የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ 640 ሠራተኞችን አሰናበተ

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥን ተግባራዊ ለማድረግ በሠራተኞች መካከል ባካሄደው ውድድር፣ ‹‹ውድድሩን ማለፍ አልቻሉም›› ያላቸውን 640 ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡