በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አወጡ

እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ በነፃ ፕሬስ ላይ በሚደረገው ጫና፣ እስርና እንግልት ምክንያት በስደት ላይ የሚገኙ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች በ’ሽብርተኝነት’ ስም በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ ላይ የተፈጸመውን እስር አወገዙ።