የብሔር ፖለቲካ በጣም ስስ (sensitive) ነው፡፡ በቀላሉ ተቆስቁሶ ብዙ ሊጓዝ ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ በኢሕአዴግ ዘመን፣ በብሔር ፌዴራሊዝም ከተከፋፈለች ወዲህ እንኳን የብሔር ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አላገኙም፡፡ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከ34 በመቶ በላይ ድርሻ አለው፡፡ (2007 National Census) ሆኖም የኦሮሞ …

በዻሳ ወይስ badhaasaa? Read more »

በአፍሪቃው ቀንድ የተከሰተው የድርቅ አደጋ አስከፊነት ቀስ በቀስ ሀቀኛውን ገጽታውን እያሳየ ነው። በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ዘገባ መሰረት፡ ግማሽ ሚልዮን ህጻናት በአሳሳቢ የረሀብ አደጋ የሚሞቱበት ስጋት ተደቅኖባቸዋል።

ላለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያና በሕዝቦቿ ላይ የተካሄደው ክህደትና ፖለቲካዊ ሸፍጥ ያደረሰው ማህበራዊና ሰብዓዊ ቀውስ ሞልቶ ፈሷል፡፡ ዜጎች ደረጃ ወጥቶላቸው ይረገጣሉ፤የሁላችንም አገር ለከሃዲዎችና ላገልጋዮቻቸው ገነት፣ ለሌሎች ገሃነብ ተደርጋ የስቃይና የመከራ ምድር ሆናለች፡፡ አቶ መለስ ፖለቲካቸውና ፖሊሲዎቻቸው ሁሉ አገርና ህዝብን አዘቅት እያወረደ …

“መቼ ይሆን የምናርፈው?”: የኦጋዴን ረሃብና ጭፍጨፋ Read more »

– ኩባንያው አራት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ያደርጋል የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የሚገኙ የማሌዥያ ኩባንያ በሆነው ፔትሮናስ ተይዘው የቆዩ የካሉብና የሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትና ሌሎች ስምንት የነዳጅ ፍለጋ ቦታዎች፣ ፔትሮትራንስ ለተባለ ተቀማጭነቱ በሆንግ ኮንግ ለሆነ የቻይና ኩባንያ ተሰጡ፡፡

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ የትምህርት ጥራት ከመምህራን ብቃት ጋር ተዳምሮ የአገሪቱ አሳሳቢ ችግር መሆኑን አስታወቁ፡፡

በየትኛው ምዕራፍና ቁጥር መሆኑ ለጊዜው ተሰወጠብኝ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ በወንድማችን ላይ መፍረድ ወይም ወንድማችንን መሳደብ እንደማይገባን ለማሳሰብ ‹ ወንድሙን ጨርቃም ብሎ የሚሳደብ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል› የሚል ወይም ወደዚህ የሚቀርብ ማስጠንቀቂያ እንዳለው የቤተ ክህነት ዳራ ያለው ሰው ማስታወስ አያቅተውም፡፡ ጥሩ ትምህርታዊ …

ወንድሙን ‹ጨርቃም› ብሎ የሚሳደብ…በይነጋል በላቸው Read more »

ሰሜን ተርቦ እነደዚያ ሲያልቅ፡ በድብቅ ነበር ማንም ሳያውቅ፡ ተብሎ ነበር ትላንትና፡ ዛሬም እለሆ እንደገና፡ ደገመ ሰለሰና። በንጉሡ በዚያ ዘመን፡ ደግሞ በደርግ ሲከወን፡ ሰለሰ አሉ በነ ወያን። ሲያወሳ ሲያወጣ ሲያወርድ፤ ያለፈውን አስተዳደር ጉድ፡ ሰለሰው እርሱም እነደገና፡ የነርሱን ግፍ አባዛና። ኦጋዴን ከመሐል …

ደገመ ሰለሰ-በሀሩር ባአረር በፍሬው አንተነሕ። Read more »

የ93 ዓመቱ አዛውንትና የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላ የልደት በዓል ሰኞ ሐምሌ 18 2011 እ.ኤ.አ በዚህ በደቡብ አፍሪካ በታላቅ ስሜት ነው የተከበረው፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ የዜና አውታሮች እና ዓለም አቀፍ የመገኛኛ ብዙሃን ለእኚህ ታላቅ አባት የእንኳን አደረሰዎ መልእክትና የመልካም …

ረጅም ዕድሜ ለማንዴላ! ረጅም ዕድሜ ለሰው ልጆች መብትና ነፃነት ለሚታገሉ ሁሉ!!! በፍቅር ለይኩን -ከደቡብ አፍሪካ Read more »

ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ፊት ቀርባ ጉዳይዋን ለማብራራት ባለፈው ሰኔ ወር በጠየቀችው መሰረት ትላንት ማክሰኞ የኢትዮጵያ፣ የሶማልያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ ተወካዮች በተገኙበትጉድይዋን ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ምክር ቤት ለማቅረብ ችላለች።ኤርትራ ብቻዋን ነበር ጉዳይዋን ለማቅረብ የፈለገቸው። ይሁና እንደ …

ኤርትራ ስለ ሶማልያ በሚደረጉ ስብሰባዎች እንዳትገኝ መታገድዋን አቶ የማነ ገብረአብ ገለጹ Read more »

ሳምንታዊው “ኢትዮጵያ በጋዜጦች” ዝግጅታችን -African Institute of Mathematical Science በኢትዮጵያ እንደሚመሰረት ተገለጸ -የአውቶብስ አገልግሎት በሀዋሳ ከተማ -በኢትዮጵያና በኬንያ የተቅማጥ በሽታ ገባ -በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ በሰሜን ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያደረሰው ጉዳት የሚሉትን ርዕሶች ይዞ ቀርቧል።

በዚህ ሳምንት ከወደ ሰሜን ሸዋ ባጭሩ እንዲህ የሚል መልካም ዜና ተሰምቷል። በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ የኢህአዴግን ስብሰባ አንሳተፍም ያሉ የኢህአዴግ አባላት የነበሩ መምህራን የ8 ቀናት ደመወዛቸው መቀጣታቸውና ከሐምሌ ወር ደመወዛቸው ተቀናሽ እንደሚሆን የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሳቸው። መምህራኑ ለደብዳቤው በቃል …

የወያኔ የአባልነት ደብተርን በመቅደድ ነፃነትን ማወጅ፤ ዛሬ!!! Read more »

ከዝግጅት ክፍላችን፤ በቅርቡ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ርሃብ አለ እንዴ ተብሎ ተጠይቆ ሳያንገራግር የሚከተለውን መልስ ሰጠ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ርሃብ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ነው”።  አለ ሌባ ጣቱን ወደላይ ቀስሮ። መለስ ዜናዊ ይህን መልስ በሰጠበት ወቅት ኦጋዴን ውስጥ ህጻናት፤ ጎልማሶችና …

መለስ ዜናዊ የወለደው ርሃብ!!! Read more »

የህዝባችንን መረጃ የማግኘት መብት በማፈን የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም እየተወራጨ ያለው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ፤በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ለተመለሰው የአሜሪካ ድምጽ የአሰተዳደር ቦርድ ያቀረበው ባለ 42 ገጽ አቤቱታ ለህዝብ ይፋ መሆኑን የግንቦት 7 ዜና ዘጋቢ ገለጸ። በወጣቱ የዲሞክራሲ አክቲቪስትና ጋዜጤኛ አበበ ገላው …

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከተቃዋሚዎች ይወግናል በማለት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ለአሜሪካ መንግሥት በማስረጃነት ያቀረበው ባለ 42 ገጽ አቤቱታ አፈትልኮ ለህዝብ ይፋ ሆነ Read more »

የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በውዴታ ግዴታ ገንዘብ እንዲለግሱ ከጠየቀ ወዲህ ፣ ተቋማቱም የተጣለባቸውን እዳ የከፈሉ ቢሆንም ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የከፈላቺሁት መጠኑ አነስተኛ ነው በሚል በድጋሚ እንዲያዋጡ ማዘዙን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ። …

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በአባይ ግድብ ግንባታ ሽፋን ዜጎችን መዝረፉን ቀጥሉአል፣ የግል ትመህርት ተቋማት በግዴታ የተጣለባቸውን ገንዘብ መክፈል አንችልም እያሉ ነው Read more »

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተደራጁ ሃይሎች የጦር መሳሪያን በመጠቀም ሰፊ የሆነ ዘረፋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየፈጸሙ መሆኑ ተደጋግሞ የተዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍል ሥር የሚገኘው ሲስኮ ላብራቶሪ …

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለው ዝርፊያ ተስፋፍቶ ቀጥሉአል፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምስት ኪሎ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሁለት ቤተ ሙከራዎች ባልታወቁ ሰዎች ተዘረፉ Read more »

ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስሪያ ቤት ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከተቀየረ በኋላ በርካታ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ከስራቸው እንዲሰናበቱ የተደረጉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እነኝህ ከስራ የተባረሩ ሰራተኖች ከነቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የጥቃቱ ሰለባ ሰራተኞች ገልጸዋል። አንዲት ለገሃር በሚገኘው …

ከስራ የተባረሩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሰራተኖች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ Read more »

በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ አንድና ስምንት ውስጥ ከ450 በላይ የንግድ ቤቶች ያለንግድ ፈቃድ ሰርታችሁዋል በሚል ምክንያት መታሸጋቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝን ኢሳት የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ የዘገበ ሲሆን ዘረኛውና ጨካኙ የወያኔ አገዛዝ የወሰደው ርምጃ ነጋዴዎቹን እጂግ ማበሳጨቱን ተያይዞ የደረሰው ዜና አመልክቷል። ከዚሁ …

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የንግዱ ማህበረሰብ ማዋከቡን ቀጥሏል፣ መርካቶ ውስጥ ከ450 በላይ ንግድ ቤቶች ታሸጉ Read more »

በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለገሰ ዓለሙ ከሁለት ሣምንታት በፊት ለስብሰባ ከፍትሕ ሚኒስትሩ ብርሃን ኃይሉ ጋር ለስራ በሚል አሜሪካ ሄዶ የነበረ ሲሆን ወደ ሃገር ሳይመለስ በዚያው መቅረቱን ለአገዛዙ ቅርበት እንዳለው የሚታወቀው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ …

የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ሃገርን እየጣሉ መኮብለላቸውን ቀጠሉ Read more »

ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በምርጫ 97 በህዝብ መተፋቱን ከተገነዘበ ወዲህ በመላው አገሪቱ የሚገኙትን አብዛኛውን የመንግሥት ሠራተኞች በሥራ ዋስትና እና የደረጃ ዕድገት ሥም እያስፈራራ አባል ያደረገ ቢሆንም አባልነታቸው ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ከመጣው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የሚታደጋቸው ሆኖ ባለመገኘቱ በርካቶች የአባልነት ግዴታቸውን …

ወያኔ በሥራ ዋስትና አስገድዶ የኢህ አደግ አባል ያደረጋቸው የመንግሥት ሠራተኞች ድርጅቱ የሚጠብቅባቸውን የአባልነት ግዴታ ላለመወጣት እያንገራገሩ ነው ተባለ Read more »

የአሜሪካንን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ በየትኛውም አለም ክፍል ካሉት አፋኝና ጨቋኝ የአምባገነን መንግሥታት ጋር ተባብሮ መሥራት የውጪ ፖሊሲው አካል የነበረው የአሜሪካ መንግሥት፤ ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ በአለማችን ላይ እያየለ የመጣውን የነጻነት ትግል ለመደገፍ በሚያስችል ሁኔታ እንዲሻሻል እርምጃዎች እየተወሰዱ …

የፕሬዝዳንት ኦባማ የዉጭ ርዳታ የማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነ አለም አቀፍ የጋራ ትብብር ድርጅት ተቋቋመ Read more »

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቀደም ሲል የጫካ ትግል ያካሂድ በነበረበት ወቅት አብረውት የነበሩትንና የድርጅቱን ጸረ አገርና ጸረ ህዝብ አቋም በሚገባ ከተረዱ ቦኋላ ለቀው በመውጣት ከተቃውሞው ጎራ የተሰለፉትን የቀድሞ ታጋዮች ማሳደዱን በመቀጠል አቶ አስገደ ገብረስላሴ በተከታታይ ለንባብ ባበቁአቸው መጻህፍት ምክንያት የቁም እስረኛ …

ህወሃት በትግራይ ህዝብና በመላው አገራችን ላይ የፈጸመውን ክህደት ለህዝብ ንባብ ያበቁ የቀድሞ ታጋይ እና አመራር አባል አቶ አስገደ ገብረስላሴ ትግራይ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኑ Read more »

በአፍሪካ ቀንድ ከአሥር ሚሊየን በላይ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ 4 ነጥብ 5 ሰው ለረሃብ ያጋለጠ ባለፉት ስድሣ ዓመታት ያልታየ የከበደ ድርቅ መከሠቱ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቃራኒው ምዕራብ ኢትዮጵያን የከበዱ የጎርፍ ሁኔታዎች እንደሚያሰጉት ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲን የጠቀሱ የሚድያ ዘገባዎች እንደሚሉት በሃገሪቱ …

የጎርፍ ማስጠንቀቂያ በምዕራብ ኢትዮጵያ Read more »

ዓለማቀፉ ማህበረ-ሰብ በአገራችን የተከሰተውን ድርቅ ስፋትና አጣዳፊነት ተገንዝቦ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን! የድርቅና ጠኔ ታሪክ የሃገራችን ታሪክ አካል ከሆነ አያሌ ዓመታትን አሰቆጥሯል፡፡ ዓመታትን ማስቆጠር ብቻም ሳይሆን በተከሰተባቸው ዓመታት ሁሉ ሕዝባችንን በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥፏል፡፡ እንስሳቶቻችን በገፍ ፈጅቷል፡፡ የአገራችንን ጥሪት በከፍተኛ ሁኔታ …

ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከከፋ የእርሃብ አደጋ እጅ ለዕጅ ተያይዘን እንታደግ!!(አንድነት ፓርቲ) Read more »

እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም  …

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ከብቶች እየሞቱ ነው Read more »

የኢሕአዴግ መንግሥት በዜጐች ላይ ሽብር በመንዛት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታወቀ፡፡ ኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመፍጠርና ሥልጣን ላይ በመቆየት ሐሳብ ላይ ግራ የተጋባ መሆኑን ዶ/ር መራራ ጉዲና ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ “በዜጐች ላይ ሽብር በመንዛት ሽብርተኝነትን ማስወገድ አይቻልም” በሚል ርዕስ …

ኢሕአዴግ በዜጐች ላይ ሽብር እየነዛ ነው ሲል መድረክ ወነጀለ (ሪፖርተር) Read more »

ባለሥልጣናቱ ትናንት በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሰሉ ባለፉት ስድሣ ዓመታት ባልታየው በዚህ ድርቅ ሣቢያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከ 11 ሚሊየን በላይ ሰው አፋጣኝ የሕይወት አድን እርዳታ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት …

ለቀንዱ ረሃብ ዓለምአቀፍ ምላሽ Read more »

የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ መነሳትና አለመነሳት የሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሆኖ ነው የሰነበተው። የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በበጀት መጓደል የገጠሙትን እክሎች ሊያስተካክል፤ የመንግስቱን ወጭ በመቀነስ ላይ ባለበት ወቅት፤ አገሪቱ ተጨማሪ ብድር የምታገኝበትና፤ ከዚህ ቀደመ የቆዩ ብድሮቿን ለመክፈል እንድትችል፤ ተጨማሪ ብድር …

የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች መካከል ያስነሳው ውዝግብ ቀጥሏል Read more »

ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ መግለጫዉ በሕዝብ ላይ ሽብር በመንዛት ሽብርተኝነትን ማስወገድ አይቻልም ብሏል።በሌላ በኩል በአሸባሪነት ተጠርጥረዉ የታሠሩት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የክስ ሒደት ለሌላ ጊዜ ተቀጥሯል

በምስራቅ አፍሪቃ በተከሰተው ድርቅ ሰበብ በብዙ ሚልዮን የሚገመት ህዝብ የሚቆጠር ህዝብ በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ የረሀብ አደጋ እንዳሰጋው የተመድ መስሪያ ቤቶች ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ የሚያወጡዋቸው መዘርዝሮች አስታወቁ።

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ) ሰሞኑን፣ አንድ ግሩም መፅሐፍ እያነበብኹኝ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ነው የወጣው፡፡ በዳንኤል ተፈራ የተፃፈና በዶ/ር ነጋሳ ጊዳዳ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዟል፡፡ አንድ ስሜቴን የኮረኮረውን ነገር ላካፍላችኹ ወድጃለኹ፡፡

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኘው ‹‹ብዝኀነትን ለዘላቂ ልማትና ማኅበራዊ ለውጥ መጠቀም ፕሮግራም›› የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) በኩል የስፔን መንግሥት በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ፕሮጀክት ነው፡፡