በደቡብ አፍሪካ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገደሉ::ደቡብ አፍሪካውያን ለውጪ ዜጎች ያላቸው ጥላቻቸው አገርሽቶባቸዋል::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ አፍሪካ ደርባን የአይን እማኞችን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ እንግሊዘኛው ድህረገጽ እንዳለው ባለፈው ሳምንት ብቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን የውጪ ዜጎች ይውጡልን በሚሉ ደቡብ አፍሪካውያን መገደላቸው ታውቋል::ዮናስ ፍቅሩ ይባላል በደርባን ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ሲሆን ስድስቱንም ሟጮች ያውቃቸዋል::ሁሉም በ20ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ናቸው::እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካውያኑ በጠራራ ጸሃይ እንደተገደሉ ተናግሯል::ምም የዘረፉት የለም መተው በቀጥታ ገለዋቸው ሄደዋል ሲል ለምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ተናግሯል::
ተገኔ አቦዬ የሚባል በደርባን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባል ሁኔታውን በተመለከተ ለፖሊስ ሪፖርት ብናደርግም ፖሊስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል::አይሰማንም ሲል ተማሮ ተናግሯል::ገዳዮቹ በአገራችን የፈለግነው የማድረግ መብት አለን የሚሉ ሲሆኑ በየጊዜው ዘረፋ እና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን በውጪ ዜጎች ላይ ይፈጽማሉ::የኢትይኦፓያ ኤምባሲ ምንም ትብብር ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም ሲል ተገኔ ይናገራል::
ወንድሞቻችን ተገለው አይተናል::በሶስት ሊትር ነሽ ጋዝ ተደፍቶባቸው ተቃጥለዋል::ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ማንም የሚረዳን የሚያድናቸውም አላገኘንም ሲል የሚናገረው ኢትዮጵያዊው ተገኔ ለኢትዮጵያውያን የሚከራከር ይሁን ጥቃቱን የሚከላከልላቸው እስካሁን አላየንም ሲል ገልጿል::የአሜሪካ ድምጽ የደርባንን ፖሊስ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም::ከጥቂት አመታቶች በፊት ጀምሮ ደቡብ አፍሪካውያን የውጪ ዜጎች ይውጡልን በሚል ጥላቻቸው እየገለጹ ሲገኙ ጥላቻውን እስከ መግደል ማቃጠል እና መዝረፍ ዘልቋል::ደሃ የሚባሉት አብዛኛው ደቡብ አፍሪካውያን ስራዎቻችንን የውጪ ዜጎች ተቆታጥረውታል ሲሉ የውጪ ዜጎችን ወደ ማጥቃት ወንጀል አምርተዋል::#ምንሊክሳልሳዊ
