(በብአዴን/ኢህዴን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የጻፍኩት) የህወሓት ፈተና – ‹‹የታገልኩት፣ የቆሰልኩት፣ የሞትኩትም እኔ ብቻ ነኝ እና የታሪኩ ባለቤትም የትግሉ ውጤት ይበልጥ ተጠቃሚም መኾን ያለብኝ እኔ ነኝ››። ይህ ትርክት ጫፍ ሄዶ ሄዶ ኢዲሞክራሲያዊነት እና ጠባብነት የወለደው ኾኖ ወደ ትምክህተኝነት ሊያድግ ይችላል። ኣብዛኞቹ የዚህ ፈተና ሰለባ የኾኑ የድርጅቱ ኣባሎች ብ1993ቱ የድርጅቱ የውስጥ ትግል የተሸኙ ሲኾን የነሱ ደጋፊዎች እዚሁ የማሕበረሰብ ሚዲያ ላይ የሚያሳዩት ትምክህት አሁንም አለ። ድርጅቱ የዚህ አይነቱ አዝማሚያ ዋናው ፈተናው ሲኾን በቀጣይ የቀሩ ትርፍራፊ የማጽዳት ስራዉን አጠናክሮ የማካሄድ ሓላፊነት አለበት። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ እኩልነት በመቀበል የታገልነው በጋራ እና ለጋራ ጥቅም ነው በማለት እዚህ ለበቃ አብዛኛው አባሉን በዚህ አስተሳሰብ ዙሪያ ማሰለፍ ከቻለ ህወሓት ውጤታማ ይኾናል። ብአዴን፦ ያለፉ ስርዓቶች፣ በተለይ የአጼኣዊው የዘውድ ስርዓት፣ ናፍቆት። ይህ በእኩልነት ያለማመን የአንዳንድ የብአዴን ትልቁ ፈተና ነው። የጥንት ታሪኮች የአንድ ብሔር ይኾኑ ዘንድ የመመኘት ከዚህ በዘለለም የትምክህት ሃይሉ የሚያራምደው በአለፉት ስርአቶች የተፈጸሙ በደሎች የመካድ አዝማሚያ። ብአዴን የዚህ አይነቶቹ አባላት ሽኝቶ ብቻ ሳይኾን የተፈጠረው አዲስ የኢትዮጵያዊነት የእኩልነት ትርጉም አልጥም ብሏቸው ወደ ድሮ አመለካከታቸው በመኮብለል ብዙ አባላቶቹ እና አመራሮች ሳይቀር ከመስመሩ ወጥተዋል። አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛ ቀለማቸው በመሄድ ፓርቲዎች አቋቁመው ብአዴንን ዞረው ታግለዉታል። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ የጋራ ሀገር ነው ያለን የልፉት ስርዕእቶች ሁላችንንም በድለዋል። እነዚህ ስርዓቶች ላይመለሱ በተባበረ ክንድ ተወግደዋል። ስርዓቶቹን ለማስወገድ የአማራ ብሔር ተወላጆችም አኩሪ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ማስተማር […]

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ): የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች …

በሕወሓት የበላይነት የብአዴንና ኦሕዴድ አስረሽ ምችው – ፈንጠዝያ ባርነት እስከመቼ ? Read more »