ሆስተሷ ስለተፈጸመባት ጥቃት ፍርድ ቤት ቀርባ መሰከረች

“ልቤ ተሰብሯል” ሆስተስ አበራሽ ኃይላይ

ሁለት ዓይኖቿ በስለት ተወግተው በመጥፋታቸውና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባት፣ ታይላንድ ባንኮክ ሆስፒታል በሕክምና ላይ የምትገኘው ሆስተስ አበራሽ ኃይላይ፣ ከትናንት በስቲያ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ፣ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የምስክርነት ቃሏን አሰማች፡፡