የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሥነ ምግባር ጉድለት አሥር ዳኞችን ከሥራ አሰናበተ
በተለያዩ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ላይ ከሕግ አግባብ ውጭ ውሳኔ እንደተወሰነባቸው በመግለጽ ቅሬታ ባቀረቡ 246 ባለጉዳዮች ምክንያት፣ በሥነ ምግባር ጉድለት በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንስፔክሽን ቡድን የተከሰሱ አሥር ዳኞችና አራት የሕግ ኦፊሰሮች ከሥራቸው ባለፈው የበጀት ዓመት መሰናበታቸውን፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡