በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስት ከምዝገባ ከትምህርት ከምግብ ማገድ አዲሱ የወያኔ ማስፈራሪያ ሆኗል::
Minilik Salsawi – የወያኔው መንግስት በራስ አለመተማመኑ እንደቀጠለ ነው::ከምርጫው በፊት በየትምህርት ተቋማቱ በየመስሪያ ቤቱ በስልጠና ስም ከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ገንዘብ አባክኖ በሕዝብ ሮሮ ናላው ዞሮ ማሾፊያ የሆነው እና በአጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ወያኔ ድህነትን አጠፋለሁ ልማት አለማለውሁ በሚ ሰበብ ከፍተኛ የሆነ እዳ በሃገሪቱ እና በመጪው ትውልድ ላይ በመጫን ህዝብን ለባሰ ድህነት በመዳረግ ላይ አልበቃ ብሎት ይህን ሰሞን ደግሞ ስልጠና ካልሰጠኋቹህ ምዝገባ የለም ምግብ የለም ትምህርት አትማሩም በማለት ተማሪዎችን ሲያጉላላ መምህራንን ደሞ ደሞዛቸውን በመቁረጥ አዲስ ሕዝብን የማሸማቀቂያ እና ማስፈራሪያ ስልት ጀምሯል::
በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስታወቂያ ቦርድ እና በበራሪ ወረቀትነት እየታደሉ የሚገኙት ወረቀቶች እንደሚያመለክቱት ማንኛውን ተማሪ ይሁን መምህር በወያኔ ስልጠና ላይ ካልተገኘ እንደሚታገድ ይገልጻል::በረሃብ ይቀጣል::አስፈላጊ ነገር አያገኝም ይባረራል::ተማሪዎችን ይሁን መምህራን ምንም አይነት ፊት ያልሰጡት ይህ ስልጠና እንደባለፈው ስልጣና ውጤት አልባ እና መቀለጃ እንደሚሆን የሚገልጹ ተማሪዎች የሃገር ሃብት ከማባከን ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም በማለት ላይ ይገኛሉ::አንድን ሕዝብ እመራለሁ ብሎ ነጋጠባ ከሚገዘት አምባገነ የሃሰት ስርኣት የሚጠበቅ ቢሆንም ተማሪዎች ይሁኑ መምህራን መብቶቻቸውን ለማስከበር ታጥቀው መነሳት ይጠበቅባቸዋል::

It is absolutely shame and fully frustration of the bancrupted regime
The year we are by now indicates the fall of the narrow nationalist woyanes
You Ethiopian teachers and students you are the foundation of this country and that is why this blind regime is trying to demoralize your bright future so don’t give up and stand together
መቼ ይሆን ስለ ኢትዮጵያ መልካም ነገር የምትፅፉት?ያ ቀን ናፈቀኝ!!!
Minelik salsawi no more one biher.nom more one kanka no more one ethiopia.viva federalisime.
እውነት ነው! ከምርጫ 2005 GTP1 ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች ባጠቃላይ ግዳጅ
የወያኔ ሠበካ ጉባኤን እንድትሣተፋ በማለት ከፍተኛ ማሥፈራት እና ተማሪውን በውጤት
መቅጣት ሥልት ከኤርትራው ሣዋ ውትድርና ያልተናነሠ ሥነልቦና ቀውሥ ውሥጥ ይገናሉ እሥቲ
ተምራችሁ በኛ ሥርአት ውሥጥ ካልገባችሁ ሥራ የለም ተሥፋ የላችሁም ድንጋይ ትፈልጣላችሁ
ወዘተ በማለት የሥርአቱ አምላኪ ሆነው እንዲቀረፁ እያረጉ ነው ይህ ነው የማይባሉ ፀረ ወያኔ
መምህራንን ከሥራ ገበታቸው አባሮ የራሡን ኮርማ መምህራንን ቀጥሯል ሌላው ለምሣሌ ያህል
ካገኘሁት መረጃ ተነሥቼ ጎንደር ዩኒቨርሥቲ የሚገኙትን ተማሪዎች አቅራቢያቸው ያለው
የመከላከያ ፋውንዴሽን በርካታ ተማሪዎችን ብር እየከፈለ ማሠልጠን ጅምሯል ይህም አበል
ተምረው ሢጨርሡ በእዳ ተመዝግቦ ይህንን ሣይከፍሉ ንቅንቅ እንደማይሉና የሠራዊት ህግና
ደንብ መሠረት አሥብቱ በሥንት አመታቸው እንደሚሠናበቱትና በቃ የሥርአቱ አምላኪ በማረግ
እያመከነ መሆኑን ሁላችንም እንገንዘብ።
ግመሎችም ይሄዳሉ ውሾችም ይጮሀሉ!ትኩረቱ ከሀሳቡ እንጅ ከሀሳብ ሰጭው አይደለም!ብልህነት እንደዚህ ነው