የአፍሪቃ ሁለተኛ ነጻነት?

ከተቋቋመ ሶስተኛ አመቱን የያዘዉ ኢትዮጽያ ጀርመን ፎሩም ኤፋዉ የተሰኘዉ ድርጅት ከትናንት በስትያ ሃሙስ ምሽት በኮለኝ ከተማ «የአፍሪቃ ሁለተኛ ነጻነት? » በሚል አንድ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዉይይቱ በአፍሪቃ ስላለዉ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት እድገት ላይ ሃሳብን አንሸራሽሮአል።