አውሮጳ የስደተኞች ማሻቀብ

በሰሜን አፍሪቃና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ወደ አውሮጳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። በጣሊያኗ የላምፔዱዛ ደሴት ብቻ እስካሁን ከ22,000 በላይ ስደተኞች መድረሳቸው ተዘግቧል።