረት ግንባታን መርቀዋል፡፡
መንግሥት ያዘጋጀው የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ረቂቅ አዋጅ ሰሞኑን ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በፕሮቪደንት ፈንድ ታቅፈው ላልነበረ የግል ድርጅት ሠራተኞች ዋስትና እንደሚሰጥ የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይገልጻል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የግል ድርጅት ተቀጣሪዎች ረቂቅ አዋጁን በበጐ ጐኑ የተመለከቱት …
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በሦስት ምስክሮች ምክንያት አይጥ ዝሆን ነሽ ተብሎ ተፈረደባት›› ዝሆኖች እንዲታሰሩና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡ በደረሳቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረትም ፖሊሶች ዝሆኖችን ማሰር ጀመሩ፡፡ ዝሆኖች ሲታሰሩ በዝሆኖች እግር ሥር ተደናግጣ ስትሽሎኮሎክ የነበረችው አይጥም፣ ከዝሆኖቹ ጋር አብራ ታሰረች፡፡ ከዝሆኖቹ ጋርም ፍርድ …
– ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች በዘካሪያስ ስንታየሁ አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
በውድነህ ዘነበ | ሪፖርተር የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡ የግብፁ ኩባንያ አስኮም ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በክልሉ 8,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ወርቅና የከበሩ …
በውድነህ ዘነበ የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡
አንድነት ፓርቲ – መድረክ ዛሬ በመቀሌ ለጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይቀሰቅስ መከልከሉን ገለጸ በየማነ ናግሽ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሰሞኑን ‹‹ሽብርና አመፅን ከሚቀሰቅሱ መካከል›› ያሉዋቸውን የአንድነት የፓርቲ አባላት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅ የሚቀሰቀስ ከሆነ የእንቅስቃሴው …
– እያንዳንዳቸው በአሥር ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ በታምሩ ፅጌ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ አሥሩም ተጠርጣሪዎች ከመጋቢት 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከአገር እንዳይወጡ በፍርድ ቤት እግድ ተጣለባቸው፡፡
በአስራት ሥዩም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ቀደም ሲል በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረውን የብድር ገደብ በማንሳት የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ መመሪያ ካወጣ በኋላ፣ ባንኮቹ ካለፈው ሐምሌ 2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 2003 ዓ.ም. ድረስ ለሰጡት ብድር 27 በመቶ …
በታምሩ ጽጌ ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ሸራተን አዲስን ከመገንባታቸው በፊት በነፃ ቤት ሠርተው እንደሰጧቸውና ይዞታውም የእነሱ እንደሆነ በወቅቱ እንደነገሯቸው የሚገልጹት ሆቴሉ ከተሠራበት ቦታ ላይ ተነስተው ወደ ሲኤምሲ የተዛወሩ በርካታ ነዋሪዎች፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቱ የራሱ መሆኑን በመግለጽ ሊነጥቃቸው መሆኑን …
በውድነህ ዘነበ በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የሚሌኒየም ግድብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የተጀመረው የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ትኩረት እየሳበ ሲሆን፣ ግዢውን ለመፈጸም በርካታ ሰዎች የኢትዮጵያ ልማት ባንክንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮችን እያጨናነቁ ነው፡፡
በየማነ ናግሽ የደቡብ ኮርያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በግብርና ልማትና በማዕድን ፍለጋ ኢንቨስትመንት ሊሠማሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ እና በለምለም ፀጋይ የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ባለድርሻና ሥራ አስኪያጁ አቶ አያሌው ተሰማ፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንንና አቶ ጌታቸው አጐናፍር መጋቢት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ካቀረቧቸው አምስት የመከላከያ ምስክሮች አራቱን አሰሙ፡፡
በልዩ ልዩ መገናኛ አውታሮች ለቀናት ሲተዋወቁ የሰነበቱት የኢትዮጵያ መንግስት ወያኔ የጠራቸው ስብሰባዎች፤ እንዲሁም በአንፃሩ የተጠሩ የተቃውሞ ሠልፎዎች በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችና በካናዳ በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል። ባልደረቦቻችን አዲሱ አበበና ሄኖክ ሰማእግዜር የዋሽንግተኑ ስብሰባ በተካሄደበት የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽና ከአዳራሹ መግቢያ ለተቃውሞ የተሰበሰቡ …
የፕሬዝዳንት ኦማር ጌሌን መንግስት በመቃወም አደባባይ የወጡ ጅቡቲያውያን በመንግስቱ ወታደሮች በኃይል እንዲበተኑ ከተደረጉበትና ታዋቂ የተቃዋሚ መሪዎችን ጨምሮ በርካቶች ለእስር ከተዳረጉበት ያለፈው የካቲት 11 አንስቶ ኅዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ባያቋጡም፤ የዜጎች በነፃ የመሰብሰብና የመቃወም መብት አሁንም እንደተገደበ ነው። ”ተቃዋሚዎች እየተዋከቡና የመንግስቱ የኃይል …
በስዊድን የኢትዮጵያውያን የሰልፍ ውሎ Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም April 9, 2011)፦ ትናንት ዓርብ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ትንሽ ትንሽ፣ ብን ብን ከሚለው ዝናብ በስተቀር ይሄን ያህል ብርድ አልነበረም። የስዊድን ክረምት (ዊንተር) ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ እንኳን …
በሰሜናዊ ሶማልያ የምትገኘው ሶማሊላንድ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በሱስ አስያዥ ዕጽ እና በወንጀል አንጻር በሚታገለው የተመድ መስሪያ ቤት ርዳታ በአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ በርዕሰ ከተማ ሀርጌሳ የተሰራ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት ከፈተች።
ማየት የተሳነው የ26 ዓመት ወጣት ስደተኛ ነው። ገና ዕውቅና ባላገኘችው ግን ራሷን ሐገር ብላ በሰየመችው ጎረቤት ሶማሊላንድ ውስጥ በስደት ሲባትት አራት ዓመታትን አስቆጥሯል። ታዲያ ተስፋ ያጣች መንፈሱን ዘወትር በብዕሩ ጠብታ በሚያፈልቃቸው የግጥም ሰንኞቹ ለማፅናናት ይሞክራል። በስደት ዓለም መከራ፦ ከአብራኩ የተከፈሉት …
ከአሜን ባሻገር ፡ ብዙ ያደናግር፣ ብዙ ያነጋግር ውድ አንባብያን፤ ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ ከፌስቡክ ድረ ገጽ ያገኘነው እና እናንተ ደጀ ሰላማውያን ብትመለከቱት ይጠቅማል ያልነው ነው። ፀሐፊው ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ "በአዲስ ጉዳይ መጽሔት መጋቢት ፲፭ ለታተመው ለበዕውቀቱ ስዩም ዐምድ፡ «እግር አልባው …
ቅዳሜ አፕሪል 9 ቀን 2011 በዳላስ ከተማ የመለስ ዜናዊ መልእክተኞች ስብሰባ ለማድረግ ሕዝብ ጠርተዋል። ይህ የሕወሐት/ኢሕአዴግ መልእክተኛ ቡድን አላማው የኢትዮጵያውያንን አንድነት የተቃዋሚውን ሊመጣ የሚችል ትብብር ለማናጋት ታስቦ የተሰራ በመሆኑ፤ ይህን መሰሪ አላማ በውጭ በነጻነት የምንኖር ሁሉ ልንቃወም ይገባል። በመሆኑም በዳላስ …
ዛሬ ጅቡቲያውያን መሪያቸውን ለመምረጥ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። በስልጣን ላይ ያሉት ኢስማኤል ኦማር ጌሊ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል። ዋንኞቹ ተቃዋሚዎች ከምርጫው ራሳቸውን አግለዋል።
“ሰሞኑን ሽብርና አመፅን የማቀናጀት ሤራ እየተጠነሰሰ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ተሣታፊዎች በሙሉ ዋጋ እንደሚከፍሉ አሳስበዋል። አቶ መለስ ይህን አስተያየት የሰጡት የመንግሥታቸውን የስምንት ወራት የሥራ ሪፖርት ለፓርላማው ባሰሙበት ወቅት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ነው። የመለስካቻው አምሃን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ፡፡
“ኦካምፖ 6” በሚል በአቃቤ ሕጉ ስም በዘፈቀደ የተሰየሙት እነዚህ ተጠርጣሪዎች በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ነው የክስ ዶሴ የተከፈተባቸው፡፡ ክሱ የተመሠረተባቸው በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት የተነሣውን አመፅና ብጥብጥ አቀናብራችኋል፣ ወይም እጃችሁ አለበት ተብለው ነው፡፡ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወይም ተከሣሾች …
ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚፈረጀው የሴቶች ግርዛት የሚያስከትላቸውን አስከፊ ጉዳቶች ለማስቀረት ታለመው የተከናወኑ ሥራዎች ሁነኛ ለውጥ ማስመዝገብ ቢያስችሉም፤ የተለያዩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች በወለዷቸው እምነቶች ሳቢያ ግን ቁጥራቸው የበዙ ሴቶች ዛሬም ግርዛት ይፈፀምባቸዋል። ይህን መሰሉ በሥፋት የታመነበት፥ አደገኝነቱና በሴቶች ላይ በዘለቄታው የሚያስከትላቸው ጉዳቶች …
በየመን የህዝባዊዉ አመፅ ግፊት አይሏል። ዛሬም በሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች በሰንዓ የተቃዉሞ ሰልፍ መቀጠላቸዉ ሲነገር አሁንም ፕሬዝደንት አሊ አብደላ ሳልህ ስልጣን ይልቀቁ የሚል ጥያቄያቸዉን አጠናክረዋል።