የጂቡቲ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ አዲስ ክፍያ ሊጠይቅ ነው
የጂቡቲ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች በዘመናዊ መሣሪያ በመፈተሽ በአንድ ኮንቴይነር ዕቃ፣ ከአሥር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡
የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር አዲሱን ክፍያ እ.ኤ.አ. ከጥር 15 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ አዲስ አሠራር 85 በመቶ የሚሆነውን የወጪና ገቢ ንግድ በጂቡቲ ወደብ በኩል ለምትጠቀመው ኢትዮጵያ ዱብ ዕዳ ሆኗል፡፡
ባለፈው ዓርብ ታኅሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ይህ መረጃ ለኢትዮጵያ መንግሥት እንደደረሰ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከጂቡቲ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስወደብና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቺፍ ኢንጂነር ዓለሙ አምባዬ ባለፈው ዓርብ ምሽት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩን ከአንድ ሰዓት በፊት መስማታቸውን ገልጸው፤ ከማሪታይም ባለሥልጣን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ማብራሪያ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
የማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኰንን አበራ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ አዲሱ ክፍያ የውጭ ዕቃዎችን ይመለከት እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር የኤክስወደብ ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አሰፋ ሙሉጌታ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር የመፈተሽ አቅሙን ለማሳደግ ከዚህ በፊት ከነበረው ልማዳዊ አሠራር (ማንዋል) ወደ ዘመናዊ (ዲጂታል) የፍተሻ ዘዴ ለመሸጋገር ሲሠራ ቆይቷል፡፡
በልማዳዊው የቀድሞ አሠራር ለፍተሻ ክፍያ አይጠይቅም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2016 በሚጀመረው ዘመናዊ ፍተሻ ግን ክፍያ እንደሚጠይቅ፣ የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር ለኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ምንጮች እንደተናገሩት፣ ይህ ክፍያ በፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ይህ ያልተጠበቀ ክፍያ ከተጀመረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከመፈተኑ ባሻገር የኑሮ ውድነቱን እጅግ ያባብሳል ይላሉ፡፡
‹‹በኮንቴይነር ክፍያ የፈጸመ ነጋዴ ላወጣው ወጪ ክፍያ የሚጠይቀው ኅብረተሰቡን ነው፤›› በማለት የሚናገሩት የኢንተርፕራይዙ ምንጮች፣ አገሪቱንም ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ያስወጣታል በማለት አዲሱ የጂቡቲ መንግሥት ተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ፣ አገሪቱን ለውስብስብ ችግር እንደሚዳርግ አበክረው ገልጸዋል፡፡
ጂቡቲ ተጨማሪ ገቢ የሚገኝበትን አዲስ አሠራር ለመጀመር መዘጋጀቷን የሰሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በዚህ ያልተጠበቀ የጂቡቲ መንግሥት ዕርምጃ በመደናገጥ የጂቡቲን መንግሥት ሐሳብ ለማስለወጥ ንግግር ለመጀመር ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡
ይህቺማ ማንን ለማታለል ነው በግልፅ ለመዝረፍ ነው እንጂ ይህም አሁን በፈጣን ባቡር በተባለው መጓጓዣ ሥርአት በርካታ እቃዎች ወደብሽላይ ከሚከፍሉት ዲሞሬጅ ልናመልጥ በመሆኑ በተዛዋሪ በተሽካርካሪዎች በአፋጣኝ ወደብ አለመድረሥ ብልሽት ወዘተ ለምንከፍለው ኪሣራ ጅቡቱ መፈርጠሟ ይታወቃል ይህን የሚያካክሥ ዘዴ ከወያኔ አቻዎቻቸው ጋር በመሆን ዝርፊያውን መላ ፈጥረው ተመልሠዋል ይህን ጠቅለል አርገን ሥናየው ባቡሩ ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ አሁንም ካለው የነዳጅ ውድነት 18 ብር ያላነሣ ለውጥን እንደማያመጣ ከተጣለብን የህገወጥ የዝርፊያ ሥልት መገንዘብ እንችላለን።
ማሥታወሻ፦ ዛሬ ያለው የብንበርግ የነዳጅ ዘገባ የ1 በርሜል ድፍድፍ 30$ መሆኑን ግንዛቤ እንውሠድ
**********************************************************
As the saying goes “you will reap what you sow”, the TPLF retards brought this great country to its knees bu relinquishing the Red Sea coastline to their Eritrean kins. This is one of the great strategic disaster our country ever had.
It is high time now to get back the port of Assab and Afar lands and coastline to the rightful owners. Ethiopia can not be a milking cow for a tiny Djibouti forever. Our message to TPLF is bring back our rightful property or face the music – dismantling the very system that killed our nation. Negotiation with Djibouti is a temporary fix that will never bring lasting solution. We shall face TPLF squarely and let them know enough is enough. Enough!!!!!!