የኃየሎም አርአያ አሟሟት (ክፍል 2)

በዳዊት ከበደ ወየሳ – አትላንታ

አንዳንድ ወዳጆቻችን ባለፈው ሰሞን ባወጣሁት የኃየሎም ግድያ ዙሪያ ቅሬታቸውን ገልጸውልኛል። ሆኖም በኔ ውስጥ ያለውና እነሱ የሚሉት እውነት አይገናኝም። ለነገሩ ብዙዎቹ ዘገባዎች ሀገር ቤት እያለሁ ያወጣኋቸው ናቸው። ይሄንን ጽሁፍ ለየት የሚያደርገው ዝርዝር ትንታኔ ውስጥ በመግባቴ ነው። አሄንም ቢሆን በእኔ እምነት ነገሮችን በመሸፋፈን የምንሄድበት መንገድ ሌሎች እውነቶችን እንዳንመለከት ያደርገናል። ምንም እንኳን ጀሚል ያሲን ግድያውን ቢፈጽምም፤ የተደረገበትን ኢሰብአዊ ተግባር አልደግፍም።