የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ሪፖርት ኢትዮጵያን በመልካም አስተዳደር አነስተኛ ደረጃ ሰጣት

በየዓመቱ የአፍሪካ አገሮችን የመልካም አስተዳደር ደረጃን ይፋ በማድረግ የሚታወቀው የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ  በመልካም አስተዳደር ረገድ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይፋ አደረገ፡፡

ባለፈው ሰኞ በለንደን ይፋ ባደረገው እ.ኤ.አ. የ2015 የአፍሪካ አገሮች መልካም አስተዳደር ደረጃ ከ54 የአፍሪካ አገሮች 21 የሚሆኑት በመልካም አስተዳደር ዝቅጠት እንዳሳዩ ጠቁሟል፡፡ 

ባለፉት አራት ዓመታት ከአንድ እስከ አሥር ከተቀመጡት መሪ አገሮች መካከል ግማሽ ያህሉ ብቻ መሻሻል እንዳሳዩ የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ እ.ኤ.አ. ከ2011 በኋላ የአፍሪካ አገሮች በመልካም አስተዳደሩ ረገድ የተወሰነ መሻሻል በጥቅሉ በማስመዝገብ ባለፈው ዓመት 50.1 ዕድገት ማስመዝገባቸውን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

‹‹የአፍሪካ አገሮች ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው ሁኔታ አንፃር ዛሬ ጤናማና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ቢሆንም፣ የ2015ቱ ሪፖርት እንደሚያሳየው ወሳኝ በሆኑ መስኮች የታየው መሻሻል በተጠበቀው ደረጃ አልተመዘገበም ወይም በተቃራኒው ተፈጽሟል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጥሩ የመሻሻል መስመር ላይ የነበሩት ጥቂት አገሮች ሳይቀር እየተንገዳገዱ መሆናቸው የማስጠንቀቂያ ደውል ሊሆነን ይገባል፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን የገለጹት የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ዶ/ር መሐመድ ኢብራሒም፣ ሁሉንም የአፍሪካ አገሮች ያማከለና ቀጣይነት ያለው መሻሻል በሁሉም መስክ ሲመዘገብ ብቻ የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ብሩህ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ከአንድ እስከ 20 ደረጃን ይዘው ከሚገኙት መሪ አገሮች መካከል የመጀመሪያዎቹ አምስት አገሮች እ.ኤ.አ. በ2015 ሪፖርት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ መሆናቸው ሲጠቆም፣ ከእነዚህም መካከል ሴኔጋል ከነበረችበት የ9ኛ፣ ኬንያ ከነበረችበት የ14ኛ፣ ሞሮኮ ከነበረችበት የ16ኛ፣ ሩዋንዳ ከነበረችበት የ11ኛና ቱኒዝያ ከነበረችበት የ8ኛ ደረጃ ተነስተው ወደ መጀመሪያዎቹ አምስት አገሮች ተርታ መካተታቸው ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ ኢትዮጵያ በጠቅላላው የመልካም አስተዳደር ግምገማ ከአሥሩ የመጀመሪያዎቹ አገሮች ተርታ ውስጥ የተካተተች ቢሆንም፣ በአዲሱ ሪፖርት አጠቃላይ ውጤቷ 48.6 በመቶ ነው፡፡ ይህም ከአፍሪካ አገሮች መካከል 31ኛ ደረጃን እንድትይዝ ሲያደርጋት ከቀጣናዋ ደግሞ 5ኛ አድርጓታል፡፡ ከአራቱ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር እመርታ ከሚታይባቸው ዘርፎች መካከል ሕዝባዊ ተሳትፎና ሰብዓዊ መብት፣ የሰው ሀብት ልማትና በተለይም ደኅንነትና የሕግ የበላይነት በቀዳሚነት ለምዘና የሚቀርቡ መሆናቸውን የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ በደኅንነትና በሕግ የበላይነት ኢትዮጵያ በአኅጉሩ 26ኛ ደረጃ ሲኖራት በምሥራቅ አፍሪካ ደግሞ 5ኛ መሆኗን ያሳያል፡፡ በዚህ ዘርፍ 13.8 የመሻሻል ዕድገቷን እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ ጠብቃ ብትገኝም፣ በአገር ውስጥ የእርስ በርስ ግጭቶችና በድንበር አካባቢ በሚታዩ ግጭቶች የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ታክሎበት ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በአገር ውስጥ በሚፈናቀሉ ዜጎችና በውጭ አገሮች የፖለቲካ ጥገኝነት በሚሹ ዜጎች ቁጥር ረገድ ሲታይ ግን፣ ደካማ አፈጻጸሞች መኖራቸውንም ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በግለሰብ ደኅንነት ረገድ በአኅጉሩ 12ኛ ደረጃን እንደያዘች የሚያሳየው ሪፖርት፣ በዚህ ንዑስ ዘርፍ በተለይም በብጥብጥና ወንጀል እንዲሁም በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ከአኅጉሪቱ በቀዳሚነት እንድትቀመጥ የሚያደርጋትን ሥራዎች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ መሥራቷን የሞ ፋውንዴሽን የ2015 ሪፖርት ያስረዳል፡፡ በአንፃሩ በሕዝባዊ ተሳትፎና በፆታ እኩልነት አገሪቱ ዝቅተኛውን ደረጃ መያዟ ብቻ ሳይሆን፣ ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ዝቅጠት ማሳየቷም ተመልክቷል፡፡ በዚህም ዘርፍ በሕዝባዊ ተሳትፎ ከአኅጉሩ 39ኛ ደረጃን ስትይዝ ለዚህም በዋነኝነት እንደማሳያ የቀረበው ፍትሐዊና ነፃ የሆነ ምርጫን የማካሄድ አቅሟ በኔጋቲቭ (-11.1) የተመዘገበ መሆኑ ታይቷል፡፡ በሴቶች ላይ በሚደርስ አድልኦና ጥቃትም አገሪቱ ኔጋቲቭ (-25.00) ያስመዘገበች መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሪፖርቱን ይፋ መሆን ተከትሎ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ከተዘገቡት ጉዳዮች መካከል ኢትዮጵያን ያካተተው የቀዳሚዎቹ አሥር አገሮች ዝርዝር፣ በአፍሪካ መፃኢ ዕድል ከፍተኛ ሚና የሚኖራቸው አገሮች መኖራቸው ነው፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ በብሔራዊ ደኅንነት፣ በመረጃ ነፃነት፣ በማኅበራዊ አለመረጋጋትና መንግሥትን ያማከለ ግጭቶችን የመፍታት፣ የሥልጣን ሽግግርና የሙስና ወንጀልን ከመከላከሉ ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው መሻሻል እንደሆነ ሜይል ኤንድ ጋርዲያን አፍሪካ የተሰኘ ድረ ገጽ አስፍሯል፡፡ ኢትዮጵያ ይፋ በሆነው አዲሱ ሪፖርት በአጠቃላይ ውጤት በ31ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ብዙ የሚጠብቃት የቤት ሥራ እንዳለ የሚጠቁም መሆኑን፣ ከላይ በተጠቀሱት ዋና ዋና የመሻሻል ዕርምጃዎች ታግዛ ደረጃዋን ልታሻሽል እንደምትችልም ግምት መኖሩ ተጠቁሟል፡፡ እንደ አገር ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር እጅግ በጣም መሻሻልን ያሳየች አገር ሆና ስትገኝ፣ በአንፃሩ ወጣቷ ደቡብ ሱዳን በከፍተኛ ዝቅጠት የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች፡፡   

የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን በሱዳናዊ ብሪታኒያዊ ቢሊየነር ዶ/ር ሞሐመድ ኢብራሒም የተመሠረተ ሲሆን፣ በአፍሪካ በመልካም አስተዳደርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያደርግና የተለያዩ ስኬታማ የሥራ ውጤቶችን የሚደግፍ ድርጅት ነው፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ በዚህ ሥራ ላይ ሲገኝ መቀመጫውም ለንደን ነው፡፡ 

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰከን ያለ እና ረጋ ያለው ወዳጅ ይፈልጋል::በፈላ ሰአት ሁሉ በስሜት መነዳት በፕሮፓጋንዳ መደበላለቅ ትልቅ አደጋ ያስከትላል::እኛ የለውጥ ሃይሎች ማለት ከራሳችን እና ከባለፈው ሂደቶቻችን መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች እንደሆንን እዚህ ደርሰናል::የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ ምርጫውን አሸነፍኩ …

ወያኔ/ኢሕአዴግ በውይይት ያምናል ብሎ ማሰብ መርዝ እንደመጠጣት ይቆጠራል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

አንዱዓለም ተፈራ

መከወኛ ሃሳብ፤

ዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው፡፡ ዘረኛው እና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከልዩ ኃይል እና ከመከላከያ ተመርጦ የተውጣጣ ሰራዊት በላይ አርማጭሆ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ማለትም በሙሴ ባንብ በጃኒካው፣ በገንበራ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ያሰራጨ ሲሆን ከሦስቱ ክፍሎች የተጣመረው ኃይል በየገበሬው መንደር ተሰግስጎ በማሸበር በመሳሪያ […]

ገዳሟን ለችግር የዳረጉት ጥበቃና ክብካቤ እየተደረገላቸው፣ ሰበካ ጉባኤው እንዳይሠራ ተደርጓል ለጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርት ለማቅረብ ጽ/ቤቱ ቢጠየቅም ሌላ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ተካሒዷል የገዳሟ ሒሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲጣራ በፓትርያርኩ የተሰጠው ትእዛዝ ተግባራዊ አልኾነም ፓትርያርኩ፣ ወደ ተግባራዊ የፀረ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ርምጃ እንዲገቡ ተጠይቋል *          *          * በ7 ወራት ሒሳብ የቅድመ ኦዲት ዳሰሳ ብቻ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ …

አቶ ሬድዋን ሁሴን በሃሰት ሲምሉለት የነበረውን ወንበር አጥተዋል።… ☞ ሃይለማርያም ከኒውዮርክ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያቸው እንዳይወጡ ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገዋል።… ☞ ጥያቄ የሚያበዙት አቶ አለማየሁ ተገኑ እና አቶ ሶፊያን አህመድ ከአሽከርነት ቦታቸው ተነስተዋል።… ☞ ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል። . የሕወሓት አሻንጉሊት የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ በትናንትናው እለት ባቀረበው የቸብ ቸብ ካቢኔ መሰረት ሕወሓት የጦር […]

ብዙን ግዜ እራሴን ኢትዮጲያዊ ማለት ምን ማለት ነው ብዬ ጠይቄያለው፡፡ ኢትዮጲያዊ ማነው? ማነው ባለአገር ?እንዴትስ ነው ይምንለየው?ሃይማኖቱስ ምንድን ነው?ብሔሩስ ምንድን ነው?ወይስ ብሔር የለውም?ምን ሙዚቃ ነው የሚያዳምጠው? ቋንቋውስ ምንድን ነው? በሚሉ ጥያቄዎች እራሴን አጨናነኩና መልስ ከሆነኝ ብዬ ኢትዮጲያ ተብሎ በሚወራበት ሁሉ …

ኢትዮጵያዊነት ማለት? ( በያቤፅ ካሳ ግችሌ ) Read more »

ሰማያዊ ፓርቲ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ::የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ውይይት ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል::ሰማያዊ ፓርቲ ከትራንስፎርሜሽን ረቅቅ ዕቅድ በፊት ለመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ፡፡ መንግስት መስከረም 28 እና 29/2008 ዓ.ም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ለመወያየት …

ሰማያዊ ፓርቲ በወያኔ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውይይት ላይ እንዲሳተፍ የቀረበለትን ጥያቋ ውድቅ አደረገ:: Read more »

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ትምህርት ሚኒስቴር አንድ ሺሕ ሞተር ብስክሌቶችን ለመግዛት ያወጣውን ጨረታ አገደ፡፡ ኤጀንሲው ጨረታውን ያገደው መስከረም 18 ቀን 2008 ዓ.ም.

ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ ጨረታው የታገደው በጨረታው ተሳታፊ የሆነው አግታ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት በማግኘቱ ነው፡፡

አግታ መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ለመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ቅሬታውን በደብዳቤ አቅርቧል፡፡ አግታ ባቀረበው አቤቱታ ትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥትን የግዥ አዋጅ በተፃረረ መልኩ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ኩባንያ ሥራው መሰጠቱን ተቃውሟል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰባት ወራት በፊት አንድ ሺሕ ሞተር ብስክሌቶች ግዥ ለመፈጸም ጨረታ አውጥቶ ነበር፡፡ በጨረታው አራት ኩባንያዎች ቢሳተፉም፣ አንዱ ኩባንያ በቴክኒክ ምክንያት ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ተደርጓል፡፡ የተቀሩት አግታ፣ ሐግቤስና በላይ አብ ሞተር ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 

አንድ ሺሕ ሞተር ብስክሌቶች ለማቅረብ አግታ 37 ሚሊዮን ብር ሲያቀርብ፣ ሐግቤስ ኩባንያ ደግሞ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ አቅርቧል፡፡ የአግታ ኩባንያ ቅሬታ ከዚህ የመነጨ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ሞተር ብስክሌቶች ለማቅረብ 13 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው መወዳደርያ ገንዘብ ያቀረበ ኩባንያ አሸናፊ መደረጉ አግባብ አይደለም፣ የመንግሥትን የግዥ ሥርዓት ይፃረራል በማለት የአግታ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማይ  ወልደአረጋይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

“መንግሥትና ሕዝብን ሊከሳራና ለሕገወጥ ወጪ የሚዳርግና ፍትሐዊ የንግድ ውድድር እንዳይኖር ያደርጋል፤” በማለት የትምህርት ሚኒስቴር የግዥ ሒደት ሕገወጥ መሆኑን አቶ ግርማይ ተናግረዋል፡፡ 

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአግታን አቤቱታ በመቀበል ለትምህርት ሚኒስቴር ጨረታውን እንዲያቆም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 75 ንዑስ አንቀጽ 1 የግዥ አፈጻጸምና ንብረት አወጋገድ አቤቱታ አጣሪና ውሳኔ ሰጪ ቦርድ፣ አቤቱታ ሲቀርብለት፣ ወዲያውኑ አግባብ ላለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማስታወቂያ ይልካል፡፡ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስም ማናቸውም ቀጣይ እንቅስቃሴ ወዲያውኑ መቆም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ 

በዚህ መሠረት የጨረታ ሒደቱ የታገደ ሲሆን፣ በአዲሱ አጠራር በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለማየሁ ጉጆ የሚመራው የግዥ አፈጻጸምና ንብረት አወጋገድ አቤቱታ አጣሪና ውሳኔ ሰጪ ቦርድ፣ የመጨረሻ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ጨረታው በእግድ ይቆያል፡፡

ኤጀንሲው ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ዕገዳ ከማስተላለፍ በተጨማሪ፣ የጨረታ ሒደቱ ሙሉ መረጃና ቃለ ጉባዔ እንዲላክለት ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ 

የትምህርት ሚኒስቴር የግዥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረየሱስ ገብረ ሚካኤል በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ 

 

Girma Bekele   ከዚህ በፊት ስለ ‹‹የኢትዮጵያዊነት ብቸኛ ባለአደራዎች›› ና ‹‹ ኢትዮጵያ ሲባል አልስማ ›› ጽንፎች መጻፌ ይታወሳል፡፡ ሌሎቹ ሁለቱ ጽንፎች በአስተሳሰባችንና በተግባራችን የሚስተዋሉት ደግሞ በአንዱ ጥግ ቆሞ ቀርነት/ኋላ ቀርነት ሲሆን በሌላው ጫፍ ደግሞ ጥራዝ-ነጠቅነት ነው፡፡ በትውልድ መካከል ያለውን መሳሳብ …

ለምንለው ሁለንተናዊ ለውጥ —- ደንቃራ የሆኑት ሌሎቹ ሁለት ጽንፎችና መፍትሄው Read more »

Minilik Salsawi – የወያኔው መንግስት በራስ አለመተማመኑ እንደቀጠለ ነው::ከምርጫው በፊት በየትምህርት ተቋማቱ በየመስሪያ ቤቱ በስልጠና ስም ከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ገንዘብ አባክኖ በሕዝብ ሮሮ ናላው ዞሮ ማሾፊያ የሆነው እና በአጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ወያኔ ድህነትን አጠፋለሁ ልማት አለማለውሁ በሚ ሰበብ ከፍተኛ …

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስት ከምዝገባ ከትምህርት ከምግብ ማገድ አዲሱ የወያኔ ማስፈራሪያ ሆኗል:: Read more »

Getachew Shiferaw አምስተኛው ምክር ቤት ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል በድሮ ስርዓት በተለየ በርካታ ሴቶች የምክር ቤቱ አባላት መሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ሴቶች የድጋፍ ድምፅ በሚሰጥበት ጊዜ ከወንዶች እኩል አንዳንዴም ፈጥነው እጃቸውን በማውጣት ምክር ቤቱ የሚያቀርባቸውን ዕጩዎች በሙሉ ድምፅ ለማሳለፍ የበኩላቸውን በማድረግ …

እያረፍን እቅዱን እንደምናሳካው ቃል እንገባለን! Read more »

የሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር ሃሳን አልባሽር ደቡብ አፍሪቃን በጎበኙበት ወቅት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዳዘዘዉ ቁጥጥር ስር ያለማዋልዋን የአገሪቱ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጥብቀዉ እየተከላከሉ ነዉ።

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ካላካተቱዋቸው የቀድሞ ሚኒስትሮች መካከል የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድ፣ የንግድ ሚኒስትሩ ከበደ ጫኔ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አለማየሁ ተገኑ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አሚን አብዱልቃድር፣ የፕላን ኮምሽን ሚኒስትሩ አቶ መኮንን ማንያዘዋል ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም አቶ ሬድዋን ሁሴንን ከኮምኒኬሽን ሚኒስትርነት አንስተው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ያደረጉዋቸው ሲሆን፣ የህዝበ ሙስሊሙን …

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአመት በላይ ለሆነ ጊዜ በውጥረት ውስጥ የምትገኘዋ የጋምቤላና የደቡብ አዋሳኝ ከተማ ቴፒ፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ሶስት ዜጎች ተገድለውባታል። ከሳምንት በፊት የፌደራል ፖሊስ አባላት አንድ ሰው ከገደሉ በሁዋላ፣ ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ደግሞ ከቴፒ 7 ኪሜትር እርቀት ላይ በምትገኝ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ …

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2008 ዓ.ም በ መንግስት ያዘጋጀውን የፖለቲካ ስልጠና ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ደሞዛቸው እንዳይከፈል በመታገዱ የምንበላውና የቤት ኪራይ የምንከፍለው አጥተናል ሲሉ ገልጸዋል።በስብሰባው ላይ የተገኙ መምህራን ደሞዝ ሲከፈላቸው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰበሰቡት መምህራን ደግሞ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተነግሯቸዋል። በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ውጭ እንዳይወጡ ታግደው ስልጠናውን በግድ …

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ 10 ክፍለ ከተሞችና 116 ወረዳዎች የሚገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሹም ሽር እና የሹመት ቦታ ለውጥ መረጃዎች የታወቁ ሲሆን፣ የማዕከል መ/ቤት ቢሮዎችና ሹም ሽር ድልደላ በዚህ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሆኖ፣ በወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች አጠቃላይ ቁጥራቸው ከ800 የማያንሱ አመራሮች በሙስና፣ከድርጅቱ ጋር ባላቸው ተቃርኖ፣ በአመራር ብቃት ማነስ እንዲሁም በትምህርት ደረጃ …

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል መንገድ ስራ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚታዩ በርካታ የአሰራር ችግሮች ለከፍተኛ ሙስና ሊያጋልጡ እንደሚችሉ በመናገር በየጊዜው እንዲስተካከሉ ሰራተኛው ቢጠየቅም፣ ከዓመት ዓመት አለመቀረፋቸው በስርዓቱና አመራሮች እምነት እንዲያጡ እንዳደደረጋቸው የኦዲት ባለሙያዎች በዓመታዊው የሰራተኞች ስብሰባ ላይ ገልጸዋል፡፡ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ስር በሚገኙ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በተደረገ አጠቃላይ ምርመራ …

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርሳል ቲቪ ጋዜጠኞች የታሰሩት፣ ሁለት የፓርላማ አባላትን ጋብዘው የኢትዮጵያ ጦር በአገሪቱ ውስጥ መቆየት አለበት የለበትም የሚል ክርክር በማድረጋቸው መሆኑን የጣቢያው የዜና ክፍል ሃላፊ የሆነው ጋዜጠኛ አብዱላዚዝ ኢብራሂም ሙሃመድ ተናግሯል። በርካታ የሶማሊያ ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መቆየቱን መቃወም ጀምረዋል። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አልሸባብን በ2 ሳምንታት ውስጥ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የአዲሱ ካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ። ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ሲያሳውቁ አብዛኞቹ የመንግስት ባለስልጣናት በነበሩበት ሲቀጥሉ ጥቂት ለውጦች ደግሞ በሹመኞቹ ዘንድ ታይተዋል።

– አቶ ሬድዋን ሁሴን በሃስት ሲምሉለት የነበረውን ወንበር አጥተዋል:: – ሃይለማርያም ከኒውዮርክ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያቸው እንዳይወጡ ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገዋል:: – ጥያቄ የሚያበዙት አቶ አለማየሁ ተገኑ እና አቶ ሶፊያን አህመድ ከአሽከርነት ቦታቸው ተነስተዋል:: – ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው …

ዘራፊው ሕወሓት ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑ ወንበሮችን ለአሽከሮቹ አድሏል:: Read more »

በሞት አፋፍ ላይ ቀናቸውን በፀጋ የሚጠባበቁ የሰማንያ አምስት ዓመት ካናዳዊ አዛውንት የስቃይ ማስታገሻ መድሃኒታቸውን እየሰጠኋቸው እያለ “ከየት አገር ነህ?” ሲሉ ጠየቁኝ በደከመ አንደበታቸው። የተለመደ የነጮች ጥያቄ በመሆኑ እንደወትሮዬ “ከአፍሪካ ነኝ” አልኳቸው። ብዙዎቹ እያንዳንዱ አገርን ለይተው የማያውቁ ስለሆነ ለወትሮው በቂ መልስ …

የተራበች ኢትዮጵያ (ከአንተነህ መርዕድ) Read more »

Bewketu Seyoum ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን …

የተቸካዮች ምክር ቤት (በ.ሥ) Read more »

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፪ ግልጽ ደብዳቤ ለምንድን ነው «እንኳን በሰላም ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ» የምንባባለው? በሰላም ኖረን፣ሰላምን አጣጥመናት እናውቃለን ወይ? • ለኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ የኃይማኖት ተቋሞች፣ • በኢትዮጵያ ስም ለተደራጁ …

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፪ ግልጽ ደብዳቤ Read more »

Girma Bekele  ‹‹ቀጣዩ ትግል›› በጋራ አገራዊ አጀንዳ ላይ መቆም አለበት ስንል ፡-‹‹ አሮጌው እንዲሞት ፣ አዲሱም እንዲወለድ እስካልተባበርን የአገሪቱን የወደፊት ብሩህ ሕልም እውን ለማድረግ አንችልም›› ሙሉጌታ ሉሌ ለዛሬ እንዲህ ልጀምር፡፡ ከዚህ በፊት አንድ ቦታ ላይ ከአንድንድ ‹‹ፓርቲዎች›› ባልተናነሰ ለትግሉ አስተዋጽኦ …

‹‹ቀጣዩ ትግል›› በጋራ አገራዊ አጀንዳ ላይ መቆም አለበት ስንል ፡-‹‹ አሮጌው እንዲሞት ፣ አዲሱም እንዲወለድ እስካልተባበርን የአገሪቱን የወደፊት ብሩህ ሕልም እውን ለማድረግ አንችልም›› ሙሉጌታ ሉሌ Read more »

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች ላይ ከኢሕአዴግ መንግስት የሚሰነዘረው የፖለቲካ ጠልቃ ገብነትና አፈና ከመቼውም ጊዜ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በምሬት ተናግረዋል። የኢሕአዴግ መንግስት “ስልጠና’ በሚል ስም በአገር-አቀፍ ደረጃ ካዘጋጃቸው ስብሰባዎች አንዱ በሆነው ሰብሰባ ጠቅላላውን የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ከሰኞ መስከረም 10 እስከ …

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት እና አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ 4 ሚሊዮን 500 ሺ ህዝብ በረሃብ መጠቃታቸውን ይፋ ቢያደርጉም፣ በከተሞች የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ዜጎች ቁጥር ሲጨመር አጠቃላይ የተረጅዎችን ቁጥር ከ8 ሚሊዮን በላይ ሊያደርሰው እንደሚችል መረጃዎች አመልክተዋል። በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሪፖርት ሲደረግ የቆየው በገጠሩ የሚታየው ችግር ብቻ ነው። ይሁን እንጅ የከተማና …

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብና የጋምቤላ አዋሳኝ በሆነቸው ቴፒ ከተማ በየጊዜው የሚታየው የጸጥታ ችግር ሰሞኑን እንደገና አገርሽቶበታል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ካለፈው አመት ጀምሮ ከፍ ዝቅ እያለ ሲካሄድ የነበረው ግጭት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነትም ሰፍቷል። መስከረም 20 ብርሃኑ የተባለ የዩኒቨርስቲ ጥበቃ የተገደለ ሲሆን፣ ለግድያው እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ …

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጉንዶ መስቀል ከተማ በሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ1 200 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ መወሰኑን ተከትሎ በከተማው ውጥረት ነግሷል። የከተማው ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው ቤቶቻችሁን አፍርሱ ብለው ትእዛዝ ሲሰጡ፣ ነዋሪዎቹ ግን አጥብቀው ተቃውመዋል። መስከረም 13 ቀን በከተማው የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በፌደራል ፖሊሶች ቢጨናገፍም፣ ውጥረቱ አሁንም …

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጠዋት በሳሸመኔ ተክለሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን መቅደስ ውስጥ ካህናትና ዲያቆናት እርስ በርስ በመደባደባቸው ሰዎች ተገድተዋል። የግጭቱ መንስኤ የቆየ መሆኑን የሚናገሩት ምእመናኑ ዛሬ የተፈጠረው ድርጊት ግን ያልተጠበቀ ነው። ካህናቱ ጎራ ለይተው መደባደባቸውን ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎአል። ኢሳት ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ባይችልም፣ በሰአቱ የተኩስ ድምጽም ተሰምቷል። ጥይቱን …

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች “መልካም ስም ከመቃብር በላይ ዘላለማዊ ሆኖ ይኖራል” በሚል ርዕስ ባወጡት መግለጫ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲረጋገጥ፤ ብሎም ለአዲሱ የፕሬስ ትውልድ ፈር ቀዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ለብዙዎች የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ቤተሰቦች መሪር ሃዘን ነው ብለዋል። ጋዜጠኛ …

አንጋፋዉ ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ በ79ዓመቱ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቅርብ ጓደኞቹ የብዕር አርበኛ እያሉ የሚያወድሱት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ፀጋዬ ገብረመድህን አርአያ በሚል የብዕር ስምም ይታወቃል።

ለዲሞክራሲ ብርታትና ለእውነተኛ ውክልና ማመላከቻ ነፃ እና ቀጥተኛ ምርጫ ዓይነተኛ ሚና አለው፡፡ይህ ሲሆን በህዝብ ለህዝብ የተመረጡ ተገቢውን ውክልና ያገኙ፣ የህዝብ ተወካዮችን ማገኘት እና “የተወካዮች ምክር ቤት” አለ ለማለት ከዋና መመዘኛዎች ወስጥ ማመላከቻ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ በዲሞክራሲ አፈና እንዲሁም …

ውክልና የሌለው “የተወካዮች ምክር ቤት” ! (ይድነቃቸው ከበደ) Read more »

የወረቀት ገንዘብ ግራፊቲ ስራችንን ከጀመርን ሳምንት ሆኖናል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከሕዝባችን በኩል የታየው ሞራል እና ተሳታፊነት አስደስች እና አበረታች መሆኑን ዛሬም ዳግም ማየት ተችሏል፡፡ ይህን መሰል ዘመቻዎች የትግላችንን ድምጽ በማጉላት እና በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር በኩል ያላቸው ሚና የጎላ ነው፡፡ …

የወረቀት ብር ግራፊቲ ስራችንን ወጥነት እናላብሰው! ለአንድ ወር ያክል በብር ኖቶች ላይ የትግላችንን ሎጎ ብቻ እናሰፍራለን! Read more »

አንድ ጓደኛዬ የሚከራይ ቤት ጠይቅልኝ ብሎኝ ወደ አንድ ደላላ ዘንድ አቀናሁ፡፡ በቦታው ስደርስ ቀጫጫውን ደላላ አንድ ወፍራም በግምት 40 አመት እድሜ ያለው ጎልማሳ ይዞ ጠምዝዞ ያስጮኸዋል፡፡ ‹‹አይለምደኝም!›› ያሰኘዋል፡፡ ሰው እያየ አልፎ ይሄዳል፡፡ እኔም ምንም ማድረግ ስላልቻልኩ እስኪለቀው ድረስ ቆሜ መጠበቅ …

ስምን ተግባር ሲያወጣው (ጌታቸው ሺፈራው) Read more »

አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለየ። በትላንትናው እለት ከቀትር በኋላ እኔ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማና ጋሽ ሙሉጌታ በሲልቨር ስፕሪግ ምሳ በልተን፣ ስለመፅሀፍ እያወራን ከዋልን በኋላ በሰላም ነበር የተለያየነው። በዛሬው እለት ግን ቨርጂኒያ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በተኛበት ህይወቱ …

ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከዚህ አለም በሞት ተለየ Read more »

ጤፍን ጨምሮ ነባር ዝርያዎች አደጋ እንደተጋረጠባቸው በጥናት ተረጋገጠ

ዝርያዎችን ለመታደግ አገር አቀፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል

ጤፍን ጨምሮ በአርሶ አደሩ ዕጅ የሚገኙት የስንዴ፣ የገብስ፣ የዳጉሳና የሌሎች አዝርዕት ነባር ዝርያዎች አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ፡፡ ከተሻሻሉ ዝርያዎች አኳያ ያላቸውን የተሻለ ምርታማነት ከግምት ባለማስገባት በተሻሻሉና በድብልቅ

ዝርያዎች ለመተካት በሚደረገው ሙከራ ሳቢያ፣ የነባሮቹ ዝርያዎች ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን በጥናት መረጋገጡን፣ የኢትዮጵያና የዓለም አቀፍ የብዝኃ ሕይወት ተቋማት ገልጸዋል፡፡

በተለይ በጤፍና በስንዴ ላይ በተደረጉ ጥናቶች በተፈጥሮ ይዞታቸው የሚታወቁት ነባር የአርሶ አደሩ ዝርያዎች፣ በሳይንሳዊ መንገድ ተዳቅለው ‹‹የተሻሻለ ዝርያ›› ተብለው የሚሰራጩት በምርታማነታቸውና በተስማሚነታቸው ውጤታማ መሆናቸውን የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎችና ተመራማሪዎች መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድተዋል፡፡

በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ገመዶ ዳቤ፣ ‹‹በተደጋጋሚ እንደሚነሳው የእኛ ያልሆኑ ዝርያዎች ምርታማ አይደሉም ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከዓለም አቀፉ የብዝኃ ሕይወት ተቋም ጋር በጋራና በተናጠል ባደረግናቸው ጥናቶች ለአገር በቀል ዝርያዎች የተሰጠው ግምት የተሳሳተ እንደሆነ ከመረጋገጡም ባሻገር፣ በዘመናዊና በሳይንሳዊ መንገድ ተሻሽለው ተዘጋጁ ከሚባሉት የተሻለ ምርታማነት እንዳላቸው ተረጋግጧል፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም፣ ‹‹በእጃችን ያለውን እምቅ ኃይል ሳንጠቀም ከውጭ በመጡ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ለማድረግ በመሞከራችን የራሳችንን አገር በቀል ዝርያዎች አደጋ ውስጥ እየጣልናቸው ነው፤›› በማለት ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተቋሙ ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ፋንታሁን ባሳዝነው በበኩላቸው፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ጤፍን ለዓለም ያበረከተችና ጤፍም ከ4,000 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ቢኖረውም፣ በአገሪቱ ከስንዴና ከገብስ በፊት ምርምር ማድረግ ቢጀመርም፣ በአሁኑ ወቅት በተሻሻሉ ዝርያዎችና በሌሎችም ምክንያት ጤፍ አደጋ ተደቅኖበታል በማለት፣ ወደፊት ሊጠፋ ይችላል የሚለውን ሥጋት አጠናክረዋል፡፡

‹‹ይህ ዝርያ (ነባሩ ጤፍ) ከባህር ወለል በታች ከ3,000 እስከ 1,500 ሜትር ከፍ ሲልም እስከ 1,700 ሜትር፣ በአገራችን መመረት ይችላል፡፡ እንዲሁም በአገራችን አርሶ አደሮች ዕጅ ያለው የጤፍ ዝርያ በምርታማነቱ የበላይነት ከፍ ያለ ቢሆንም፣ አሁን አሁን ግን በተሻሻሉ ዝርያዎችና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ነባር ዝርያዎች ከፍተኛ አደጋ መጥቶባቸዋል፤›› በማለት ተባባሪ ተመራማሪው አስጠንቅቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ከ5,900 በላይ የጤፍ ዝርያ ናሙናዎች ተሰብስበው በኢትዮጵያ ዘረመል ባንክ ውስጥ እየተጠበቁ ሲሆን፣ በዚህ ሰብል ዝርያ ላይ የሚደረገው ናሙና የማሰባሰብና የባህርይ ትንተና ሥራ በግብርና ሳይንስ ምርምር ከ1950ዎቹ መጨረሻ አንስቶ ነበር የተጀመረው፡፡

እንደ ኃላፊዎቹ ከሆነ የባህርይ ትንተና አካል የሆነው ምርምር በ2006 እና በ2007 ዓ.ም. ተካሄዶ ነበር፡፡ ምርምሩም 12 የአርሶ አደር ዝርያዎችና ቁንጮ ተብሎ የሚታወቀውን ጤፍ ጨምሮ ሦስት አዳዲስ ዝርያዎችን (የተሻሻሉ ዝርያዎች) ያካተተ ሲሆን፣ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በሌሎች አራት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የአርሶ አደር ማዕከላት ውስጥ የምርምር ሥራዎች መከናወናቸው ተነግሯል፡፡

በምርምር ሥራው የተገኙትን ውጤቶች ይፋ ያደረጉት አቶ ፋንታሁን፣ ‹‹ለማወዳደሪያነት በተረመጡት የተሻሻሉ ዝርያዎችና በአርሶ አደር ዝርያዎች መካከል መመዘኛ በተደረጉት ከመድረሻ ቀን፣ ከእህል ምርት፣ ከቁመት፣ ከዛላ እርዝመት አንፃር ሲታይ በስታትስቲክሳዊ ሥሌት መሠረት ልዩነት እንደሌላቸው ታይቷል፤›› ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ የተለቀቁት የተሻሻሉ ዝርያዎች የተሻለ የምርት መጠን እንደሚኖራቸው በስፋት የሚታመን ቢሆንም፣ በተጠቀሱት የናሙና ውጤቶችና በስታትስቲክሳዊ ሥሌቶች መሠረት የአርሶ አደሩ ነባር ዝርያዎች የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡

ለአብነት ያህል ቁንጮ በሚባለው የተሻሻለ የጤፍ ዝርያና በነባሩ ዝርያ ላይ በአራት አካባቢዎች በተካሄደ ጥናት መሠረት፣ ነባሩ ዝርያ በሔክታር 22 ኩንታል ምርት ሲሰጥ ቁንጮ ግን 21 ኩንታል ብቻ መስጠቱን በአስረጅነት ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ጤፍ ሁሉ በሌሎችም የአዝርዕት ዓይነቶች ላይ ተመሳሳይ ውጤት መታየቱን የሚገልጹት የተቋሙ ተመራማሪዎችና ኃላፊዎች፣ አገር በቀል ዝርያዎች ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸውና የተለየ የአመራረት ፓኬጅም ተግባራዊ መደረግ እንደለበት አሳስበዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የብዝኃ ሕይወት ተቋም በበኩሉ በአማራና በትግራይ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ሥፍራዎች በስንዴና በዳጉሳ ላይ ባካሄዳቸው የናሙና ጥናቶች፣ ከውጭ ከሚገቡትም ሆነ ከተዳቀሉት የተሻሻሉ ዝርያዎች አኳያ በሚሰጡት የምርት መጠንና በጥራት አገር በቀሎቹ ነባር ዝርያዎች የተሻሉ መሆናቸውን ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ብዝኃ ሕይወት ተቋም ተጠሪ ካርሎ ፋዳ፣ ስኮላ ሳንታ አና ከተባለው የጣሊያን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምር በተካሄደ ጥናት፣ በአርሶ አደሩ ዕጅ የሚገኙትና ለማካሮኒና ለፓስታ ማምረቻ የሚያገለግሉ ስንዴዎች (ዱረም) በተፈጥሮ ካላቸው የዝርያ ተያያዥነትም ሆነ ዘረመል አወቃቀር አንፃር፣ ለገበሬው ከተሰራጩ የተሻሻሉ ዝርያዎች (Mediterranean Group)  ከሚባሉት በእጅጉ የተሻለ ምርታማነት እንደሚታይባቸው አስረድተዋል፡፡ 

አደጋ ተደቅኖባቸዋል የተባሉ ዝርያዎችንና ሌሎች በይፋ ያልተለዩ አገር በቀል ዝርያዎችን በተሻለ መንገድ ለመጠቀምና ‹‹ከመዋጥ ሥጋት›› ለማዳን፣ የተለየ ፓኬጅ  በመዘጋጀቱ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ዋና ዳይሬክተሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ረዘም ላሉ ዓመታት ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በተያያዘ መንግሥት ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ትኩረት መስጠቱን፣ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡ በተለይ ለምርትና ለምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ መሆኑን የሚገልጸው መንግሥት፣ በግብርና ምርምር አቅምና በቴክኖሎጂ መስክ ዕድገት እየተመዘገበ መምጣቱን ደጋግሞ ሲናገር መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የምርምር ማዕከላትን በመላ አገሪቱ እየተስፋፉ በመምጣታቸው በተሻሻሉ ዝርያዎች የተሻለ ውጤትና ተስፋ እየታየ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የአሁኑ የጥናት ውጤት ግን ጥያቄን አጭሯል፡፡ በተለይ ባለፉት ዓመታት መንግሥት የግብርና ምርምር ተቋማት እንዲስፋፉና የነባሮችንም አቅም በማሳደግ በግብርና ምርት ዕድገት መታየቱን ይገልጻል፡፡ ነገር ግን በዘርፉ የተሰማሩ ተመራማሪዎች፣ የእስከዛሬው ጥረት አሁን ይፋ ከወጣው የጥናት ውጤት አኳያ ሲታይ የቀድሞዎቹ ኢንቨስትመንቶችና ጥረቶች ተገቢነት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ ያሳደረ መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ሙስና በአዲስ አበባ በኔትወርክ በመያያዙ ከኢሕአዴግ በስተቀር የሚፈታው እንደሌለ ተነገረ

ተመዘገበ የተባለው የባለሥልጣናት ሀብት ይፋ እንዲደረግ ተጠየቀ 

‹‹በየስብሰባው እየተወዳደሱና በጭብጨባ እየተደጋገፉ መለያየት ይቁም›› የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በኔትወርክ የተያያዙ በመሆናቸው ሊፈታቸውም ሆነ ሊያስቆማቸው የሚችለው ‹‹ድርጅቱ›› ኢሕአዴግ ብቻ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ለግማሽ ቀን አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የሁሉም ክፍላተ ከተሞች፣ ወረዳዎች ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ነበር፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደተናገሩት የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ 

በመጠናቀቅ ላይ ካለው መስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ሊባል በሚችል ሁኔታ ከግንባታ፣ ከመሬትና ቤቶች ጋር በተገናኘ ነዋሪዎች እያለቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይ በአዲሱ የሥራ ዘመን ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ያወቁ፣ የጠረጠሩና ሹክሹክታ የሰሙ የክፍላተ ከተሞችና የወረዳዎች ተሿሚዎች ‹‹የሚፈርስ የማይፈርስ፣ መንገድ የሚወጣበት የማይወጣበት፣ ክርክር ያለበት የሌለበት፣ ግንባታ የተፈቀደለት ያልተፈቀደለት…›› በማለት በሥራ ሰዓትና ከሥራ ውጪ የነዋሪዎችን ግድግዳና የውጭ በር ቀለም ሲቀቡ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡን ሰላም እየነሳው በመሆኑ፣ የአስተዳደሩና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ሊያስቆሟቸው ወይም ዕርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል፡፡ 

በመቐለ ከተማ በተደረገው የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ አሥረኛ ጉባዔ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጥሩ ሥራ መሠራቱ የተገለጸ ቢሆንም፣ በመልካም አስተዳደር በኩል ግን ከፍተኛ ችግር እንደነበር መታመኑንና ፓርቲው ‹‹ተጠያቂ ነኝ ማለቱን››፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን ለተሳታፊዎች አስታውሰዋል፡፡ በመቀጠልም ይህንን ምቹ ሁኔታ ሕዝቡ መጠቀም ስላለበት ከመንግሥት ጎን በመቆም ብልሹ አሠራርን፣ ሙስናንና ሌሎች ለሕዝቡም ሆነ ለአገር የማይጠቅሙ አሠራሮችንና ድርጊቶችን ማጋለጥ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ 

በየስብሰባው በመወዳደስና በጭብጨባ በመደጋገፍ መንቀሳቀስ መቆም እንዳለበትና ሕዝብ ያስቀመጠው ኃላፊ ለሕዝብ ማገልገል እንዳለበት መንገር ያለበት ኅብረተሰቡ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ በየስብሰባው የጉንጭ ጅምናስቲክ ሠርቶ መለያየትን ቆም አድርጎ ባለሥልጣኑ የሚጓዝበት ተሽከርካሪ፣ የሚኖርበትና የሚከፈለው ደመወዝ ሕዝቡ በሚከፍለው ታክስ መሆኑን በመግለጽ፣ በአግባቡ እንዲያገለግለው መናገር እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ 

የኮሚሽነሩን ማብራሪያ ተከትሎ የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ የመንግሥት ተሿሚዎች የሕዝብ ሀብት በሙስናና በኪራይ ሰብሳቢነት እንዳይበዘብዙና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማለት የሕዝብ ተሿሚዎች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማድረጉ ትልቅ ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የመንግሥት ተሿሚዎች መመዝገባቸው ከመገለጹ ውጪ ለሕዝቡ ይፋ አልተደረገም፡፡ ተመዝግቦ በድብቅ መያዙ ትርጉም ስለሌለው የትኛው ባለሥልጣን ምን ያህል ሀብት እንዳስመዘገበ ለሕዝብ ይፋ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ሕዝቡ የሚያውቀውን ያህል ማስመዝገቡንና ያላስመዘገበም ከሆነ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት እውነቱ ላይ እንዲደርስ እንደሚረዳ ተሳታፊዎች አውስተዋል፡፡ 

ሀብታቸውን ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ይፋ እንዲደረጉ በተነሳው ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነር ዓሊ፣ መሥሪያ ቤታቸው ለማንም ክፍት መሆኑንና ማንም መጥቶ የሚፈልገውን ማስረጃ ማግኘት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ መረጃ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ ደብዳቤ ጽፎ፣ ‹‹የእከሌን ባለሥልጣን ሀብት ማወቅ እፈልጋለሁ?›› ካለ ወዲያውኑ እንደሚገለጽለት ተናግረው፣ በመገናኛ ብዙኃን ግን ‹‹የእከሌ ባለሥልጣን ሀብት ይህንን ያህል ነው፤›› ብሎ ይፋ ማድረግ ከሕግ አንፃርም እንደሚያስኬድና ነውር መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በዓለም ደረጃም ከሲንጋፖር በስተቀር የሁሉንም ዜጎች ሀብት መዝግቦ ይፋ ያደረገ አገር አለመኖሩን አክለዋል፡፡ በቅርቡ በኮሚሽኑ ድረ ገጽ በኢሜይል መጠየቅና መረጃ ማግኘት እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡ 

የመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ በተለይ በሙስና ተጠርጥረው ስለሚታሰሩና ስለሚፈረድባቸው ተከሳሾች ተናግረዋል፡፡ አንድ በሙስና የተጠረጠረ ሰው በርካታ ገንዘብ በሙስና ካገኘ በኋላ ዘመዶቹ ዘንድ በታትኖ በማስቀመጥ፣ ሲፈተሽ የሚገኝበት ጥፋት በጣም ትንሽ ስለሚሆን የተወሰነ ዓመት ታስሮ እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡ 

ከእስር እንደተፈታ ለተወሰኑ ወራት ቀድሞ ከሚኖርበት አካባቢ በመልቀቅ ከቆየ በኋላ አስመጪና ላኪ ሆኖ እንደሚታይ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ ይህንን የሚያዩ ተሿሚዎች የተወሰኑ ዓመታት ታስረው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው እንደሚተርፉ ራሳቸውን በማሳመን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ሀብትን እየበዘበዙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመለከተው አካል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ዕርምጃ ሊወስድበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ 

ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር ትምህርቱ ከአምስት ዓመት ሕፃን እንዲጀምር በኮሚሽኑ የቀረበውን ሐሳብ የውይይቱ ተሳታፊዎች ድጋፍ ሰጥተውታል፡፡ 

በመቐለው ጉባዔ የተደረገው ስምምነት እንዳለ ሳይቀነስ ወደ ታች መውረድ እንዳለበት ያሳሰቡት የውይይቱ ተካፋዮች፣ በተለይ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ዕጦት በሚታይባቸው ግብር አስከፋይና ንግድ ፈቃድ አዳሽ መሥሪያ ቤቶች የማይተገበር መመርያ እያወጡ የንግዱን ኅብረተሰብ ሳይወድ በግድ ወደ ሙስና እንዲገባ የሚያደርጉበት አሠራር ትኩረት እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡ የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ዕጦት ቢስተካከል ለውጥ ሊመጣ እንደሚችልም አክለዋል፡፡ 

‹‹ድርጅቱ ይታማል›› ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ተሿሚው እንክት አድርጎ ከበላ በኋላ እሮሮ ሲበዛበት ከነበረበት ቦታ ወይም ክፍለ ከተማ ተነስቶ ወደ ሌላ ክፍለ ከተማ ወይም ማዘጋጃ ቤት እንደሚሾም ገልጸው፣ ‹‹እርስዎ (አቶ ዓሊን) ለድርጅቱ ቅርብ ስለሆኑ ቢወያዩበትና መፍትሔ እንዲመጣ ቢያደርጉ የተሻለ ነው፤›› ማለታቸው የስብሰባውን ተሳታፊዎች አስፈግጓል፡፡ ከድርጅቱ ውጪ ማንም ሊፈታው እንደማይችልም አክለዋል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችን ችግር የሚፈታ መንግሥት እንዴት የሙስናን ችግር መፍታት እንዳቃተው እንዳልገባቸውም ተናግረዋል፡፡ 

ገዢው ፓርቲ ብቻውን የሚያደርገው ነገር እንደሌለ የገለጹት አቶ ዓሊ፣ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ድርጊቶችን ማስፈጸም እንዳልተቻለ የገለጹት አቶ ዓሊ፣ የማይገባ ድርጊት መፈጸሙ እየታወቀ ዞር ተደርጎ በከፍተኛ ደረጃ የሚሾም ተሿሚ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡ 

 

ታላቁ ያገር ባለውለታ ጄኔራል መኮንን በ1927 አመተ ምህረት በበለሳ ወረዳ በሊቦ አውራጃ በጎንደር ክፍለ ሀገር ተወለዱ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በ1945 አመተ ምህረት በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ተቀጥረው ለአንድ አመት ያህል የሬድዮ መገናኛ ትህምርታቸውን …

ሜጀር ጀኔራል ፋንታ በላይ ላገራቸው ሲሉ የሞትን ዕዋ የተቀበሉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጀግና Read more »

Yohanes Molla – Chocolate Porch/ጠይም በረንዳ -“ጂጂ ደህና ናት። አብረን ነው ያለነው። እንግዲህ አብረን እየተጫወትን፣ አብረን እየበላን እየጠጣን፣ እየወጣን እየገባን ነው ያለነው። (ሳቅ) ኒው ዮርክ ነው ያለሁት አሁን። ወሬውን ከተለያየ ሰው፣ በየኢንተርኔቱ ስናይ ደንግጠን ከእናቴ ጋር ከኦክላንድ ወደዚህ መጣን። ምንም …

ጂጂ ደህና ናት። — ሶፊያ ሽባባው Read more »

….እንግዲህ 547 ጎጆ ወጪዎች ወደ ጎጆዋቸው ሊገቡ ነው!….. የአምስት አመት የኮንትራት ኑሯቸውን ይጀመራሉ!……547ቱ የፓርላማ አባላት ናቸው ጎጆ ወጪዎች!…..ደግ አደረጉ በደህና ጊዜ ስማቸውን አስቀየሩት!….. ባይሆንማ ኖሮ መደበኛው ስማቸው ‘የህዝብ እንደራሴ” ነበር!…. እነሱስ አውቀውበታል!….እንደራሴ ብሎ ነገር የለም!…. ጭራሽ የህዝብ እንደራሴ!….ሆሆ!. የምክርቤት አባል …

ፓርላማ ለእንቦሳ! (የትነበርክ ታደለ) Read more »

በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ጊዜ በተሰናዳው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የታደሙት የሒልተንና የሸራተን ኃላፊዎች፣ መንግሥት በቅርቡ መተግበር በጀመረው የሆቴሎች ደረጃ አሰጣጥ አለመደሰታቸውን ገለጹ፡፡ 

በሒልተን ዓለም አቀፍ የአውሮፓና የአፍሪካ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ፊትዝጊቦን ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ስለሚገኘው የሆቴሎች ደረጃ አሰጣጥ ተጠይቀዋል፡፡ ሒልተን አዲስ አበባ የአራት ኮከብ ደረጃ ማግኘቱን ተከትሎ ቅሬታቸውን ካቀረቡ 11 ባለኮከብ ሆቴሎች ውስጥ አንዱ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ምንም እንኳ በደረጃ አሰጣጡ ሒደትና በሒልተን ውጤት ላይ አስተያየት ከመስጠት ቢጠነቀቁም፣ ደረጃ መዳቢዎች ከሚያወጡት የኮከብ ደረጃ ይልቅ የሒልተንን ማምነት የሚገልጸው ደንበኞች ከሒልተን የሚጠብቁት አገልግሎት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሒልተን ብራንድ ከሚሰጠው የኮከብ ደረጃ ይልቅ በደንበኞቹ ይታወቃል ያሉት ፊትዝጊቦን፣ በተዘዋዋሪ ከመናገር ውጪ በቀጥታ ቅሬታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ሸራተን አዲስ ሆቴልን የሚያስተዳድረው ስታርውድ  ሆቴሎችና ሪዞርቶች ዓለም አቀፍ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንትና የአፍሪካና የህንድ ውቅያኖስ የቀጣናው የኦፕሬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ሐሳን አህዳብም ከሪፖርተር ስለደረጃ አሰጣጡ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንደ አህዳብ አባባል በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ አገሮች ያሉ ደረጃ አውጪዎች ሊገነዘቡት የሚገባው የሆቴል ደረጃ አሰጣጥ ‹‹ጊዜው ያለፈበት›› ሥርዓት መሆኑን ነው፡፡ ሆቴሎች ባላቸው የብራንድና የቄንጠኝነት ደረጃ መመደብ አለባቸው የሚሉት አህዳብ፣ ከደረጃ አሰጣጥ ይልቅ በብራንድ ላይ መተኮር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በየጊዜው እየተቀየረ ባለው የሰዎች አኗኗር ሳቢያ የኮከብ ደረጃ ሆቴሎችን ገላጭ ሆኖ እንዳላገኙት በመጥቀስ፣ ሸራተን ባለአምስት ኮከብ ከመባል ይልቅ ‹‹ለግዠሪ ኮሌክሽን›› በሚለው ደረጃው በደንበኞቹ ዘንድ እንደሚታወቅ፣ ይኸው ብራንድም መገለጫው እንደሆነ በመግለጽ የኮከብ ደረጃ አሰጣጥን አጣጥለውታል፡፡ 

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሆቴሎች ደረጃ አሰጣጥን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት ከሆኑት መካከል ከዓለም የቱሪዝም ድርጅት ባለሙያዎች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ባስተዋወቀው የደረጃ አሰጣጥ ሥርዓት መሠረት፣ እስካሁን መግለጫ የተሰጠባቸው 95 ባለኮከብ ሆቴሎች በአዲስ አበባ ተመዝነው ውጤት ቢነገራቸውም እነማን እንደሆኑ ለሕዝብ ይፋ ከማድረግ ግን ሚኒስቴሩ ተቆጥቦ ቆይቷል፡፡ የአዲስ አበባ ሆቴሎች ደረጃ አሰጣጥን ካጠናቀቀ በኋላ ለቀረቡለት ቅሬታዎች ምላሽ በመስጠት የደረጃ አሰጣጡ ያካተታቸው ሆቴሎችና ያገኙትን ደረጃ ይፋ እንደሚያደርግ ቢያስታውቅም እስካሁን ዝምታን መርጧል፡፡ ይሁንና ባለአምስት ኮከብ ደረጃ ያገኙት ሸራተን፣ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል እንዲሁም ካፒታል ሆቴልና ስፓ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውጪ የተቀሩት ሆቴሎች ከአራት እስከ አንድ ኮከብ ባለው ደረጃ የተመደቡ ናቸው፡፡ 

ሒልተን ኢንተርናሽናል ሁለተኛውን ሆቴል በሐዋሳ ለማስተዳደር ከሰንሻይ ቢዝነስ ጋር በተዋዋለበት ሳምንት፣ ሸራተንን የሚያስተዳድረው ስታርውድ በበኩሉ በአፍሪካ 20 የሆቴል ፕሮጀክቶች ላይ እየሠራ መሆኑንና ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱን በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ይፋ አድርጓል፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ ምንም ይፋ የሚያደርገው የሆቴል ፕሮጀክት እንደሌለ የስታርውድ የአፍሪካና የህንድ ውቅያኖሶች ቀጣና ልማት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ኔል ጆርጅ አስታውቀዋል፡፡ 

አህዳብ በበኩላቸው ሸራተን አዲስን ከጥንስሱ ጀምሮ ሲያተዳድሩ ቆይተው በቅርቡ ያረፉት ዣን ፔዬር ማኒጎፍ በምክትላቸው ተተክተው ሆቴሉን የማስተዳደር ኃላፊነት እንደተረከቡና ሆቴሉ ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶችም ሳይስተጓጎሉ መቀጠላቸውን ከሪፖርተር ተጠይቀው አብራርተዋል፡፡ በሟቹ ማኒጎፍ አስተዳደር ጊዜ ከሠራተኞች ጋር የነበረውን ግጭት በሚመለከትም ተጠይቀዋል፡፡ ሟቹ በነበራቸው ሥራን በፍጥነት የመሥራት ፍላጎትና ችኮላ ይከሰቱ ከነበሩ ችግሮች ውጪ የጎላ ችግር እንዳልተፈጠረ ጠቅሰዋል፡፡ በአንፃሩ በተለያዩ ጊዜያት መብታቸውን በመጠየቃቸው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከሥራ ገበታቸው መሰናበታቸውን ሠራተኞች ሲገልጹና አስተዳደሩን ሲከሱ እንደነበር አይዘነጋም፡፡  

 

በዚህ ጽሑፍ የማነሣቸው ርእሰ ጉዳዮች በአራት የተከፈሉ ናቸው፡፡ አንደኛው፡-  ስለ ዩኒቨርስቲ አጠር ያለ መሠረታዊ ሐሳብ እና የአካዳሚያዊ ነጻነት መርሖዎች፤ ኹለተኛ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመንግሥት መዳፍ ሥር ስለ መውደቅ፤ ሦስተኛው፡- የፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬን ገጸ ሰብእና (persona) በኹለት ወጎች ሥር ማብራራት …

የዩኒቨርስቲው በር ተሰብሯል! ዐምዶቹም ተነቃንቀዋል! ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ (የአ.አ ዩ የቀድሞ የፍልስፍና መምህር) Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና