ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች የሰጠችውን የጥገኝነት ፍቃድ አልቀለበሰችም – ህዳር 06, 2015
የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያ ለመሳተፍ ወደ ቦትስዋና በቅርብ ለሄዱት 10 የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት የቦትስዋና መንግስት ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም በማለት በቦትስዋና ጥገነት የጠየቁት…