በተለያዩ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ላይ ከሕግ አግባብ ውጭ ውሳኔ እንደተወሰነባቸው በመግለጽ ቅሬታ ባቀረቡ 246 ባለጉዳዮች ምክንያት፣ በሥነ ምግባር ጉድለት በ

ፍኖት- የጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል ንብረቶች እስከአሁን አልተመለሱም
ባለፈው መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም በ “ሽብር” ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዕለቱ ሲያሽከረክሯት የነበረች የቤት መኪና እና መተዳደሪያቸው የሆነውን የቤት ኪራይ ገንዘብ እንዲመለስላቸው ጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል ቢጠይቁም እስከአሁን እንዳልተመለሰላቸው ገለፁ፡፡
ወ/ሮ ሰርክዓለም ንብረቶቹ በተያዙበት ማዕከላዊ እስር ቤት ሄደው የመኪናውን ሊብሬ በእሳቸው ስም እንደሆነ ለማስረጃነት ቢያቀርቡም “ከአንቺ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY(UDJ)
ቁጥር፡-አንድነት /437/2ዐዐ4
ቀን 15/01/2004 ዓም
ግልጽ ደብዳቤ
ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በሽብርተኝነት ስም የታሰሩ አባሎቻችንና ሌሎች ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው ስለመጠየቅ፣
በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በግልጽ እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በሕገ-መንግሥቱ በተደነገገው የመደራጀት መብት መሠረት ሕጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እውን […]

አቶ ኦልባና ሌሊሳ በምዕራብ ሸዋ ጨሊ ወረዳ በ1966 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም በተወለዱበት አካባቢ አጠናቀው ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመግባት በግብርና ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡ ከዚያም በመንግሥት ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በሚተዳደር መስሪያ ቤት ተቀጥረው ለዓመታት አገልግለዋል፡፡ በማታው መርሐ ግብር በአምቦ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል እየተማሩ እንደነበርና በተደረገባቸው የፖለቲካ ጫና ምክንያት ሥራቸውን በፈቃዳቸው […]

ወ/ት ሊዲያ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝደንት የአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ልጅ ናት፡፡ በአባቷ ዙሪያ ባልደረባችን ብዙአየሁ ወንድሙ አነጋርሯታል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡
አባትሽ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ በመጀመሪያ አቶ ዘሪሁን የት ተወለዱ?
ወ/ት ሊዲያ- ዘርዬ የተወለደው እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ሥፍራው መርከቶ የሚባል አካባቢ ነው፡፡
ስለ ትምህርታቸው አጠቃላይ ሁኔታ ብትገልጪልኝ […]

ሽብርተኝነት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ጀምሮ እየጎላ የመጣ አደገኛ ክስተት ነው፡፡ አደገኛነቱ በግልጽ የታየው እ.ኤ.አ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም በኒውዮርክ ከተማ የንግድ ማዕከል ላይ በደረሰው ጥቃት ነው፡፡ በዚህ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠር ህይወት ጠፍቷል፡፡ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዓለም ሕዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል ድንጋጤና የመንፈስ ጭንቀት ፈጥሯል፡፡
ተንታኞች ሽብርተኝነትን በተለያየ […]

ከሽብር እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩትን ጋዜጠኞች ሁኔታ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) ተወካዮች በአካል ተገኝተው እንደጎበኙ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ህብረት (ኢብጋህ) አስታወቀ።
ዋና ጽህፈት ቤቱ በቤልጂየም ብራሰልስ ያደረገው ይኸው ፌዴሬሽን ልኡካኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልክበት ዋንኛ ዓላማ ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና አውሮፓውያን ጋዜጠኞች የሚደረግላቸውን አያያዝና የታሰሩበትን ትክክለኛ […]

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሰሞኑን መንግሥት በአሸባሪነት የጠረጠራቸውን ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ማሰሩ ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ እና በሌሎች ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ ሱራፍኤል ግርማ ከቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት እና ከወቅቱ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)ሊቀ-መንበር ከሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ቆይታ አድርጓል።
የሰሞኑን የእስር ሂደቶች ፓርቲው እንዴት ነው የሚመለከተው?
በተለያዩ ጊዜያት እንደገለፅነው፣ ፓርቲያችን ለፍትህና ለዴሞክራሲ ይታገላል፤ ሕገመንግስቱ ያጎናፀፈንን መብቶች […]

‹‹ … የዓለም ሰላም ጠበቃዎች፣ የጋዜጠኞች መብቶች አስከባሪዎች፣ የዴሞክራሲ ሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ነን ለሚሉትና በውጭ ሀገር የተቃዋሚዎች አፈ ቀላጤዎች በመሆን በማገልገል ላይ ለሚገኙ አንዳንድ ኃይሎች ሳይንበረከክ፣ መንግሥት የአመፅ ጥሪ የሚያቀርቡትን ኃይሎች ሀይ ሊላቸው ይገባል … ››
ከላይ የሰፈረው ጥቅስ የተወሰደው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ለንባብ ከበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 3 ነው። ምንጣፍ የሚያክለው አዲስ […]

– የሆስተሷን ዓይኖች ያጠፋው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ‹‹በመጠጥ ሞቅታ ተገፋፍቼ ነው፤ ንብረቴን ለማስጠበቅ ዋስትና ይፈቀድልኝ›› የሆስተሷ የቀድሞ ባለ…

ቢሯችን እስኪጸዳ ድረስ በር አካባቢ ቆም ብለን ብሶታችንን ማውራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም የለመድነው ነገር ሆንዋል፡፡ እናም ዛሬ ጧት እንደልማዳችን ወደ አራት የምንጠጋ አለቃና ምንዝሮች ባንድነት ቆመን ስለኢትዮጵያና ስለዓለም ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ማውራት ያዝን፡፡ የኔን ጫጫሪነት ማንም ያውቃል ብዬ አላስብም፡፡ ሁላችንም እየፎገላን በተለይ ስላገራችን አሳሳቢና አስጨናቂ ሁኔታ ማውራታችንን ቀጠልን፡፡ የሚገርመው ነገር ማንኛችንም ብንሆን ለፖለቲካና […]