በአሸባሪነት የተጠረጠሩት ጋዜጠኞች የክስ ሒደት
በሌላ ዜና ሁለት ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ መንግሥት ይፈፅምብናል ያሉትን ዛቻና ማስፈራሪያ ሽሽት ወደ ዉጪ ሐገር መሰደዳቸዉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሸባሪነት ክስ የተመሠረተባቸዉን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና የጋዜጠኞችን ክስ ሒደት ዛሬ ሲያደምጥ ዋለ።አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት በግላቸዉ ጠበቃ ማቆም ላልቻሉ ተከሳሾች መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸዉ አዞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል።በሌላ ዜና ሁለት ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ መንግሥት ይፈፅምብናል ያሉትን ዛቻና ማስፈራሪያ ሽሽት ወደ ዉጪ ሐገር መሰደዳቸዉ ተዘግቧል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል። ያዳምጡ