ጂጂ ደህና ናት። — ሶፊያ ሽባባው
Yohanes Molla – Chocolate Porch/ጠይም በረንዳ -“ጂጂ ደህና ናት። አብረን ነው ያለነው። እንግዲህ አብረን እየተጫወትን፣ አብረን እየበላን እየጠጣን፣ እየወጣን እየገባን ነው ያለነው። (ሳቅ) ኒው ዮርክ ነው ያለሁት አሁን። ወሬውን ከተለያየ ሰው፣ በየኢንተርኔቱ ስናይ ደንግጠን ከእናቴ ጋር ከኦክላንድ ወደዚህ መጣን። ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም። እሷም ስለሚወራው ነገር ምንም የምታውቀው ነገር የለም ነበር። አልሰማችም። እኛ ነን ከትናንት ወዲያ የነገርናት። ምንም የሆነ ነገር የለም። ደህና ናት እጅጋየሁ።….
እኔ ስለወሬው ምንጭ እርግጠኛ አይደለሁም። ምንጩ ምን እንደሆነ አላውቅም። ሁኔታዋን ሳያት ትንሽ privacy ምትፈልግ ይመስለኛል። ሰው የሚያልፍበት ብዙ የራሱ ነገር አለ። ምንም እንኳን የሚዲያ ሰው ብትሆንም፣ ለሰው ማጋራት የማትፈልገው የግል ነገር ይኖራታል። አሁን የምትፈልገው privacy ነው። …ያልሆነ ነገር ስትሰማ ይረብሻልና ስንነግራት ደንግጣለች።
‘ሚያስቡልኝን ሰዎች፣ ሚጨነቁልኝን ሰዎች thank you በሉልኝ። ስለኔ ተጨንቃችሁ ስላደረጋችሁት ነገር በሙሉ አመሰግናለሁ። ምንም አልሆንኩም ደህና ነኝ።’ በዪልኝ ነው ያለችው። …ለያንዳንዱ ሰው መልስ ሰጥተንም የምንጨርሰው ነገር አይደለም። እና ተጨንቀህ መደወልህ፣ ትክክለኛው መረጃ ለብዙ ሰው እንዲያደርግ ያስችላልና እናመሰግናለን።”
(በቻልኩት ፍጥነት ስታወራ፣ በቀጥታ ስለተየብኩት፥ ቃል በቃል ላይሆን ይችላል)
— ሶፊያ ሽባባው (ከታዲያስ አዲስ ጋር ያደረገችው የስልክ ቆይታ) ከተቻለ በኋላ ወይም በቀጣዩ ሳምንት በቀጥታ ስልክ (ወይም በተቀረጸ ድምጽ) ያስገቧታል።
በግሌም ያደረግኩት ማጣራት ይህንኑ ነበር ያረጋገጠልኝ።
ክፉ አይንካሽ ጂጂዬ፣ የኔ ንግስት I love you to death!
P.S. እንግዲህ የደህንነቷንም ወሬ SHARE በማድረግ መልእክቱን ለወዳጆቿ አድርሱ። መውሰድ ያለባትን የግል ጊዜዋን ወስዳ በአዲስ ስራ እንድትመለስ እንናፍቃለን።
