የበዕውቀቱ ስዩም «እግር አልባው ባለክንፍ» ጽሑፍ ላይ የቀረበ ሂስ


ከአሜን ባሻገር ፡ ብዙ ያደናግር፣ ብዙ ያነጋግር

ውድ አንባብያን፤ ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ ከፌስቡክ ድረ ገጽ ያገኘነው እና እናንተ ደጀ ሰላማውያን ብትመለከቱት ይጠቅማል ያልነው ነው። ፀሐፊው ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ "በአዲስ ጉዳይ መጽሔት መጋቢት ፲፭ ለታተመው ለበዕውቀቱ ስዩም ዐምድ፡ «እግር አልባው ባለክንፍ» በሚለው ጽሑፍ ላይ የቀረበ ሂስ።" ሲሉ ያቀረቡትን ይህንን ጽሑፍ በዕውቀቱ ሥዩም ከተባሉት እና ለዚህ ውይይት መነሻ ከሆኑት ፀሐፊ ጽሑፍ ጋር አብረን አቅርበነዋል። ተመልከቱት። የተለያዩ ሰዎች የሰጧቸውን አስተያየቶች ለመመልከት ወደ "ፌስቡክ ገጻችን" ጎራ ይበሉ። 

ቸር ወሬ ያሰማን፤
ደጀ ሰላም

(ቄስ ወንድምስሻ አየለ):- የአምድህ ርእስም ሆነ የምታነሳቸው ጉዳዮች ሊታዩና ሊሄሱ የሚገባቸውን በዚህ ዘመን ላለው ትውልድ ጥቅም በትክክል የመረጥካቸው ናቸው። በዚህም ምክንያት በሚገባ በተረዳኸውና ባስተዋልከው ርእስ ማሄሱ ተፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን እንድተቀጥልበት እመክራለሁ፤ የተነገረውንና የተጻፈውን ሁሉ «አሜን» ብሎ ማለፉ በቂ ላይሆን ስለሚችል።
እኔም በተራዬ ያንተኑ ሂስ «አሜን» ብቻ ብዬ ላለማለፍ ከአሜን ባሻገር ልተቸው አሰብኩ። ጉዳዩ ሃይማኖታዊ በመሆኑና እኔም የማምነውንና የምመሰክረውን እሴት ስለነቀፍክብኝ ቢያንስ የሃይማኖቱ መመሪያ በሆነው መጽሐፍቅዱስ መነሻነት መገምገም ፈለግሁ።

(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)