ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ራሱን የቻለ መሥሪያ ቤት ሊቋቋም ነው

– የኖርዌይ ልዕልትና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመጣሉ

በዳዊት ታዬ

የኮንፈረንስ ቱሪዝም ፍሰት እያደገና አሁን ባለው ደረጃ ከአቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ፣ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ብቻ የሚመለከት መሥሪያ ቤት እንደሚቋቋም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡