የባኮ ግብርና ኮሌጅ ተማሪዎች የት እንደተወሰዱ አልታወቀም

ትናንት በባኮ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ ቆይታለች ። ወደ ነቀምት ያመሩ የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በባኮ ለማለፍ ተቸግረው ባኮ መግቢያ ላይ ለመገተር ተገደዋል ። በባኮ ተቃውሞ የፖሊስ መኪኖችና ድርጅቶች ተቃጥለዋል ።የአጋዚ ልዩ ኃይሎች ባኮ ከገቡ በኋላ የግብርና ኮሌጁን በመቆጣጠር ከመቶ በላይ ተማሪዎችን በኦራል መኪና ጭነዉ ከከተማዋ ውጪ በመውሰድ ፎቶግራፍና እና ቪድዮ ቀርፀዋቸዋል