መኢአድ 14 አባላቱን በፍርድ ቤት ማሳገዱን አስታወቀ

‹‹እኛን የማገድ ሥልጣን የላቸውም›› ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ

በብርቱካን ፈንታ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለድርጅቱ ውስጣዊ ብጥብጥ መንስዔዎች ናቸው ያላቸውን 14 አባላቱን በፍርድ ቤት እንዲታገዱ ማድረጉን ትናንት በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡