ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያንን በጅምላ ማሰሩን ቀጠሉአል፤ ሰሞኑን በሽብርተኝነት ሥም 29 የኦሮሞ ተወላጆች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ
ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስብኝ ይችላል በማለት እንቅልፍ እያጣ የመጣው የወያኔ አገዛዝ ሰሞኑን በዜጎች ላይ ጅምላ እስራት ማካሄዱን በመቀጠል የኦነግን የሽብር ዓላማ ያራምዳሉ በማለት 29 ሰዎች ማሰሩን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ አመለከተ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት የዘረኛው ወያኔ ሰለባ ከሆኑት 29 ግለሰቦች መካከል የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግሬስ (አሕኮ)ና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ፓርቲዎች አባል የሆኑ ዘጠኝ ግለሰቦች ይገኙበታል። […]