ደገመ ሰለሰ-በሀሩር ባአረር በፍሬው አንተነሕ።
ሰሜን ተርቦ እነደዚያ ሲያልቅ፡
በድብቅ ነበር ማንም ሳያውቅ፡
ተብሎ ነበር ትላንትና፡
ዛሬም እለሆ እንደገና፡
ደገመ ሰለሰና።
በንጉሡ በዚያ ዘመን፡
ደግሞ በደርግ ሲከወን፡
ሰለሰ አሉ በነ ወያን።
ሲያወሳ ሲያወጣ ሲያወርድ፤
ያለፈውን አስተዳደር ጉድ፡
ሰለሰው እርሱም እነደገና፡
የነርሱን ግፍ አባዛና።
ኦጋዴን ከመሐል ደቡብ፡
ሳልስ በድርቅ ሲሰለብ፡
በረሀብ ጦርነት ሲማገድ፡
ባሩር ባርረ ሲነድ፡
አልታየ አልተሰማ ጉድ፡
እንዳለፈው በሚስጥር ነበር፡
ሳልስም እንዲሁ በስውር።
መቼ ተጀመረ የረሀብ ሰቆቃ፡
ዛሬ ሊባል ይሆን ውሸት አያባቃ።
በጦሩ አፍሮ ሲያጋየው ቆይቶ፡
አፍን ደብቆ ካአለም ሌይቶ፡
ማንም እዳይሰም እንዳያይ ሰውሮ፡
ለአመታት ስቃይ እጋልጦ ከጉዋሮ፡
ዛሬም እንደገን ለማፈን ሲያቅተው፡
የስውሮን ሁሉ በግላጭ አወጣው፡
ባለም አደባባይ የሳልሱን ዘራው።
ረሀቡን ጥማቱን ስቃዩን መሞቱን፡
ለፖለቲካ ትርፍ ለስልጣን ማዋሉን፡
ተረስቶት እኮ ነው ጭራሽ እንዳይባል፡
የጥፋቱ ጠቢብ ሁሉንም ያውቀዋል።
ጦርነት ወለደ ድርቅና ረሀብን፡
መጥፎ አስተዳደር ምክንያቱ መሆኑን፡
ማንም አያጣውም ተጠያቂነቱን፡
በጊዜ ዳኝነት ለፍርድ መቅረቡን።
ተራበ ተጠማ ዛሬም እንደገና፡
ያለፈው ስቃዩ መች አነሰና።
በጦርነት ሰድደ መንደዱ ሳያንሰው፡
ሳልስ እንደገና በረሀብ አመሰው፡
የኦጋዴን ረሀብ የበዛ መከራው፡
እልገባህ ከሆነ የትላንት ወሎ ለው፡
ማስተውል ከከዳህህ የትላን ትግራይ ነው።
ወሎ ትጋረይ ትላንት፡
ኦጋዴን ባእለት፡
ታሪኩ ፈራጅ ነው፡
ሰውማ እንዳሻው፡
ፖለቲኩ በላው።
ባሐገር በሕዝብ ላይ ከዳር እስከዳር፡
የግፍ በደል ዝናም ዶፎበት እያደር፡
መጣለት ይለናል”ያእድገት መንግስት”
በድህነት ኑሮ ሕዝባችን ሲዋትት።
ሰምተህ ተገንዘበው እውነትና ሀቁን፡
እድገቱ ሲሰበክ ረሀቡ መስፈኑን፡
ነጣንት ሲውራ ጭቆና መብዛቱን፡
ዲሞክራሲ ሲባለ አፈና መሆኑን፡
ሰብእና ሲለፈፈ ሰውነቱ መሻሩን፡
የስርአቱ እርባና ከቶውም አልታን።
በከፋ ዘረፋ እያየን ማበጡን፡
እድገት መጣ መጣ መጣ መጣ ቢለን፡
ይህን ያህል ውሸት፡
ይህን ያክል ክህድት፡
አምንነ ከተቀበልን፡
እርሱ ምን አተፋ ቅሎቹ እኛ ነን።
በለቱ ስሌቱን ከኪሱ በመምዘዝ፡
ያመጣብን ጣያ ያመጣብን መዘዝ፡
ለትውልድ ሀላፊ ብዙ የሚያናቁር፡
አጥፍቶ ለማትፋት የቀመረው ቀመር፡
ከቶ ከርሱ በፊት ጭራሽ ላይቀበር።
አመታት አለፉ በፖለቲካ እፅ፡
ደንዝዞ አደንዝዞ ጥፋትህን ሰያንፅ፡
አልገባህ ከሆነ እንደቀበረልህ፡
የጊዜ ፈንጂውን በያረማመድህ፡
ንቃና ተራመድ ሰንቅ ለመንገድህ፡
አዘጋጅተህ ጠብቅ ብዙ ጉዞ አለብህ፡
ወገን ተበራታ አስላ ተሰብስበህ፡
የጥፋት አማእበል ከጥልቁ ሳይጥልህ፡
ሆ-ብለህ ባንድነት ድረስ ለወገንህ።
ሁሉም በየፊናው ከወቀሳ አይተርፍም፡
ከተጠያቂነት አንተም እንደነረሱም፡
ለስቃዩ መናር ለዚህና ለዚያም፡
ለድሉ መዘግየት ዳግሞ በታሪክም።
ከታሪክ ወቀሳ ከሀጢአት ደሞዝ፡
አንተም እንዳይደረስህ የጥፋቱ መዘዝ፡
አንድነት ዛሬ ነው፡
ንቃና ቀምረው፡
ለህዝቡ መዳኛ ታሪክን ድገመው፡
አብረህ ተነባብረህረህ መሰረቱን ጣለው፡
ድል የሕዝብ መሆኑን ከቶም አትዘንጋው።
ሕዝብ ተርቦ እንደዚያ ሲያልቅ፡
በስውር ነበር ማንም ሳያውቅ፡
ታሪክ እራስዋን ማስለስዋን ማወቅ፡
ከነገ ጥፋት ለመጠንቀቅ።
ሰላም ቢያገኝ ማረሱን፡
ላእለቱ ማምረቱን፡
ለነገውም ማዋሉን።
በጦርነት እሳት ማግዶ፡
እንዳይቀመጥ አሳዶ፡
ድርቅ ቢመጣ ተጠያቂ፡
አስተዳደር ያላዋቂ።
እውነቱ ይህ ነው ጠንቅቅ፡
ያዘነብህ በሕዝቡ ላይ ድርቅ፡
ባፈና ሞገድ እንዲያልቅ፡
በሰላሙ ስትሸምቅ፡
በክፉ አስተዳደር ዶልተህ፡
ህዝቡን የማገድህ አንተው ነህ
ማንም ምንም ይቅር ላይልህ።
ጦርነት ረሀብ በሽታ፡
በጠነሰሰው ላይፈታ፡
መፍትሄ ላይዎን እውነቱ፡
ካልተቆረጠ እትብቱ፡
የጥፋት እልቂት አዙሪቱ፡
ሕዝብ አይሽርም በከንቱ።
በሁሉም አቅጣጫ በውርደት፡
ሲሰናበት በታሪክ ሂደት፡
ሲያልቅ አያምር የማታ ማታ፡
አንተም እንዳለፉት በተራህ፡
ከታሪክ ትቢያ ወደቅህ፡
ሕዝብ ተርቦ እንደዚያ ሲያልቅ፡
በስውር ነበር ማንም ሳያውቅ፡
እንዳለፉት መድገምህን እወቅ፡
አንተም በተራህ ተጠየቅ።
አልነበረም አልተሰማም፡
በሐገር ታሪክ አልታየም፡
የዚህ አይነት ሸፍጥ ውሸት፡
እዲህ ያለ ክህደት፡
ሕዝብን ሁሉ የሚያስት፡
በጦርነት በሽታ ሞት፡
ታሪግ ሐገርን ለውርደት፡
ባእልቂት ሰቆቃ የሚሞግት።
ነግረናል ይኸው ከጥዋቱ፡
ሐገርን በጥፋት ሳትፈቱ፡
መላ ለሕዝቡ ባንድለት፡
ቀኑ ሳይጨልም በፊት።
ዛሬም እንዳለፈው ድርቅ ሰልሶ፡
የረሀብ አለንጋ ስቃይ ተላብሶ፡
ተፈጀ ሰዉ እንስሳት፡
በውሀ ጥም ነዶ ጠኔ ግሳት፡
አሁንም እንአደለፍው ተቀጣ፡
አወይ መከራ አወይ ጣጣ።
ቢያስብልህ ኖሮ ላንተ ቢቆምልህ፡
ለጦርና ረህብ ለበሽታ ገልጦህ፡
የመከራ ዝናም ባላዘነበብህ፡፡
በስቃይህ ዋሽቶ አፈና ጥሎብህ፡
ሌላው እንዳያውቀው ከቶ እንዳይደርስልህ፡
ሞትን በያይለቱ ደግሶ ባልፈጀህ።
ስደቱን አየነው፡
አጥንት ተሞዋገተው፡
እልቂቱን ታዘብነው፡
ተዘርቶ በሜዳ በጋመ በረሀው፡
ወገን ስቃይህን ማነው ያሰታወለው?
ቀን ተሌት ተጉዞ ጠብታ ፍለጋ፡
ተነድቶ ተግዞ ህዝብም እንደመንጋ፡
ሲቃትት ይታያል አያ በዘመንህ፡
ከናለፉት ሁሉ በምኑ ተሻልህ፡
እስከናካቴውም ጭራሹን የባስህ።
ረሀብም ጦርነት ቶርም ረሀብ ሆኖህ፡
መግቦህ ነበረ አንተንም በቀየህ፡
ይህን ሰታሰልስ እነደምነ አስቻለህ፡
በረሃብ ጦርነት የረሃብ ጦር ከሆነህ፡
እርሱ ካደረገው በምኑ ተለየህ።
ታሪክ መልሳ ሰልሳ፡
ለሰዎች ዘር ስቃይ ለትውልድ አበሳ፡
የዘንድሮ ነገር መቼም አትረሳ።
ሕዝብ ተርቦ እንደዚያ ሲያልቅ፡
በስውር ነበር በድብቅ፡
ታሪክ እራስቃን ሰለሰች፡
የበደልን በደል ገለጠች፡
ባደባባይ አወጣች።
ጊዜ አንችም እንደገና፡
ለልጆችሽ ዋይና፡
ነጻ ይውጡ ሕዝብ ሁሉ፡
እነርሱም እንደገና ሲድሉ፡
በተራቸው ይፈርዳሉ።
የትም ቢሆን መቼም፡
ረሃብ ድርቅ አንድ በቦታም፡
የግፍ መግለጫ የበደልም፡
በመልካም ስርአት አይታይም፡
ቢከሰትም ድርቅ የተፈጥሮ፡
በመልካም ስርአት ወትሮ፡
ሕዝብ አይራብ አይጠማም፡
ላእልቂት ማገዶ አይቀርብም።
ስለዚህ ስማ ተገንዘብ፡
የጥፋት ስርአት ገደብ፡
ሕዝብን በረሃብ መስለብ።
የሁሉም ሂደት መሰረቱ፡
አስተዳደር ብልሀቱ፡
ስተሀል ክደሀል በያይለቱ፡
መሰከረ የስራህ ታሪክ በወቅቱ።
አመጸኛን ክፋት ለጥፋት፡
ዛሬም እንደሚፈልጋት፡
ምስክር አያሻም ይኸው፡
የጥፋትህን ብድራት ክፍለው፡
በሰማይም በምድር፡
መቸም ቢዘገይ ፍረድ አይቀር።
መትፎ አስተዳደር ጦርንተ ይወልአል፡
ሰላሙን ያጣ ሕዘብ ከምርት ይዘናጋል፡
ረሃቡ ስደቱ በሽታም ይበዛል፡
መከራው በዝቶብት የነገውን ያጣል፡
በበደል ላይ በደል ለልቂት ይጋለታል፡
ካዙሪትም ገብቶ መግቢያ መውጫ ያጣል፡
የዚህ አይነት ሂደት
መጨረሻው ጥፋት።
ሰምተህ አላደመትህ፡
አይተህ አላሰታወልህ፡
የጥፋት አዙሪት ተብትቦ ጠፈረህ፡
አዘሮ አዙሮ ጠልፎ እስኪጥልህ፡
በውድቀት ላይ ውድቀት ውርደት አመረትህ፡
ብድራቱን ክፈል እዳውም በዛብህ።
የወገንህ በደል አንተም ካልተሰማህ፡
የኛኛው መከራ ቆርቆሮ ካልከፋህ፡
ቁጭትህም በዝቶ አይተኸው ካለፍህ፡
አንተም ከበዳዩ ትደበለዋለህ፡
ባባሪ ለትፋት ስለመጠራትህ፡
አትጠራመረ ትወቀሰዋለህ፡
በታሪክ ማህደር አንተም አልተረፍህ፡
ነግ በኔ እነዲሆን ማንም አያሰጠናህ።
ድሀ ካለቀሰ ፍትህ ከተዛባ፡
ምህረት አያገኝም የጥፋቱ አምባ፡
ጠጥቶ መቅረቱ የድሃውን እንባ፡
ደሙን ካዘራበት በወጣ በገባ፡
አምላክን ያሰቆጣል መከራ ይበዛል፡
በዚያ የፍርድ ቀን የሞት ሞት ይሆናል።
በሰላሙ መንግድ መራመድ እያለ፡
በቅንነት መንገድ መገስገስ እያለ፡
በሆነ ባልሆነው ጦሩን ከሰበቀው፡
በራሱ ፈረድ ማንም አያድለው።
ከላይና ካተች ከፊቱም ከሁዋላም፡
በቀኝም በግራም በዙሪያ ገደቡም፡
በያይነቱ ሁሉ እንደተወጠረ፡
እንዴት ሳይታየታው ሳይሰማው ቀረ!!!!
ብረቱ ቀይ ነው ቅረጽ ለማረሻ፡
ጠንቅቀህ ተራመድ ድልን የምትሻ።
በአርረ በአሩር ሲታመስ እያየህ፡
በድርቅ በበሽታ ሲማገድ እያየህ፡
በስደት በሲቃ ሲዋትት እያየህ፡
ጉዳይህ ካለሆነ ምንም ካልተሰማህ፡
ነገ ባለተራ ባለጣው አንተነህ።
ቁልቁል እየሄደ አደግን ይለናል፡
በረሃብ ሲታለብ ጠገበ ኢለናል፡
ሕዝብ እየረገፈ ሞት የለም ይለናል፡
ባአሩር ሴያነደው ሰላም ነው ይለናል፡
አንደበቱን ከፍቶ ነጻል ነው ይለናል፡
ውሸት እውነት ሆኖ አደባባይ ወጥቶአል፡
ዘመነ ገርንቢጥ ሌላ ምን ይባላል፡
ቅልም ድንካይ ሰብሮአል፡
የታቹ ላይ ሆንዋል።
ምስራቅን በመዝፈን ምእራብ ይታያል፡
ከምስራቅ ሲፈለግ ከደቡብ ይጠፋል፡
ተመለሰ ሲባል የትም አይገኝም፡
ርእዮቱም ባዶ ወና ምንም የለም፡
ከመገላበጡ ጭራሹን አረረ፡
እየባሰ ሄድ ነገሩም መረረ፡፡
አንድ ቀን ያለውን፡
ዳግም ላይደግምልን፡
እርግማን ይመስል ንግግሩ ሁሉ፡
የተባለው ቀሬቶ ያዙሪት መዋሉ፡
የተቃረነውን ስናይ በሽቁልቁሉ፡
የላዩ ወደታች የታቹ ወደላይ፡
የተገላቢቶሽ ያልሆነውን ስናይ፡
ስንት አመት አለፍ የወሬ መሰንቆ፡
እውነትን በውሸት ተክቶ ደብልቆ።
አወይ አነቺ ጊዜ፡
እንዲሁ በዋዜ፡
የማይሆን ሲከወን፡
የሚሆን ሲኮነን፡
እንደምን አለፍሽ እስኪ ተናገሪ፡
ከክህደት እርምጃ አንቺም አታብሪ።
ሕዝብ ተርቦ እነደዚያ ሲያልቅ፡
በድብቅ ነበር ማንም ሳያውቅ፡
ተብሎ ነበር ትላንትና፡
ዛሬም እለሆ እንደገና፡
ሰለሰ ደገመና።
ፍሬው አንተነሕ።
07 20 2011