መካከለኛ ነጋዴዎች በአዲሱ ዕርምጃ መጎዳታቸውን ገለጹ

በውድነህ ዘነበ

ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት በራሳቸው አነሳሽነት መርካቶ ላይ የተሰበሰቡ 800 የሚጠጉ መካከለኛ ነጋዴዎች መንግሥት ‹‹የአገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ሥርዓት ለማስያዝ›› በሚል እየወሰደ ያለው አዲሱ ዕርምጃ ክፉኛ ችግር ውስጥ እየተከተታቸው መሆኑን ገለጹ፡፡