መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡

Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!

የተወገዘ የነበረው የተለመደ ሆኗል፡፡ ጉቦ መውሰድ ኃጢአትና ወንጀል መባሉ ቀርቶ ጉቦ አለመቀበል ጅልነትና ሞኝነት እየተባለ ነው፡፡ፀረ ሕዝብ፣ ስስታም፣ ስግብግብና በሙስና የተጨማለቁ ለግል ጥቅምና ክብር ሲሉ አገርንና ወገንን ከመሸጥ፣ ከመለወጥ፣ ከመካድና ከመርገጥ ወደኋላ የማይሉ ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ መቀመጥ የሌለባቸው፣ መሾምና መከበር የማይገባቸው ባለሥልጣናት እንደዚህ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሹሞችን ይዞ አገርን ከአደጋ ማዳን፣ ሕዝብን ከድህነት ማላቀቅና ፍትሕና ዴሞክራሲን ማስፈን አይቻልም፡፡

ይህን ሕዝብ ከድህነት ማላቀቅና ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን የሚሆነውና በተግባር የሚታየው፣ ሀቀኖቹ በሌቦቹ ላይ የበላይነት ሲያረጋግጡ ብቻ ነው፡፡ በተግባር ሀቀኞች በሌቦች ላይ የበላይነት ሊኖራቸው የሚችለው ደግሞ ሲታገሉና በትግሉም ዋጋ መክፈል ሊኖርባቸው እንደሚገባ አምነው ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡
በቃል፣ በንድፈ ሐሳብ፣ በመግለጫና በቃለ መጠይቅ የመንግሥት ሌቦች እንዳሉ መናገሩና ማውገዙ ብቻ የትም አያደርስም፡፡ እንቅፋት ናቸው ብሎ መግለጹ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመንግሥት ሌቦች ካልተወገዱ የሌቦች መንግሥት ይመሠርታሉ ብሎ ማመን፣ ይህ የሌቦች መንግሥት እውን እንዳይሆን ለመቅጣት፣ ለማስወገድና ለመጠራረግ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡

ሌቦችን ለማስወገድ ተቸገርን ብለው ሊያማርሩ አይገባም፡፡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ችግር የለም ነገ ከነገ ወዲያ እናስወግዳቸዋለን ተብሎ የሚተው ጉዳይም አይደለም፡፡ ሀቀኛው በተዝናና ቁጥር ሌባው እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ በገንዘብ ተከታዩን ይገዛል፡፡ በገንዘብ ኔትወርክ ይዘረጋል፡፡ በገንዘብ ከውጭ ጠላት ጋርም ሊተሳሰር ይችላል (ሌብነት ድንበር የለሽ ነውና)፡፡ በገንዘብ ሀቀኞችን የሚያስወግዱ ኃይሎችን በማሰማራት ሊያሸንፍ ይችላል፡፡ በገንዘብ የመገናኛ ብዙኀንን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡አቅም ያጣውን፣ ዕውቀትና ልምድ ያነሰውን በትምህርትና በሥልጠና ማጠናከር ይቻላል፡፡ ሌባና ወንጀለኛን ግን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ ብቻ ነው መፍትሔው፡፡በከፍተኛ የአገር ኃላፊነት በመንግሥት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን ማጥራት ነው፡፡ የሕዝብ፣ የአገር፣የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የሰላም ጠላቶችን ማስወገድ ነው፡፡ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

4 Comments on “መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡”

  1. The western world have shown us that they do not care about the Nation Ethiopia and her people.For as long as non Tigre Ethiopians die in Somalia to protect the interest of USA thats all it matters.The Tigre mercenaries must be destroyed in any means possible.They have to be eliminated before they would drag Ethiopia to chaos.We have to support G7 and EPPF as well as ESAT.At least through ESAT our poor people that have been stolen,terrorized,Dehumanized,arrested and humiliated by the Tigre mercenaries will get enough information how these mercenaries take advantage to be milliners while the rest of Ethiopians have to suffer through systematic destruction of our mother land.We have to support the Armed struggle that could destroy the Tigre mercenaries.G7 and EPPF should be seen not only as freedom fighters but also as a power that can stabilize the Nation in case the Tigre mercenaries would collapse of any type of civil disobedience at any time.Our people that have been affected by the drought are now migrating from their land to the nearest cities to survive.Its because the Tigre mercenaries hide the reality just because they had invited Obama and Diaspora where they have used millions of dollars for few days while our people had nothing to eat.These Tigre mercenaries could have come with a billion dollar of the 50 billion they have stolen and save our people but they do not care about our people.They came to liberate Tigray from the rest of Ethiopia and we should never expect them to reach for the rest of Ethiopians.I am Andargachew and ESAT is mine.Death to TPLF and Hodams.

  2. እንደሚታውቀው ሁሉ ወያኔዎች በተለያየ ደረጃ የሃገሪቱን ሃብት ያለ ጤያቂ እየዘረፉ እንደሆነ ግልጽ ነው::ከሃያ አራት አመት በፊት ባዶ እግራቸውን አገሪቱን የወረሩት ወያኔዎች በአሁኑ ግዘ የትላለቅ ፎቆች:ሆቴሎች:ፋብሪካዎች:እንዲሁም የባለ ብዙ ፋብረካዎች ባለቤቶች ሆነዋል::በተቃራኒው አብዛኝኣው ኢትዮጵያዊ በረሃብ እየተሰቃየ እየተሰደደ እያየን ነው::በአለፈው ሃይ አራት አመታት አንድም ዘራፊ ወያኔ በስርቆት ሲከሰስ ሲታሰር አይታይም ::ምክንያቱም ሌብነት የወያኔ ፖሊሲ እንጂ የሚያስጤይቅ ባለመሆኑ ነው::

    [Reply]

  3. እውነት ብለሀል ወንድም ይህ የወንበዴ ቡድን ወያኔ ቅጫም ቱሀን ቅማላቸውን ያራገፋብሽ እናት ሀገር ኢትዬጵያ አፍ አውጥታ ትፍረድባቸው የሌባ ፍርድ ቤት ምን ሊፈርድ ይችላልን።

    በሜክሢኮና ብራዚል ኮሎምቢያ ካሉት የእፅ ሚሊየነሮች ጋር እኩል የሚታይ ወንበዴዎች ናቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*