የኦሮምያ ተማሪዎች ተቃውሞና የምሁራን አስተያየት
በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና በምኒያፖሊስ ምኒሶታ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆችም ለኦሮሞ ተማሪዎች ያላቸውን አጋርነት በሰላማዊ ሰልፍ፣በሻማ ማብራትና በተለያዩ የውይይት መድረኮች በመግለፅ ላይ ናቸው።
በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና በምኒያፖሊስ ምኒሶታ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆችም ለኦሮሞ ተማሪዎች ያላቸውን አጋርነት በሰላማዊ ሰልፍ፣በሻማ ማብራትና በተለያዩ የውይይት መድረኮች በመግለፅ ላይ ናቸው።
የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ስላለ የወሰደውን 100 ሺሕ ሔክታር፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ ቢያቀርብም እስካሁን በሃራጅ ተሽጦ ባንኩ ሊያገኘው የቻለው 2.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የካሩቱሪ ዳይሬክተር ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለ100 ሺህ ሔክታር ሊዝ መሬት አንድ ጊዜ የሚከፈል 5.6 ሚሊዮን ዶላር በባንክ እንዳይከፍል ታዞ በጥሬ ገንዘብ ጉዳዩ […]![]()
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአሁን በፊት የባህርዳር ነዋሪዎች ባህርዳር ላይ የሚገኘው የአባይ ድልድይ ችግር አጋጥሞታል በማለት በልዩ ልዩ ስብሰባዎች ቢያሳስቡም የገዢው መንግስት አመራሮች በቅርቡ ተለዋጭ ይሰራል በማለት ሲሸነግሉ ቆይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የድልድዩ ወደ ሰሜን መውጫ ክፍል ላይ ያለው ንጣፍ ዝቅ እያለ በመሄዱ ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በቦታው የፌደራልና …
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የቴሌቪዥን ዘጋቢውንና ዜና አቅራቢውን ፍቃዱ ምርካናን ከእሥር እንዲፈቱ ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ቡድን – ሲፒጄ ጠየቀ፡፡
አኩሪ አተርን በተለያየ መንገድ ለምግብነት በርካቶች ይጠቀሙበታል። ከምሥራቅ እስያ አካባቢ መገኘቱ የሚገርለት ይህ የእህል ዘር በፕሮቲን የበለፀገ በመሆኑ ለተለያዩ የተመጣጠኑ ምግቦች ዝግጅት ሲዉል ዓመታት ተቆጥረዋል።
ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ትግል፣ ኢትዮጵያ እንደ እናት ሆና የረዳቻቸዉ ፣ እንደ ጋና፣ ታንዛኒያና ሴኔጋል ያሉ የአፍሪካ አገሮች እንኩዋን ሳይቀሩ የትናየት በደረሱበት ዘመን፣ እንደ ደርግ ዘመን አሁንም በኢትዮጵያ፣ ረሃብና ችጋር የሚገድለን አልበቃ ብሎ፣ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያዉያን እጅ እየተገደሉ ነው። በቅርቡ በጎንደር እና በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎቸ እንዳየነው፣ በዜጎች ላይ የደረሰው ግድያ፣ ድብደባና ግፍ እጅግ በጣም ልቤን እንዳደማው መግለጽ እወዳለሁ። […]
The post ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን -ሃብታሙ አያሌው appeared first on ሳተናው .
የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ ሃይማኖታዊው ኩነት እንዳይካሄድ ያስጠነቀቁ ቢሆንም አዘጋጆቹ ችላ እንዳሉትና ሟቹ ሃይማኖታዊ መሪ ሼኽ ዮኒስ ሙሴን ለማሰብ እንደተሰባሰቡ ምንጮች ጠቁመዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ የተሰባሰቡትን ሰዎች ለመበተን ሞክረው እንደነበር ጂቡቲ ያሉት ጋዜጠኞችና እማኞች ተናግረዋል። በሀገሪቱ ያለ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገድሉ ዘግቧል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከዛ የበዛ ነው ይላሉ።
የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ዛሬ ማረፋቸው ታውቋል።
ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ የወሰደውን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል። የኦሮሞ ህዝብ በአጋንንት ተመስሎ ተሰድቧልና ተሳዳቢው ባለስልጣን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል። መንግስት ለሞቱት ዜጎች ሃላፊነቱን እንዲወስድና ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በአዲስ አበባ የሚገነቡት ፎቆች የማን ናቸው? ሲሉም ጠይቀዋል።አርጅተናል አልቻልንም ስልጣናችንን እናስረክብ ያሉ አመራሮችም አሉ። ሰፊ ሰአት በሚሸፍነው ስብሰባ …
የሰማያዊ ፓርቲ እና የአራት ደርጅቶች ስብስበ የሆነው መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። ቀደም ሲል ኦፌኮ በአዳማና ለሌች የኦሮሚያ ቦታዎች ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረና በባላስልጣናት ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ እውቅና እንደተነፈገ ይታወቃል። ይህ የአሁኑ ሰልፍ ፣ በመድረክ ያሉትን እና ሰማያዊን ጨመሮ አምስት ደርጅቶች በጋራ የጠሩት ሰልፍ ሲሆን፣ የሚደረገዉን በአዲስ አበባ ነው። ኦፈኮ የጠራው ሰልፍ ማስተር ፕላኑን በመቃወም […]
The post ለታህሳስ 17 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ ተጠርቱዋል – የሚሊዮኖች ድምጽ appeared first on ሳተናው .
ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ቤቱ የሚዘጋጀውን ምግብ እንደማይበሉ ማሳወቃቸውንና ጩኸት በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ያመልጣሉ በሚል በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እስረኞቹ በርካታ በደሎች እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በሽብር […]
The post ባህርዳር ላይ እስረኞች ተቃውሞ አሰሙ appeared first on ሳተናው .
ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ከተማ ህዝቡ የመንግስትን እርምጃ ሙሉ በሙሉ አውግዟል። በሌላ በኩል መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተከትሎ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ ጠርተዋል። የሰልፉ አላማ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት …
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከዚህች ከኣዲስ ኣበባዋ የመሬት ነጠቃ ጥያቄ በጅጉ ገዝፎ የሄደ ነው። ከፍተኛው ጥያቄ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ህወሃት ይህን ዘረኛ ፖለቲካውን ተሸክሞ ኣዲስ ኣበባ ከገባ በሁዋላ በተለይ ኦሮሞንና ኣማራን ጸጥ ኣድርጎ ለመግዛት የተጠቀመው ዘዴ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ከታች እስከ ላይ ያሉትን ባለ ስልጣናት በኣልተማሩና የማስተዳደር ችሎታ በሌላቸው ነገር ግን ታዛዥ ብቻ በሆኑ […]
የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ብዙ ፈተናዎችን ያሳለፈች ወጣት ናት። ከልጅነቷ አንስቶ የቤት ሰራተኛ ሆና አገልግላለች ፤ኃላም የጎዳና ተዳዳሪ ነበረች። እዛው ጎዳና ላይም ነፍሰ ጡር እና እመጫት ሊስትሮም ሆና ሰርታለች።
ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ታመው ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ከገቡትና ለ10 ቀናት በህክምና ላይ ቆይተው ጥቅምት 6 ቀን ህይወታቸው ካለፈው ወይዘሮ አየለች ደግፌ ጆሮ ላይ የጠፋው 5 ግራም የጆሮ ወርቅ፤ ሆስፒታሉንና የሟች ቤተሰብን እያወዛገበ ነው፡፡ የሆስፒታሉ የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊ ሲስተር አስናቀች ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ወርቁ ከአስከሬኑ ጋር አብሮ የተገነዘ በመሆኑ መቃብሩ ይቆፈርልኝ” ማለታቸውን የሟች ልጅ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
እናቴን “ለመጨረሻ ጊዜ ፅኑ ህሙማን ክፍል ገብተን ስናያት ወርቁ ጆሮዋ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ” ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ከሞተች በኋላ ወርቁን ስጠይቅ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዟል ተባልኩኝ፤ እውነቱ እንዲወጣ ስለምፈልግ መቃብሩ እንዲቆፈር ብፈቅድም እስካሁን ምንም ምላሽ አላገኘሁም” ብሏል፡፡
“ዛሬ ነገ እያሉኝ በመመላለስ ብዙ ተንከራተትኩ፤ እኔ ጉዳዬ ከወርቁ አይደለም፤ ነገር ግን መቃብሩ ተቆፍሮ እውነቱ እንዲወጣና ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን እፈልጋለሁ” ይላል አቶ ሰለሞን፡፡ ሆኖም ሥራዬንና ጊዜዬን ከማባከን በቀር እስካሁን አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አማርሯል የሟች ልጅ፡፡
የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩምን አነጋግሬ ነበር ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ኃላፊዋ ወርቁን እንድትከፍል ወስነው ነበር፤ ነርሷ ዋጋውን ከጠየቀችኝና ከነገርኳት በኋላ ነው መቃብሩ ይቆፈር ያለችኝ” ብሏል፡፡ እኔ ከራሴ ጋር እየታገልኩም ቢሆን እውነት እንዲወጣ፣ ወጪውን ሸፍና ቁፋሮውን እንድታካሂድ ብፈቅድም ኃላፊዋ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረች ጊዜዬን እያባከነች ነው ያለው አቶ ሰለሞን፤ ሆስፒታሉ ለጉዳዩ እልባት የማይሰጠኝ ከሆነ ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ ፍርድ ቤት አመራለሁ ብሏል፡፡
አንድ ህመምተኛ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል (ICU) ሲገባ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ የጠይቀናቸው የህክምና ባለሙያ እንደነገሩን፤ ህመምተኛው “እንኳን ጌጣጌጥ ከቤቱ ያመጣውን ፒጃማ እንኳን መልበስ አይችልም፤ ብዙ ጊዜ ፅኑ ህሙማን በማሽን ስለሚተነፍሱና የልብ ምታቸው በየጊዜው ስለሚታይ በአብዛኛው ደረታቸው ክፍት መሆን አለበት፤ ስለዚህ በአንሶላና በብርድልብስ ብቻ ይሸፈናሉ” ከዚህ አንፃር ህመምተኞች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል ሊገቡ ሲዘጋጁ ማናቸውም ጌጣጌጥና ብራስሌት ወላልቆ ለቅርብ ቤተሰባቸው እንደሚሰጥ የጠቆሙት ባለሙያዋ፤ ይህም የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊዎች ሥራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
“የጆሮ ጌጡ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዞ ቢሆን እንኳን የፅኑ ህመምተኛ ክፍል ኃላፊዋ ስራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ከተጠያቂነት አያመልጡም” ብለዋል – ባለሙያዋ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩም ምላሽ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡
የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር […]![]()
መንግሥት ሁከት በሚፈጥሩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል
በጎንደር ጭልጋ አካባቢ ቅማንትና አማራ በሚል በተደራጁ ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች ለሞት መዳረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ነዋሪዎች በስጋት ከቤታቸው ሳይወጡ እንደሰነበቱ ምንጮች ገለፁ፡፡
ግጭቱ ስር የሰደደ እንደነበር የጠቆሙት የአካባቢው ምንጮቻችን፤ ከመስከረም ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ፣ ከሳምንት በላይ ባስቆጠረው አደገኛ ግጭትም ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
ቅማንት በሚል የተደራጀው ቡድን፣ “የቅማንት ጥያቄ እስኪመለስ ትምህርት የለም፤ እናንተም አትማሩም” በሚል ት/ቤቶች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር የጠቀሱት ምንጮች፤ በዚህም የተነሳ የአካባቢው ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል ይላሉ፡፡ የቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ምላሽ ካገኘ በኋላ ከሰሞኑ ለተፈጠረው ግጭት መነሻ የሆነው “ዞን ይዋቀርልን፣ ድንበር ይከለልልን” በሚል በተነሳ ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡
ቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩበት ከ3 ዓመት በፊት አካባቢው ውጥረትና ግጭት ተለይቶት እንደማያውቅ የሚጠቅሱት ነዋሪዎች፤ ከሁለት አመት በፊት ሚያዚያ ወር ላይ በአይከል ከተማ ከፍተኛ ረብሻ ተነስቶ ሰዎች መጎዳታቸውንና በርካታ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ባሳለፍነው ሐሙስ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ግጭቱ በከፍተኛ ደረጃ መቀስቀሱን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ በእለቱ አንድ የቅማንት ወጣት መገደሉን ተከትሎ ቅማንት በሚል የተደራጁ ቡድኖች፤ ዳቦ ቤት ማቃጠላቸውንና ሱቅ ማውደማቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን ተከትሎ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚል የተደራጁ ወገኖች በቋራ፣ ሺንፋ፣ ነጋዴ በሃርና ገንዳ ውሃ በተባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ቅማንቶችን እያባረሩ ቤት ንብረት ማቃጠል እንደጀመሩ ይገልፃሉ፡፡
ከእነዚህ አካባቢ የተባረሩ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ጭልጋ ውስጥ በየድንኳኑ ተጠልለው የአካባቢው ህብረተሰብ የእለት ጉርስ እያቀረበላቸው እንደሚገኝና ሰሞኑን ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው እንዳወያዩ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የተነሳ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን የሚጠቅሱት ምንጮች፤ ሰዎች ከቤት መውጣት እንደተሳናቸውና በየመንገዱ ጦር፣ ገጀራ፣ ቢለዋ፣ መጥረቢያና የጦር መሳሪያዎች የያዙ ሰዎች እንደሚዟዟሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ትናንት በአንፃሩ ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንደነበር ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በገጠር አካባቢዎች ተደራጅተው ለጠብ የተዘጋጁ የቅማንት ተወላጆችን መበተን እንዳልተቻለ የሚጠቅሱት የሚናገሩት ምንጮች፤ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ግን ከዚህ በኋላ በግጭቱ ተሳታፊ የሚሆኑና ፀብ የሚጭሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መናገራቸን ጠቅሰዋል፡፡ ህብረተሰቡም የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ላለመግባት ተስማምቷል ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ከቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ግጭቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመው የአካባቢውን ሰላም በሚያውኩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሒውማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰውና ሣምንታትን ባስቆጠረው ተቃውሞ ቢያንስ 75 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አስታወቀ።
በሀገሪቱ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ ሀገር ከመበታተኑ በፊት የሃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡
የመግባባት አንድነትና ሰላም ማህበር (ሰላም) ባወጣው መግለጫ፤ በሌሎች ሀገራት የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት ያስከተለው ጉዳትና ቀውስ በአገራችን እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች የሽምግልና ሸንጎ በማቋቋም፣ በሀገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ የብሄራዊ እርቅ ጥሪ እንዲያቀርቡ ተማፅኗል፡፡
ሀገርና ዜጎች ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የገቡበት አጋጣሚ አለመከሰቱን የጠቆመው ማህበሩ፤ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የሚታየው በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖትና በቀዬ የመከፋፈል አባዜ እስራትና ስደት እንዲሁም፣ ግጭትና ጦርነት መፍትሔ ይበጅለት ዘንድ እንዲተጉ ጠይቋል፡፡ በሃይማኖት አባቶች መካከል ያለው ግጭትም እልባት እንዲያገኝ ማህበሩ ተማፅኗል፡፡
ኢትዮጵያ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖባት መቆየቷ ባይካድም ያልተቋረጠ ግጭት እያስተናገደች ባለበት በአሁኑ ሰዓት “ፍፁም ሰላም የሰፈነባት አገር ናት” በሚል ከእውነታው መሸሽ ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፤ “በሀገሪቱ የበቀል እርምጃ እየሰፋና እየከፋ በመምጣቱ ምክንያት ማብቂያ ወደሌለው የጥፋት ጎዳና እያመራን እንገኛለን” ብሏል፡፡
“አስከፊ የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ እንደሚመጣ አስቀድመን ስጋታችንን ተናግረን ነበር” ያለው ማህበሩ፤ ሆኖም ለእርቀ ሰላም ስንማፀን “በሀገሪቱ ፍፁም ሰላም ሰፍኗል” በሚል ሰሚ ጆሮ ሳናገኝ ቀርተናል ብሏል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት በመተባበር ሀገሪቱ አሁን ከገባችበት አስጊ ሁኔታ ትወጣ ዘንድ እንዲፀልዩና የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረትም እገዛ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ቪቫ ላ ታማኝ!!!
በትናንትናው እለት በኦሮሚያ በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የተገደለ ወጣት የቀብር ሥነ-ስርዓት።
የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል፡፡
በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ትላንት ባስተላለፍነው ዝግጅት ማሰማታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የችግሩ ሰላባ ከሆኑት መካከል አንድ ሰማቸን ለመግለጽ ያልፈለጉ የትግራይ ተዋላጅን አነጋግረናል።
ውጭ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ።
ከጥቂቅ ደቂቃዎች በፊት ለዘ-ሐበሻ በደረሰው ዜና መሠረት በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ነውጥ ነበር:: የዚህ የተኩስ መነሻ ከልደታ ፍርድ ቤት እስረኞች ስላመለጡ ነው ተብሏል፡፡የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም እስረኞች ያመለጡ ሲሆን አክባቢው ተረብሾ ይገኛል፡፡ የአይን እማኞች እንደሚገልጹት እስረኞች አምልጠዋል በሚል ከሃያ በላይ የጥይት ድምጾችን ሰምተዋል፡፡ በተለይም በዛሬው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት መምህር […]![]()
የሳውዲ አረብያ የተፈጥሮ ሃብት፣ ሃገሪቱን ባለፀጋ እና ተሰሚነት ያላት አገር እንድትሆን አድርጓል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የሳውዲ የሃብት ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዘይት ዋጋ መውረዱና የየመኑ ጦርነት እንዲሁም በአካባቢው ከኢራን ጋር የሚካሄደው ሽኩቻ እስካሁን በገንዘብ አቅም የያዘችውን ቦታ ሳያሳጣት አይቀርም ።
እነ በረከተ መርገምት እና እነ ደመቀ መኮነን እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት የሚመራ ብዛታቸው ሰባት የሚሆኑ ልዑካን ወደ መተማ ከተማ ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ሂደዋል በስምንት የፌዴራል ፓሊስ ፓትሮል እየታጀቡ አቅንተዋል ። ከሱዳን ጋር በተሸጠው መሬት ሊመክሩ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ በሆኑ ሰዎች መረጃው ደርሶኛል ። በዚህ ጉዳይ ላይ የመተማ ከተማ እና የሸህዲ ከተማ ነዋሪዎች በግፍ በጭነት […]![]()
በቋራ፣በመተማና በሸንፋ በአካባቢዉ ታጣቂ አማጺያንና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል ሳምንቱን ሙሉ የተኩስ ልዉዉጥ አለመቋረጡን፣ የሞቱ ሰዎች መኞራቸዉ፣መንገድ መዘጋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል። በምእራብ ትግራይ ወልቃይት ጠገዴን ወደ አማራዉ መስተዳድር ለመመለስ የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህንንኑ በመስጋት ብአዴን የወልቃይት ህዝብንና ኢህአዴግን ለማሸማገል የሚያደርገዉ ጥረት ተቀባይነት እንዳላገኘ ታዉቋል። የወልቃይት ተወላጆች ለቢቢኤን እንደገለጹት ሽምግልና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የህዝብ […]![]()
የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የኬንያ ፖሊስ በሕገ- ወጥ አገሪትዋ ዉስጥ የሚኖሩ ያላቸዉን 54 ኢትዮጵያዉያን ማሰሩ ተመለከተ። እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ በኬንያ ናይሮቢ ካሳራኒ በሚባል አካባቢ ሦስት ክፍል ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን የተያዙት ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ እንደሆነ ገልጾአል።
‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው ክብሯ እንመልሳታለን፡፡ ያችን አኙዋዎች፣ ኑዌሮች፣ መዠንገሮች፣ ኦፖዎች፣ ኮሞዎችና ደገኞች አንድ ላይ በሕብረት የሚኖሩባትን – ጋምቤላ፡፡ ሁላችንም አፍሪካዊያኖች ነን፡፡ ጥላቻና ልዩነት ለማናችንም አይበጁንም…››
Everything is destroyed or burned at Sola Grow, a company that grows seedlings. When protests in Ethiopia, three Dutch agricultural businesses as well as destroyed. A rose grower, a seed company and a grass and livestock farm were targeted by violent protesters. “Our guards have their guns empty shot in the air, but the attack was […]![]()
ትናንት በባኮ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ ቆይታለች ። ወደ ነቀምት ያመሩ የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በባኮ ለማለፍ ተቸግረው ባኮ መግቢያ ላይ ለመገተር ተገደዋል ። በባኮ ተቃውሞ የፖሊስ መኪኖችና ድርጅቶች ተቃጥለዋል ።የአጋዚ ልዩ ኃይሎች ባኮ ከገቡ በኋላ የግብርና ኮሌጁን በመቆጣጠር ከመቶ በላይ ተማሪዎችን በኦራል መኪና ጭነዉ ከከተማዋ ውጪ በመውሰድ ፎቶግራፍና እና ቪድዮ ቀርፀዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹን […]![]()
ከአዲስ አበባ ጎንደር የገቡት የአገዛዙ ባለስልጣናት የህወሓቱ አባይ ፀሀዬ፣ የህወሓት ተላላኪ የሆነው ብአዴን ቁንጮዎች በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ናቸው፡፡ የክልሉ ሹም ገዱ አንዳርጋቸውም በአጃቢነት ተገኝቷል፡፡ አባይ፣ በረከትና አዲሱ በትናንትናው ዕለት የዞኑን ካቢኔ አባላትና ጥቂት የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎችን በጎሃ ሆቴል ሰብስበው በጎንደር ስለሰፈነው አለመረጋጋት፣ አመፅና ጦርነት ለማነጋገር ሞክረው “ይህ ሁሉ ችግር ከደረሰና ሁኔታው ከቁጥጥር […]![]()
በዮሐንስ ደሳለኝ (ጀርመን – ፍራንክፈርት)
በየዓመቱ ዲሰምበር 10 የሚከበረው የሰብዓዊ መብት ቀን ሐሙስ December 10,2015 በፍራንክፈርት የዋናው ባቡር ጣቢያ አካባቢ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አመሸ። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ተገን ጠያቂዎች የተገኙበት ይህ አከባበር ለየት ያለና የወቅቱ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባው ብርድ ያልበገረው ነበር።
በጋራ ግብረ ኃይል የፖለቲካው ትግል ይቀጥላል ሰማያዊ ፓርቲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በመስጠት፣ መንግስት የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመከታተል ለማጋለጥ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎችን በጋራ ለማካሄድ እንደተስማሙ ምክትል ሊቀመንበሩ […]
The post ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ appeared first on ሳተናው .
የጂቡቲ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች በዘመናዊ መሣሪያ በመፈተሽ በአንድ ኮንቴይነር ዕቃ፣ ከአሥር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡
የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር አዲሱን ክፍያ እ.ኤ.አ. ከጥር 15 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ አዲስ አሠራር 85 በመቶ የሚሆነውን የወጪና ገቢ ንግድ በጂቡቲ ወደብ በኩል ለምትጠቀመው ኢትዮጵያ ዱብ ዕዳ ሆኗል፡፡
ባለፈው ዓርብ ታኅሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ይህ መረጃ ለኢትዮጵያ መንግሥት እንደደረሰ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከጂቡቲ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስወደብና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቺፍ ኢንጂነር ዓለሙ አምባዬ ባለፈው ዓርብ ምሽት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩን ከአንድ ሰዓት በፊት መስማታቸውን ገልጸው፤ ከማሪታይም ባለሥልጣን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ማብራሪያ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
የማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኰንን አበራ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ አዲሱ ክፍያ የውጭ ዕቃዎችን ይመለከት እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር የኤክስወደብ ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አሰፋ ሙሉጌታ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር የመፈተሽ አቅሙን ለማሳደግ ከዚህ በፊት ከነበረው ልማዳዊ አሠራር (ማንዋል) ወደ ዘመናዊ (ዲጂታል) የፍተሻ ዘዴ ለመሸጋገር ሲሠራ ቆይቷል፡፡
በልማዳዊው የቀድሞ አሠራር ለፍተሻ ክፍያ አይጠይቅም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2016 በሚጀመረው ዘመናዊ ፍተሻ ግን ክፍያ እንደሚጠይቅ፣ የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር ለኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ምንጮች እንደተናገሩት፣ ይህ ክፍያ በፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ይህ ያልተጠበቀ ክፍያ ከተጀመረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከመፈተኑ ባሻገር የኑሮ ውድነቱን እጅግ ያባብሳል ይላሉ፡፡
‹‹በኮንቴይነር ክፍያ የፈጸመ ነጋዴ ላወጣው ወጪ ክፍያ የሚጠይቀው ኅብረተሰቡን ነው፤›› በማለት የሚናገሩት የኢንተርፕራይዙ ምንጮች፣ አገሪቱንም ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ያስወጣታል በማለት አዲሱ የጂቡቲ መንግሥት ተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ፣ አገሪቱን ለውስብስብ ችግር እንደሚዳርግ አበክረው ገልጸዋል፡፡
ጂቡቲ ተጨማሪ ገቢ የሚገኝበትን አዲስ አሠራር ለመጀመር መዘጋጀቷን የሰሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በዚህ ያልተጠበቀ የጂቡቲ መንግሥት ዕርምጃ በመደናገጥ የጂቡቲን መንግሥት ሐሳብ ለማስለወጥ ንግግር ለመጀመር ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡
“አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ፤ በእነኚህ ጉዳዮች ላይ፥ በዓላማው ላይ፥ በይዘቱ ላይ፥ የተማላ ግልጽነት፥ የተሟላ መተማመን፥ የተሟላ የጋራ መግባባት ባልተያዘበት ሁኔታ እነዚህ ጥያቄዎች እየተነሱ እያሉ የክልሉ መንግስት አይቶ እንዳላየ ሆኖ ዘሎ ወደ አፈጻጸሙ የሚገባበት ሁኔታ አይኖርም። ይሄንን ለሕብረተሰቡ ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።” የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር…
ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች። ታጣቂዎቹ …
ቁ፡ 1 12/14/2015 በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ከቤተ አማራ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ የአማራ ህዝብ ጀግኖች አባቶቹና እናቶቹ ከሌሎች አገር ወዳድ ወገኖች ጋር በመሆን ከመሰረቷት ብሎም በተከታታይ የደም እና የአጥንት ዋጋ ከፍለው ጠብቀው ካቆዩአት የገዛ አገሩ ለዘመናት በተሸረበ ሴራ ወደ ጎን …
“በኦሮሚያ ክልል እየሞቱ ያሉት አማሮች ገዳይ ወያኔ ነው ፤ አማራው ከኦሮሞው ጋር መተባበር አለበት” – ከቤተ አማራ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ Read more »
የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበዉ መድረክ ዛሬ ባወጣዉ በመግለጫዉ የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ «ሕገ-ወጥ» በማለት ተቃዉሞታል። ዕቅዱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይላት በወሰዱት እርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን፤ በመቶ የሚቆጠሩ መቁሠላቸዉንም መድረክ አስታዉቋል።
ላለፉት በርካታ አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየከረረ ነው፤ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል እያልን ስንጎተጉትና ስንጽፍ ነበር። ህዝብ ይሄንን መንግስት በጣም እንደሚጠላ፤ ሕዝብ ጨዋ ስለሆነ ታግሶ እንጂ የመረረው እለታ ጉድ እንደሚፈላ ስንናገርና ስናስጠነቅቅ ነበር። ሰዎቹ አልሰሙንም። ጭራሽ 100% አሸነፍን ብለው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት በገሃድ አሳዩ። ከአንድ ሶስት ወራት በፊት በዲቪ የመጣ አንድ የመንግስት ሰራተኛ “ ነገሮች በጣም ታምቀዋል። […]
The post ደግሜ አስጠነቅቃለሁ – ግርማ ካሳ appeared first on ሳተናው .
ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ላለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ለመከላከል መከላከያ ሰራዊቱን ሳይቀር አሰማርቶ በወሰደው እርምጃ ከ45 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በመላ ኦሮምያ በሚገኙ ከተሞች የፀጥታ ሃይሎች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ።የመንግስት ባለስልጣናት የአዲስ …
ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንዳስነሳው በሚነገረው ግጭት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በአማራና ቅማንት ህዝብ መካከል ለዘመናት የቆየውን አንድነትና ዝምድና በማፍረስ አካባቢውን ወደ ግጭት ለመቀየር ገዢው ፓርቲ አስታጥቆ ያሰማራቸው ሚሊሺያዎች ግድያ እየፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ድርጊት ተፈጽሞ አያውቅም የሚሉት ነዋሪዎች ግጭቱ …
ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በአንዋር መስጊድ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ ፣ ዛሬም በአዋሳና ሻሸመኔ ድንበር አካባቢ ተመሳሳይ ፍንዳታ ተከስቶ 2 ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ ጥቃቱ በኦሮምያና ደቡብ ክልሎች መካከል መካሄዱ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለማጋጨት ሊሆን ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።