ወፈፌው ፌስቡክ… (ትንሽ ቀልዳዘል ምክር) – ዳንኤል ተፈራ
ፌስቡክ አንዳንዴ ጨርቁን ጥሎ ያብዳል። እብደቱ ገጀራ እስከማቀበል ሊደርስ ይችላል። እንደዚህ ሲሆን በተቻለ መጠን ጥግ ይዘህ አሰላስል፤ አብረህ እንዳታብድ ተጠንቀቅ። አንዳንዴ ደግሞ ፌስቡክ ወፈፌ ይሆናል። ወፍፎ ያወፍፍሃል። አብረህ ትወፍፍና “ግን ምን ነካኝ?” ብለህ ራስህን ትጠይቃለህ። አንዳንዴም መረን የለቀቀ ባለጌ ያደርግሃል። …