በነዳጅ ማደያ ላይ ፈንጂ በመጣላቸው በሞት የተቀጡ ግለሰቦች ውሳኔ ፀና
በታምሩ ጽጌ
ለም ሆቴል አካባቢና ከቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል አለፍ ብሎ ባሉ የኖክ ነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የፈነዱ ፈንጂዎችን ማጥመዳቸው የተረጋገጠባቸውና ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በሞት፣ በዕድሜ ልክና በዓመታት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው አምስት ግለሰቦች ላይ ቅጣቱ እንዲፀና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የካቲት 14 ቀን 2003 ዓ.ም. ውሳኔ አስተላለፈ፡፡