ቅምጥሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን የበረራ አስተናጋጆችን መቅጠሩ ተሰምቷል (ቪዲዮ)

በቂ የተማረ የሰው ሃይል ባለበት ኢትዮጵያውያንን በቻይንኛ ቋንቋ አሰልጥኖ በሃገሪት የተንሰራፋውን የስራ አጥነት መቅረፍ እየተቻለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን ሴቶችን ሰብስቦ በበረራ አስተናጋጅነት መቅጠሩን CCTV Africa በድህረገጹ በቭድዮ አስደግፎ አስነብቦናል::

በኢስያ አፍሪካ መካከል የሚገኘውን የበረራ ደንበኞች ቁጥር ያሳድግልኛል ብሎ የታሰበው የአየር መንገዱ እርምጃ እጅግ የተሳሳተ እና በትንሽ ስልጠና ታግዞ ለዜጎች የሚደረገውን ቅድሚያ የመስጠት እድል እንዳበላሸው የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች አየር መንገዱ ቢያስብበት የቋንቋ ስልጠና እጅግ ቀላል እና ለዜጎች የተሻለ በር ለመክፈት የሚረዳ ነው::ሲሉም አክለው ተናግረዋል ::ቻይናውያን ደንበኞቼ በርክተውብኛል የአለም አቀፍ የበረራ ስፘኤ አድጎልኛል ስለዚህ ቻይናውያን የበረራ አስተናጋጆችን ቀጥሯለሁ የሚለው አየር መንገዱ ስራ አጥ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን በዘርፉ አሰልጥኖ ለማሰራት አለመፈለጉ ትዝብት ውስጥ የከተተው ሲሆን በዚህ ጉዳይ አጥጋቢ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም::

[youtube http://www.youtube.com/watch?v=7mL5y8v0kkg]