የወያኔ ፍርድ ቤት የአቃቤ ህግ በእነ ኤልያስ ክፍሌ ላይ ያለውን መረጃን አዳመጠ

የወያኔ ካንጋሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬም በሸባሪነትና መንግሥትን በሐይል በማስወገድ የተከሰሱ አምስት ጋዜጠኞችንና የተቃዋሞ ፖለቲከኞችን ክስ ሲያደምጥ ዉሏል። አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ያቀረበዉን መረጃ ተከታትሎ፥ የተከሳሽ ጠበቆችን የመከላከያ ክርክር አድምጧል። ፍርድ ግን አልሰጠም። ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የጀርምን ራዲዮ የአዲስ አባባ ታደሰ እንግዳዉ ዝርዝር ዘገባ አለዉ። ያድምጡ