በሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል ክስ ከነ አቶ አንዱዋለም ጋር ታስረዉ የነበሩ አቶ ዘመነ ሞላ እና አቶ አሳምነዉ ብረሃኑ ፣ ትላንት ማክሰኞ ኖቬምበር 15 ቀን የተፈቱ ሲሆን፣ አቶ ደበበ እሸቱና አቶ ስለሺ ሃጎስ ደግሞ፣ ዓርብ ኖቬምበር 11 ቀን እንደተፈቱ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያለመክታል። እነዚህ ወገኖች በምን ምክንያት እንደተፈቱ ለጊዜዉ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ገዢዉ ፓርቲ በሽብር […]

ይህን ጥያቄ፤ ለአንድ ጤነኛ ሰው ቢያቀርቡለት፤”እንደዚህ የሚሉት(ያሉት)፤ለትግሬዎች ጥላቻ ያላቸው ናቸው”ሊል እንደሚችል ግልፅ ነው።ይህ አያከራክረንም።አከራካሪ የሚሆነው፤እነዛ፤ ለትግሬዎች ጥላቻ ያላቸው፤ እነማን ናቸው?” የሚለው ተከታይ ጥያቄ ነው። ግን.. ይህን ያለው ማን ይመስላችሁዋል? ቅንጅት? የቅንጅት ደጋፊዎች?ህብረት? የግል ጋዜጦች? ወይስ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች? “ትግሬን ወደ መቀሌ፤ንብረቱን ወደ ቀበሌ” ብሎ በአደባባይ ያወጀው፤ ህወሀት ቢሆንስ ምን ይሰማችሁዋል?ምንስ ትላላችሁ? በእርግጥ ህወሀት፤በገዛ አባሎቹ […]

ነዋሪው የስብሰባውን አዳራሽ ጥሎ ለመውጣት የተነሳሳው፤በአዲሱ የመሬት ሊዝ አዋጅና በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ፣የክፍያ ስርዓትና ባለይዞታዎች በካሬ ሜትር እንዲከፍሉ በተተመነው ገንዘብ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ጥያቄ አቅርበው ከመድረክ መላሽ በመነፈጉ ምክንያት ነው፡፡ ዕሁድ ሕዳር 3 ቀን 2004 ዓ.ም በየካ ክ/ ከተማ የቀድሞ ወረዳ 12 ነዋሪ፤ከፈረንሳይ ኤምባሲ ዝቅ ብሎ የሚገኘው ፈረንሳይ መናፈሻ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ጀምሮ […]

የዳዉሮ ዋካ ህዝብ ቀን 2011-11-15 የኔሰው ገብሬ ይባላል። ዕድሜው ወደ 29 አመት ነው።ሥራው መምህር ነበር።የተወለደው በጂማ ከተማ ዉስጥ ሲሆን የአንደኛም ሆነ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው እዚያው ጂማ ከተማ ነበር። ከዚያም ወደ ዋካ ከተማ በመምጣት ታላቅ እህቱ ዘንድ ኑሮዉን አደረገ። ከዚያም ወደ መምህራን ኮሌጅ በመግባት በመምህርነት ሰልጥኖ በዳዉሮ ዞን ዉስጥ በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች […]

በደቡብ ክልል ዳዉሮ ዞን ተርቻ ከተማ በባለስልጣናት ይካሄዳል ያለውን ኢፍትሃዊ የአስተዳደር አሠራር በመቃወም ራሱን የሰዋው የአካባቢዉ ነዋሪ የቀብር ሰነ…

በቀድሞ ባለቤቱ በደረሰባት ጥቃት ሁለት አይኖቿን ያጣችው ተጠቂ በአዲስ አበባ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የጾታ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል ህግና የማስፈጸም ብቃት እንዲጠናከር ጠይቃለች።

ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዋካ ከተማ ነዋሪ የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬ የስድስት ወረዳዎች ባለስልጣናት በአንድነት ተሰባስበው በቅርቡ በዋካ የተፈጠረውን ችግር በሚወያዩበት ወቅት፣ በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ እየተቃጠለ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ገብቷል። መምህሩ ራሱን እያነደደ ወደ ውስጥ ሲገባ የተመለከቱት የወረዳ ባለስልጣናት በመደናገጣቸው ከመምህሩ ለመራቅ ጥረት ያደርጉ ነበር ተብሎአል። ምሁሩ በከተማው ውስጥ ከሚታወቁት በሳል […]

አጭር መልእክት መጻፍ አሰኘኝ – ደካክሞኝ ልተኛ ስል፡፡ ከበፊትም የነሱና የኛ ታሪኮች መመሳሰል በጣሙን ያስደንቀኝ ነበር፡፡ የነሱና የኛ ችግር ተቀራራቢ እንደሆነ በተለይ ካለፉት ስምንትና ዘጠኝ ወራት ወዲህ እነሱ እየደረሰባቸው በሚገኘው የጭፍጨፋና የግድያ የሰቆቃ ኑሮ መገንዘብ ችያለሁ – የሁለታችንም አሳዳሪ ጌቶች ክፉኛ ጨካኞች ናቸው – ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው፡፡ እነሱ እንደሕዝብ በጣም ጠንካሮች ናቸው፡፡ እኛ ግን የነሱን የብቃት […]

ህወሀት ለሁለት ከተከፈለ በሁዋላ እነ ስዬ፤ እነ መለስን የሚገልጿቸው፦”ተንበርካኪው የቤተ-መንግስት ቡድን”እያሉ እንደነበር ብዙዎቻችን እናስታውሳለን። ምክንያታቸውም፦”መለስ በምዕራባውያን ተጽዕኖና ትዕዛዝ የሚሽከረከር አሻንጉሊት እንጂ፤ የራሱ የሆነ አቋም የሌለው ልፍስፍስ ሰው ነው” የሚል ነበር። ለዚህም ከማሌሊት ምሥረታ ዋዜማ አንስቶ አስከ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ድረስ ፤አቶ መለስ መልካቸውን ከምሥራቁና ከምዕራቡ ዓለም መስተዋት ጋር ለማስተካከል ያደረጓቸውን በርካታ መገለባበጦች በዝርዝር አስቀምጠዋል። በነገራችን ላይ […]

ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ የፍትህ ሚኒስቴር፣ ለልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በ26 ተከሳሾች ላይ ወደ ስድስት የሚደርሱ ክሶችን በይፋ ጥቅምት ሰላሳ 2004 ዓ.ም አቅርቧል። የፍትህ ሚኒስቴር ከከሰሳቸዉ 26 ተከሳሾች መካከል፣ በአንደኛ ተከሳሽነት የተጠቀሱት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አንዱዋለም አራጌ፣ በስምንተኛ ተከሳሽነት የተጠቀሱት አንጋፋዉ ጋዜጠኛ አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ስምንት […]

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱትና በጠንካራነታቸው ከሚጠቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የነበረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራ