የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተወካዮች ለአስተዳደሩ ቅሬታዎችን አቀረቡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የከተማዋ ማኅበራት ተወካዮች ጋር ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው ስብሰባ፣ በከተማው ውስጥ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የኑሮ ውድነት መባባስና የመኖርያ ቤቶች ችግሮች እንዳሉ ቅሬታ ቀረበለት፡፡