የቤንሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ተነሱ
– የፀረ ሙስናና የፖሊስ ኮሚሽነሮችም ተነስተዋል
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ጋስ፣ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለአምስት ቀናት ባደረገው ግምገማ ከነሐሴ 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡