እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈንና ማሰር ላይ የተሰማራ ጁንታ (ምንሊክ ሳልሳዊ‬)

Minilik Salsawi – ህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት አገር ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለእስር የተዳረጉባት አገር እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዘረፋ ላይ እና ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈን እና ማሰር ላይ የተሰማራ ጁንታ በነገሰበት አገር ውስጥ የምንኖር ተጨቋኝ ብዙሃን የህዝቦች የጋራ መተባበር እና ለለውጥ መነሳት አስፈላጊ እና እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ መሆኑን በማወቅ እያንዳንዳችን ከትግሉ በመቀላቀል ለነገው ትውልድ እና ለዛሬው እኛነታችን ነጻነት መሳካት ድርሻችንን ማበርከት ግድ ይለናል።

ወያኔ የያዘው መንገድ አጥፍተህ ጥፋ የሚል ጸረ ሰላም እና ጸረ ሕዝብ ከመሆኑም በላይ በጸረ አሸባሪነት ቁማር ምእራባውያንን ተገን በማድረግ ዜጎችን ለከፍተኛ እንግልት እና ሰቆቃ እየዳረገ ሲሆን በየትኛውም አለማችን ክፍል ያልታየ እና የሽብርተኝነት ውጊያ እናካሂዳለን የሚሉ ሃያላኖች እንኳን በተግብር በሃገራቸው ወንጀል እና ሽብር ሲፍጠር በፍጹም ዜጎቻቸውን የማይወነጅሉበትን ህግ ወያኔ ግን ህግ ይከበር የሰው ልጆች እኩልነት እና ነጻነት ይረጋገጥ ባሉ ዜጎች ላይ አጸያፊ እርምጃ ለመውሰድ እና የተቃወመውንም ይሁን የሚመክረውን ሁሉ አሸባሪ በማለት እየወነጀለበት ይገኛል።

ይህ የማያዛልቅ የወያኔ ጸሎት ይህን ሰሞን አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።ወያኔ የጀመረው የስልጣን ማስረዘሚያ ስልት ራሱን እና በክሎኒግ ያባዛቸውን ጭፍሮቹን ወደ መቃብር እያወረደ መሆኑ ለአፍታ ቆም ብሎ ማስብ አልቻለም።ካለወያኔ መኖር የማይችሉ በጥቅም የታሰሩ በደረቅ ፖለቲካ የታወሩ እውቀት አልባ ካድሬዎች እና ሹምባሽ ደህንነቶች የአገሪቱ አንጡረ ሃብት በመዝረፍ እና ዜጎችን በመግደል በዚሁ የሚቀጠል መሆኑን አስበውት ከሆነ ተሳስተዋል።በአሁን ሰአት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ፈላጊ ሃይል በመሆኑ ወደ ትግሉ መሰማራቱን ወደው ሳይሆን በግድ እውነትን እንዲውጡ እናደርጋቸዋለን።ለሃገሪቱ እና ለህዝቡ በማሰብ በሂደት ለውጥ ለማምጣት የተጀመረው ጉዞ ወደ በቀላዊ መንገድ የተቀላቀለ በመሆኑ በቅርብ ቀናቶች ውስት ወያኔ የጀመረው የማያዛልቅ ጸሎት እንዴት እንደሚያስቀጽፈው በተግባር እናሳየዋለን። ከትግሉ በመቀላቀል ለነገው ትውልድ እና ለዛሬው እኛነታችን ነጻነት መሳካት ድርሻችንን ማበርከት ግድ ይለናል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

7 Comments on “እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈንና ማሰር ላይ የተሰማራ ጁንታ (ምንሊክ ሳልሳዊ‬)”

  1. Who are you guys hoping to deceive? Every Ethiopian knows by now that you guys are a bunch of former derg caderes who were responsible for the 17 years of mass killing of innocent ethiopians. You can bark how much you want but the truth is the whole world now is disgisted by the hollow propaganda shaibya is instructing you to spread.

  2. Actually we are 18 to 25 years old. You can call as Derg and we are fine with it. Woyanee made derg look like an angele. What we dont want to be is Woyanee since it means everything evil.

  3. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    የምእራቡ ዲያስፖራና ተልባ አንድ ናቸው:ሁለቱም ቢንጫጩ ባንድ ሙገጫ ይወገጣሉ:መቼም ዲያስፖራ ይዘራሉ ግን ፍሬ አያፈሩም:ይለምናሉ,ግን አያገኙም:በር ያንካካሉ ግን አይከፈትላቸውም::

  4. ደርግም ኢህአዴግም ሁለቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ታሪክ የማይረሳው እና አሳዛኝ ፈርጀብዙ ኢሰብአዊ ግድያ በህፃት፣ወጣቶች፣አዋቂዎች፣አዛውንቶች፣ምሁራን እና ወታደሮች ላይ ፈፅመዋል እየፈፀሙም ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*