የባንክ ባለሙያዎች ከውጪ ምንዛሬ ጋር በተያያዘ ሐገሪቷ አደጋ ውስጥ ናት ይላሉ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) –

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሃገሪቱ ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች በባዶ ካዝናዎች ተተክተዋል ይላል ከባንኮች አከባቢ የሚወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት በላኪነት ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት የገዢው መደብ ባለስልጣናት እና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጥቅም ትሥሥር ላይ የተለጠፉ አቆርቋዥ ነጋዴዎች ንግድን ሽፋን በማድረግ ሃገሪቷን በማራቆት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ::አንዳንድ ባለስልጣናት ደሞ እንደ ቻይና ህንድ እና ቱርክ ከመሳሰሉ ከውጪ አገር ዜጎች ጋር የውስጥ ሽርክና በመፍጠር በጥቅም ትሥሥር ከመሬት ጀምሮ እስከ ማንኛውም ማተሪያሎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ በኢንቨስትመንት ስም ከሚመሰረተው ድርጅት ጋር የማይገናኙ ውድ እቃዎች ሳይቀሩ ገብተው ሃገሪቷ ማግኘት የሚገባትን እንዳታገኝ ባለስልጣናት ጋሬጣ ሆነዋል:: ሃገሪቱ ለምታስገባው እቃዎች የምታወጣው የውጪ ምንዛሬ ከላኪዎች ከምታገኘው የውጪ ምንዛሬ ሰባት እጥፍ ነው::የውጪ ምንዛሬ ዳገት ሆኖባታል::

እንደባንክ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ የወያኔ ባለስልጣናት ቤተሰቦች እና ዘመድ አዝማዶች በላኪነት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ገንዘብን ምንም አይነት ዋስትና ሳያሲዙ በአነስተኛ ወለድ እየወሰዱ የማይከፍሉ እና ሰነድ የሚያስጠፉ እንዲሁም ያለምንም ቀረጥ እና ታክስ ወደ ውጭ ሃገር ምርቶችን በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የኢሲያ ሃገራት ባንኮች ይዶሉታል:: የባለስልጣናት ቀጭን የስልክ ትእዛዝ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ኢሮዎች እና ፓውንዶች ከባንክ ይወሰዳሉ።

ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን ለመሸጥ እና ለመግዛት ዋጋ ቢወስንም የግል ባንኮች ግን የውጭ ምንዛሬ መግዣ ዋጋን ወደጎን በመተው ከወያኔ የላኪ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ በመሸጫ ዋጋ እንዲሸምቱ ሲደረግ በዝምታ ታልፈዋል:: አንዳንድ ላኪዎች ከመንግስት ባንኮች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ በተዘዋዋሪ ለግል ባንኮች ሲቸበችቡ እየታየ በዝምታ እየታለፈ ነው::በመተማ በሞያሌ በመልካ ጀብዱ በኩምሩክ በሁመራ በሃርትሼክ ወዘተ በኢትዮጵያ ዙሪያ ገባ የድንበር ከተሞች ላይ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩት በአብዛኛው የወያኔ አባላት እና የአከባቢ ባለስልጣናት ካድረዎች ከሚወጡ የሃገር ውስጥ ምርቶች የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት ታውቋል::ይህም ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::

መሰረታዊ ለሆኑ የገቢ እቃዎች የጠፋው የውጭ ምንዛሬ በባለስልጣናት ሲዘረፍ ለሃገሪቱ የፖለቲካ ፍጆታ የመከላከያ እና የደህንነት መዋቅሮች ሲመደብ ማየት በህዝብ ጉሮሮ ላይ ቆሞ ስልጣንን በማስረዘም ሃገርን እየገደሉ መሆኑ በአደባባይ እያየነው ያለነው ሃቅ ነው:;የብሄራዊ ባንክ ከጊዜው የገዢ መደቦች ጋር በማበር የሃገርን ሀለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች አሳልፎ እየሰጠ ከባንክ አሰራር ውጭ ከፖለቲካው ጋር ግንኙነት ያሌላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ማግኘት ያለባቸውን የውጭ ምንዛሬ ባለማግኘታቸው በሰላሳ እና አርባ ፐርሰንት ጭማሪ ምንዛሬዎችን በመግዛት ጋሬጣ የተፈጠረባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ የገዢው መደብ አባላት የፈጠሩት የውጭ ምንዛሬ ዘረፋ በሃገሪቷ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲሰራፋ አድርጎታል:: #ምንሊክሳልሳዊ

 

12 Comments on “የባንክ ባለሙያዎች ከውጪ ምንዛሬ ጋር በተያያዘ ሐገሪቷ አደጋ ውስጥ ናት ይላሉ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) –”

  1. weyane ethiopian badu askerat weyna hagera ethiopia ahunm edgmwalew berket simone eskalhe derase ethiopia alklate mote lberket simone

  2. I am calling Arbegnochginbar special force to kill top tplf leaders before they destroy our country Ethiopia:

  3. Ethiopia’s Top enemy are ferenjis.

    Woyane in power because ferenjis want that.

    The ferenjis, USA and EU, are responsible for all crimes committed by woyane.

    ” Making The World A More Dangerous Place

    Forget anything you might read about “brutal dictators” that need to go or the importance of “democracy” to the region.That’s dumbed-down pablum for the masses and has literally nothing to do with the motivations of the (clinically insane) external power brokers actually driving the events on the ground and crafting the narrative that is faithfully scribed and re-told by the media. In fact, disturbingly often, the scribed narrative is exactly opposite of the truth. “

  4. ” እንደባንክ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ የወያኔ ባለስልጣናት ቤተሰቦች እና ዘመድ አዝማዶች በላኪነት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ገንዘብን ምንም አይነት ዋስትና ሳያሲዙ በአነስተኛ ወለድ እየወሰዱ የማይከፍሉ እና ሰነድ የሚያስጠፉ እንዲሁም ያለምንም ቀረጥ እና ታክስ ወደ ውጭ ሃገር ምርቶችን በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የኢሲያ ሃገራት ባንኮች ይዶሉታል:: የባለስልጣናት ቀጭን የስልክ ትእዛዝ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ኢሮዎች እና ፓውንዶች ከባንክ ይወሰዳሉ። ”

    You guys know that weyane, that always asks ferenjis for food aid, not because of insufficient grain production in Ethiopia,but in order to smear Ethiopia, exports millions of tons of grain or food to foreign countries ?

  5. I’m tierd to hearing you guys,,, complaining complaining ,,,about zerafi , gedai. Ayatochih yaqoyouh netsant techiroachew ayidelem. Mebtehen lemaskeber hagerhin kewirdet kemetifat lemadan mesewatineten yiteyikal! Le ant bayidersih lijochih yenetsanetin kaba atliqew semihn eiyteru yinoraluna hagerh Ethiopiam lezelalem mennor tichlalechina!!! Esti wendinetihn asay!!!!

  6. ውሸት ነው ሙሥናን ለመዋጋት ተብሎ የተዘረጋው መረብ ውሥጥ ላለመግባት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*